>

አጣዬ - የአቢይ አህመድ አኪር መውደቂያ የመጨረሻዋ ካርድ (ይነጋል በላቸው)

አጣዬ – የአቢይ አህመድ አኪር መውደቂያ የመጨረሻዋ ካርድ

ይነጋል በላቸው


አሰለጡ አቢይ አህመድ በትንቢት የተነገረለት የሦስት ዓመቱ “ንጉሥ” ሊሆን እንደሚችል በተለይ ሰሞነኛ ሀገራዊ ክስተቶች አፍ አውጥተው እየተናገሩ ናቸው፡፡ ከርሱ በኋላ ኢትዮጵያ እፎይ የምትልበትና ለበርካታ ዘመናት ካነፈሯት ቁስሎች የምታገግምበት ጊዜ እንደሚመጣላት ብዙዎቻችን በጉጉት የምንጠብቀው ነው፡፡

እያንዳንዱ መንግሥትና የመንግሥቱም መዋቅር መነሻና መድረሻ ያለው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እግዜሩ እንዳማረ እንደማይገድል ደግሞ ዕውቅ ነው፡፡ “ሲያልቅ አያምር” ወይም “እንደሠራ አይገድል” የምንለውም ለዚህ ነው፡፡

መውጣት እንዳለ መውረድም አለ፡፡ ማማር እንዳለ በእርጅና ወይ በበሽታና በአደጋ ምክንያት ፉንጋና አስጠሊታ መሆንም አለ፡፡ መወለድ እንዳለ መሞትም አለ፡፡ መትከል አለ – መንቀልም አለ፡፡ መፋቀር እንዳለ መጣላትም አለ፡፡ ሁሉም ነገር የመለጣጠቅና የመከታተል ሂደት ውጤት ነው፡፡ አንዳንዱ ይፈጥናል፣ አንዳንዱ ይዘገያል፡፡  እንደተጀመረ ሳያልቅ፣ እንደተወለደ ሳያረጅ፣ እንዳማረበት ሳያስጠላ፣ እንደከበረ ሳይደኸይና እንደቆመ ሳይወድቅ የሚቀር ግን የለም፡፡ እያወራሁት የምገኘው የዲያሌክቲክስን ህግ ነው፡፡ ቁንኑና ጅንኑ አቢይም የዚህ ህግ ተገዢ ነው፡፡ እሱ ማን ሆነና!

ይሁንና ሰማይንና ምድርን በመዳፉ ሥር ያስገባና የእግዚአብሔርን መንበር የወሰደ የሚመስለው አቢቹ በዚህ ፍጥነት ውድቀቱ ይመጣል ብሎ ያሰበ ይኖታል ብሎ መገመት ይቸግራል፡፡ እኔ በበኩሌ ትንሽ ይቆያል የሚል እምነት ነበረኝ፡፡ ግን “የማያድግ ልጅ ባባቱ ብልት ይጫወታል” እንዲሉ አቢቹም ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ መነካት የሌለባቸውን የኢትዮጵያ ስስ ብልቶች በድፍረትና በዕብሪታዊ ትምክህት ደነቋቆላቸውና ከንጉሥ አዙር ዘለግ ከመለስና ከመንግሥቱ ደግሞ አጠር ባለ የንግሥና ዘመኑ የሥልጣን አኪሩ ወደቀ፤ ዕድሜ ለሰሜን ሸዋዋ አጣዬና አካባቢዋ፡፡ የሽዎች አማሮች ደም እየጮኸበት ነውና የሥልጣን ዘመኑ ከዚህም ባነሰ ቢያጥር የኢትዮጵያ አምላክ  አይፈረድበትም፡፡

