“ባትመርጡን ጨብጠን እናስረክባችሗለን ፤ ይህ ውሸት ነውና ኦሮሚያ የማይደፈር አስፈሪ ጭለማ ነው ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የኦሮሞ ብልፅግና 180 ወንበር አግቶ ስለምን መጨባበጥ ነው የምታወሩት ?
* .. አታደናቅፉን ብላችሗል ከምኑ ነው የማናደናቅፋችሁ ? ከአምባ ገነንነቱ፣ ከግድያው፣ ከዝርፊያው …. ሌላ ምን እየሰራችሁ ነው
* እናንተ ፍርሀትንና ጨለማን ነው የነገሳችሁብን!”
አንዷለም አራጌ ከኢዜማ
* * *
ማነው ኢትዮጵያ በዜጎች ደም የምትለመልም የብልጽግ ማሳ ናት ያላችሁ?
ክርስትያን ታደለ – አብን
* .. ብልጽግና ባይኖር ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከዚህ የከፋ ምን ሊመጣባቸው ኖሯል?
* .. አዲስቷ የመደመር ኢትዮጵያ ብላችሁ የምታቀነቅኑት እኮ እናንተው ናችሁ፤ ኢትዮጵያ የሶስት አመት እንቦቃቅላ መስላችሁ
* .. ዛሬም ድረስ በዜጎች ላይ ጅምላ ጭፍጨፋ እያደረገ ያለውን ህወሀትን አሸባሪ ለማለት የምታፍሩት የምትሽኮረመሙት እኮ እናንተው ናችሁ፤ አባት ላይ መጨከን ሆኖባችሁ እንደሆነ ይገባናል