ሩሲያ ሰራሹን Pantsir የአየር መቃወሚያ ሀገራችን ታጠቀች …
(በጋዜጠኛ እስሌማን አባይ)
– የአንዱ ዋጋ እስከ 300 ሚሊዮን ዶላር ነው ሲደርስ 120 ሚሳይሎች እና 9 መተኮሻዎች ይኖሩታል!
– ቻይና ፣ ሳውዲአረቢያ ፣ ቱርክ ፣ ህንድ እና ቤላሩስ ታጥቀውታል!!
– 400 ኪ.ሜ ድረስ ኢላማን የመምታት አቅም አለው!
ዝርዝሩ እነሆ!!
“የመከላከያ አቬሺን ይፋ እንዳደረገው የህዳሴ ግድቡ የአየር ቀጣና ከአየር በረራ ነፃ ተደርጓል። ይህ የአየር ክልል ጥሶ ማለፍ የሚሞክር በራሪ አካል በአየር መቃወሚያ ቴክኖሎጂዎቻችን ይመታል ማለት ነው። ዘመናዊ የአየር መቃወሚያ ተገጥሞ ሁሌም ለ 24 ሰዓታት በንቃት እየተጠበቀ ነውም ተብሏል። መሳሪያው እስከ 400 ኪ.ሜ ርቀት ቅኝት የሚያደርግና በዚህ ርቀት ከበረራ የሚመጣ በራሪ አካልን detect ያደርጋል የሚል ጥቆማም ተሠጥቷል።
ቴክኖሎጂው የትኛው ይሆን?
የሀያል ጦር ባለቤት አገራት የየራሳቸው አየር መቃወሚያ አላቸው። አንድን አገር ሊያሰጋ የሚችል ጠላት የሚገኝበት ርቀት፣ ሊጠቀማቸው የሚችላቸው መሳሪያዎችና ኢላማ ውስጥ ሊያስገባቸው ይችላል የሚባሉ ቦታዎች ከአገራት የመግዛት አቅም ጋር ተዳምረው የአየር መቃወሚያ ቴክኖሎጂ ምርጫቸውን የሚወስን ነው። ይሁንና በውጤታማነታቸው በሁሉም መስፈርቶች ጫፍ ላይ የሚገኙት የራሺያው (S-300, S-400, S-500) እንዲሁም የአሜሪካው Patriot air defence systems ናቸው። ከነዚህ በተጨማሪ የቻይናው HQ-9, የእስራኤሉ Spyder, እንዲሁም ሌላኛው የራሺያ Pantsir ተጠቃሾች ናቸው። የኛ የትኛው ሊሆን ይችላል?
በመጀመሪያ ደረጃ አገራችን የራሺያውን Pantsir አየር መቃወሚያ ከራሺያ መረከባችን military watch magazine ጨምሮ የራሺያው Sputnic ራሱ በይፋ የዘገበው ነው። የእስራኤሉን Spyder ተረክበት ተከላውን ስለማጠናቀቃችንም የተለያዩ ወታደራዊ ኢንተሊጀንስ ተቋማትን ጨምሮ ፍንጮች ተሰጥተዋል። ስፓይደርን ከእስራኤል አገዙት እንደ ህንድ፣ ቬትናም ወዘተ ካሉ አገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያም ተካትታለች። ነገር ግን የግብፅ እየየ ላለመስማት እስራኤል ዝርዝር ሠረጃ አልሰጠችበትም።
የቻይናውን HQ-9 ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ አገራት የጋራ የአየር ደህንነት ቀጠና እንዲኖራቸው ለማስቻል ቻይና ታቀርብላቸው ዘንድ መስማማታቸውን ከጠቀሱ መረጃዎች ውጪ ይፋ የሆነ መረጃ የለም። ቢሆንም ቅሉ ሁሉም 400 k.m ድረስ መቃኘት አይችሉም። ስፓይደር የአጭርና መካከለኛ ቅኝት በዋናነት ወደመሬት በጣም ዝቅ ብለው የሚመጡና ረቂቅ ሰው አልባ ድሮኖችን ማምከን ነው ብቃቱ፤ ፓንትሲርም ራሱ የአጭር ርቀት ሬንጅ ያለው ሲሆን ከ s-300 ወይም 400 ካልተጣመረ ያንን ሬንጅ አይሸፍንም። የቻይናው HQ-9 ከፍተኛው ሬንጁ 150 ኪሎ ሜትር ነው። የአሜሪካው patriot ደግሞ አሁን ባለው ሁኔታ ለኢትዮጵያ የሚቀርብ አይደለም የሚለው ያስማማል። ስለሆነም እኛ የታጠቅነው የራሺያውን S-300 አድቫንስድ ቨርዥን ወይም S-400 ነው ብሎ መገመት ይቻላል።