አንድ አምባገነን መሪ ሊወድቅ ሲል የሚስተዋሉ ምልክቶች አሉ፡፡ መንግሥቱ የወደቀው ግንቦት … ቆይ ቆይ ለምን ከአፄ ኃይለ ሥላሤ አልጀምርም … አፄ ኃይለ ሥላሤ ውድቀታቸው የጀመረው በ1953ቱ የታኅሣስ ግርግር ሆኖ የተፋጠነው ግን በ1965ቱ የወሎ ርሀብ ነው፡፡ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በጎደሎ ቀን ሊያውም በሰይጣን ገደኛ ቁጥር ግንቦት 13/1983 ከሥልጣንም ከሀገርም ሳይሆን ከመቅረቱ በፊት ግንቦት 8 ቀን 1981 ነው ቀልቡ የተገፈፈውና የውድቀቱን ጎዳና የተያያዘው (ይቺ ግንቦት ወር መቼም ጠምሳናለች)፡፡ መለስ ዜናዊ ግንቦት ሰባት ቀን 1997 የተደረገው ሀገራዊ ምርጫ እንጥሉን ዱብ ካደረገው ወዲህ መቅኖ አጣና አንዴ አልጋ ላይ አንዴ ወንበር ላይ ሲል ቆይቶ የያዘው ደዌና የጋዜጠኛ አበበ ገላው ጩኸት ተጋግዘው ከምድር አሰናበቱት፤ እንደድምር የቡድን አገዛዝም ከሰውዬው ሞት በኋላ ወያኔ ለጥቂት ዓመታት ተንገታግታ የዛሬ ሦስት ዓመት ግድም ትህነግ/ማሌሊት ላትነሣ ወደቀች፡፡ 

አቢይ አህመድም በኖቤል ሽልማት በኩል የተዋረሰው የአጋንንት መንፈስ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በዝና እላይ አወጣውና በዕብሪት ከወጠረው በኋላ ሰሞኑን በዚሁ ሰውዬ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በሚመስል አኳኋን የሰሜን ሸዋን ህዝብ ለመጨረስ በሰጠው አመራር ሳቢያ ግብኣተ መሬቱ መቆፈር ጀመረ፡፡ ይህን እኔ አይደለሁም የምለው፡፡ ኮከቡ ነው፡፡ የአቢይ ከከብ ሦስት ዓመት ብቻ ነው የፈቀደለት፡፡ ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2013፡፡ ቁጠሩት – ልክ ሦስት ዓመት፡፡ ከዚህ በኋላ ባለው የቁልቁለት ጉዞ አንዴውን አኪሩ ወድቋልና መሳቂያ መሣለቂያ እንደሆነ ግን ልክ እንደ አባቱ አህመድ ግራኝ ብዙ ጥፋትና ውድመት እያደረሰ የተሣፈረባት የዛር ውላጅ ጀልባ ከማይቀረው ኢትዮጵያዊ መርከብ ጋር ተጋጭታ እስክትበታተን ጥቂት ጊዜ ይቆያል፡፡ የሚያስከትለው ሰብኣዊና ቁሣዊ ኪሣራ ግን አንድዬ ይሁነን እንጂ…

አሁን አቢይ አፍ የለውም፡፡ ኩክኒው የተራገፈበት ዶሮ መስሏል፡፡ በሚያስተዳድራት ሀገር አምስት ከተማ በእሳት እየነደደና ራሱ አደራጅቶና ዘመናዊ ትጥቅ አስታጥቆ በላካቸው መንግሥታዊ ሽፍቶች ሕዝብ እያለቀ አጅሬ እንደዱሮው አኪሩ ያልወደቀ መስሎት ለቃሉ አጠቃቀሜ ይቅርታ ይደረግልኝና አለባበሱን አሳምሮና የፊት ማዲያቱን  እንደሸርሙጣ ኳኩሎ ህንጻ ያመስርቃል፤ በየክፍለ ከተማውም ለመንገድ ውበትና ለአትክልት ተከላ በሚል አስፋልትና ክፍት ቦታዎችን ያስቆፍራል – አንገብጋቢው ችግራችን የመንገድ ውበትና አበባ ይመስል፡፡ ቀደም ባለ ዘመን በኢጣሊያ እንዲህ ሆነ፡፡ በአንድ ሰፈር ውስጥ ሕጻናት ሲጫወቱ አንደኛው ሕጻን 36 ሜትር በሚጠልቅ የደረቀ የውኃ ጉድጓድ ውስጥ ይገባል፡፡ ልጁን ከዚያ ጉድጓድ ለማውጣት ዘዴ ጠፍቶ መንደርተኛው ሁሉ ይጨነቃል፡፡ አንዱ አካፋ፣ ሌላው ዶማ፣ አንዱ ድጅኖ ሌላው ባሬላ … እየያዘ ሁሉም በቻለው ሲማስን ከነዚያ አካፋና ዶማ ይዘው ነጭ ላብ ከሚዘፍቃቸው ሰዎች መካከል አንዱ በወሬ ወሬ ሰምቶ የመጣው የሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ነበር፡፡ የኛው ጉድ ግን በመተከልና በሸዋ በርካታ ከተሞች ከነነዋሪዎቻቸውና የዘመናት ጥሪታቸው በመትረየስና በእሳት ነዲድ እየጋዩ ምንም ሳይመስለው ዓለሙን ይቀጫል፡፡ የዚህ ሰው ተፈጥሮ ቢመረመር ልዩ ሥነ ሕይወታዊ (ባዮሎጂካል) ንጥረ ነገሮች ሳይኖሩት አይቀርም፡፡ ሟቾች አማሮች በመሆናቸው ምንም ላይሰማው ይችል ይሆናል፤ የግድያው መሃንዲስ እርሱ በመሆኑ በውስጡ ሊደሰትና በድል አድራጊነት ስሜት ሊኮፈስ ይችላል፡፡ ነገር ግን ለታይታውም ቢሆን፣ ለሟች ወገኖች ሞራል ሲባልም ቢሆን፣ የፌዴራል ተብዬው ዋና መሪ ከመሆኑ አንጻርም ቢሆን የተለመደ የማስመሰያ ወይም የሽንገላ ቃላትን ቢወረውር ቢያንስ የሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር መሆኑንና እየሆነ ባለው ነገር ማዘኑን ለየዋሃን ታዛቢዎች መጠቆም በቻለ ነበር – ይህን ዕድል በትዕቢቱ ሳይጠቀምበት መቅረቱ ራሱን እንደሚጎዳው ካለፈ በኋላም ቢሆን ይገነዘባል ብዬ አሰባለሁ፡፡ የአክራሪ ወንድሞቹን ስሜት ጠበቅሁ ብሎ የተጎጂዎችን ስሜት ደጋግሞ ወጋው፤ የሰውዬውም ኃጢኣት ከፊተኛው የኋለኛው ባሰ፡፡ በነገራችን ላይ ቅንጣት ባለማዘኑና በዝምታም በማለፉ ምክንያት ነው የድርጊቱ ዋና ተዋናይ እሱና የቅርብ ሰዎቹ እንደሆኑ ሁላችንም ይልጥ ልንገነዘብ የቻልነው፤ ዶሮ የሞተበትም አልመሰለው፡፡ እንዴ፣ ውሻና ድመት ሲሞትብን እንኳን እኮ እናዝናለን፡፡ የዚህ ሰውዬ አንጀት ግን በርግጥም የተለዬ ነው፤ መጥኔ ለቤተሰቡ!!