S-300-400 ሬንጁ መቀራረቡ ብቻ አይደም የግምቱ መነሾ። የመሳሪያውን ሙሉ ክፍል መግዛት ሳያስፈልግ፣ አላስፈላጊ ወጪን በማስቀረት ቀደም ሲል ከራሷ ከተገዛው pantsir ጋር እንዲናበብና እንዲቀናጅ ማድረግ የሚያስችል መሆኑም ነው።
Pantsir
አውርፕላኖችን ፣ የጦር ጀቶችን ፣ ሄሌኮፕተር፣ ከጦር ጀቶች ላይ የሚተኮሱ ቦምቦችን፣ ሚሳየሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በፍጥነት ማውደም የሚችል የዘመነ የአየር መቃወሚያ ሲስተም መሆኑ ይታወቃል። ይሁንና በጣም ውጤታማ የሚሆነው ሰው አልባ አይሮፕላኖችና ምድር ለምድር ተምዘግዝገው የሚመጡ የጠላት መሳሪያዎችን ማውደም ላይ ነው። ሶሪያ ላይ መሳሪያው በተግባር ተፈትኗል። እነሱ ያደረጉት pantasir s 1 ሲስተሙን ውድና አሜሪካንም የሚያስፈራት ከሆነው S 400 ጋር በማጣመር ነበር። የምድር ለምድርና ድሮኖችን እንዲሁም S 400 ው የርቀት ተምዘግዛጊዎችን በማምከን ስኬታማ ሆኗል። በሶሪያ እንደተጠመደም በአንድ ሌሊት ከአሜሪካ ጦር መርከብ 127 tamhawk ሚሳይሎች ተተኩሰው 90 በመቶዎቹን አየር ላይ ማምከን አስችሏል።
S-300/400
ይህ ራሺያ ሰራሽ air defence aystem ጀት፣ ሚሳይል፣ አነስተኛና ከፍተኛ aircraft, ሰው አልባ አይሮፕላን (drone) አነፍንፎ ምንነትና ማንነቱን የሚለይ ነው። S-300 advanced ስሪቱ ልክ እንደ S-400 እስከ 400 ኪ.ሜ ድረስ የሚመጣን የጠላት በራሪ ቴክኖሎጂ ያነፈንፋል። የ S-400 advanced ስሪት ደግሞ ሬንጁ 600 ኪ.ሜ ይደርሳል። የሚሳይይሎቹ ፍጥነትም በሴኮንድ 4.8 ኪሎ ሜትር ጀምሮ እንደ ቨርዢኑ ሁኔታ እስከ 7 ኪ.ሜ በሴኮንድ የሚወነጨፍ ነው። የሚተኩሳቸው ሚሳይሎችም እስከ 400 km ይደርሳሉ። በአንድ ጊዜም እስከ 100 ኢላማዎችን detect አድርጎ እርምጃ መውሰድ ይችላል። ኢላማውን በትክክል የመምታች ብቃቱ አለማቀፍ ተፈላጊ አድርጎታል።
ቴክኖሎጂው በሚገርም ሁኔታ በቀደሙት ጊዜያት መሳሪያዎች የነበረውንና የተለያዩ ተግባራትን በተለያዩ መሳሪያዎች በተናጠል ይሠራ የነበረውን ሁሉ በአንድ platform መፈፀም የሚያስችል ሆኖ ነው የተሰራው።
ከሳተላይት ጋርም የተሳሰረ በመሆኑ አንድ አገር በዚህ S-300, s-400 በሁሉም ቦታዎች ያዘጋጀቻቸውን የሚሳይልና የጠላት መከላከያ መሳሪያ ሁሉንም በአንድ ማስተዳደር ያስችላል። በዚህም በጠላት የተላከ ጦር ጀት ወይም ሚሳይል ሲመጣ ገና በሩቁ አነፍንፎ ምንነቱን ይለይና በምን አይነት መሳሪያ መመታት እንዳለበት፣ የት ቦታ ከተጠመደ መሳሪያ ቢተኮስ ለበለጠ advantage እንደሚያበቃ፣ ከየብስ? የጦር ጄት ማስነሳት? ወዘተ ተንትኖ ምርጫውን ለጦር ሃይሉ አቅልሎ የሚያቀርብ ነው።
እዚህ ላይ፣ የመሳሪያውን አቅም አሟጦ መጠቀም(utilize) ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ልክ እንደ ስማርት ስልክ መሆኑ ነው። ባለሙያዎች መሳሪያውን በሚገባ እንዲካኑበት ማሰልጠን። ይህም ከመሳሪያው ባለቤት አገር ለሚመጡ ባለሙያዎች የሚወጣውን ወጪና ሊፈጠር የሚችል ክፍተት መዝጋት ያስችላል።
[ እዚህ የገለፅኩላችሁንና ሌሎች ያላሳፈርኳቸው አጠናካሪ የንባብ ተጋልጦየን አዋህጄ ነው ኢትዮጵያችን የራሺያውን የራዳር ቴክኖሎጂ ታጥቃልናለች ያልኩት ]
ፎቶዎች ከጎግል የተወሰዱ ናቸው!!