ጊዜው ብዙ የመሥሪያ እንጂ ብዙ የመናገሪያ አይደለም፡፡ ለማንኛውም ጸሎትና ምህላ ይደረግ፡፡ የኢትዮጵያ ችግር መንስኤው ሰው ይሁን እንጂ መፍትሔው በአብዛኛው ከእግዚአብሔር ነው፡፡ ፈተናችን ቢበዛም ማለፉ አይቀርም፡፡

በተለይ በከተሞች አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ ከሚበላውም ከሚጠጣውም ትንሽ ትንሽ መያዝ ጥሩ ነው፡፡ በተለይ ሕጻናትና ህሙማን ያሉባቸው ቤቶች የሚበላና የሚጠጣ ነገር አቅም በፈቀደ ቤት ባዶ እንዳይሆን ቢደረግ ክፋት የለውም፡፡ አማሮች በምትኖሩባቸው አካባቢዎች ጥንቃቄ አድርጉ፡፡ ቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ጠንቀኛ እንደሆኑ የጎሉ ምልክቶች እየታዩ ነውና ራስን ለመጠበቅ መመካከር፣ መነጋገርና በቂ ዝግጅት አድርጎ ከዚህች ከምትመጣዋ ጎርፍ ለመዳን መሞከር ዘርን የመተካት ያህል ነው፡፡ ብትችሉ ብትችሉ አማራና ትግሬዎች ታረቁ፤ አትደንቁሩ፡፡ ብልኅ ኦሮሞዎችም ከትግራይ ተማሩ፤ ከትግሬዎችም ልምድ ቅሰሙ፡፡ የሚታይ ሁሉ እውነት አይደለም፤ የተጨበጠ ሁሉ የራስ አይደለም፤ትናንትን ከዛሬና ዛሬን ከነገ በማገናዘብ ጤናማ አስተሳሰብ መፍጠር በየትኛውም ዘመን ከማንም ጋር አብሮ ያኗኑራልና ከሞቅታ ወጥቶ በምክንያታዊ የጋራ አስተሳሰብ መመራት አዋጭ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ በትህነግ ምን እንደተጠቀመ ማሰብ ነው፤ ኦሮሞም በኦነግም ሆነ በኦህዲድ ከወንድሞቹ ይለይ እንደሆነ እንጂ ተጨባጭ ጥቅም እንደማያገኝ የታመነ ነው፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ የዘውጉ አባላት የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም በሥልጣንም ሆነ በሀብት አይከብሩም ማለት አይደለም፤ ይህን እየታዘብን ነው ግን ዘላቂ አይደለም፡፡ ዛሬ የሚያግበሰብስ ሁሉ ነገ የት ልጣለው የሚልበት ጊዜ ይመጣል፡፡ የ“ዛሬ”ን አጥበርባሪነት ከትናንት የማይማር በ“ነገ” ሕይወቱ የፈረደ ብቻ ነው፡፡ አባይ ፀሐዬንና አቦይ ስብሃትን ያዬ …፡፡ ዳግመኛ በእሳት ላለመጫወት በግድ እጅን እሳት ውስጥ መክተት አይጠበቅብንም  – አበራሽን ውለታቢስ ማድረግ ካልፈለግን በስተቀር፡፡ ስለዚህ የማሰብና የማሰላሰል ኃይላችንን እንጠቀምበት፡፡

ነፍስ ይማር አቢይ አህመድ፡፡ “የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ሉካንዳ ቤት አጠገብ ሲልከሰከስ ታዬ” አሉ፡፡ “ወጣ ወጣና እንደሸንበቆ ተንከባለለ እንደሙቀጫ”ም አሉ – ሰሚ ጠፋ እንጂ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ይህን የጭቃ እሾህ አ.አ.አ መደገፌ አሁን ይቆጨኛል፡፡ በሱም ምክንያት ከጥቂት ጓደኞቼ ጋር መቃረኔ ይጸጽተኛል፡፡ ቢሆንም በምላስ ተቀምሶ ምንነቱ እንዳይታወቅ ሰው ጨው አይደለምና እኔም ሆንኩ የኔ ቢጤ ተጸጻቾች ብዙም አይቆጨን፡፡ ያለ ነው፡፡ “ሳንተዋወቅ ተጋባን፤ ስንተዋወቅ ተፋታን” የሚለውን የአራዶች ብሂል ማስታወስም ለመጽናናት ጠቃሚ ነው፡፡ ሻሎም፡፡ 

Filed in: Amharic