>

"አጣዬ ከተማን ጭራሽ የማያውቋት ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ታጣቂዎችን ማርከናል...!!! (አቶ ደምስ ደበበ - የአጣዬ ከተማ ከንቲባ)

“አጣዬ ከተማን ጭራሽ የማያውቋት ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ታጣቂዎችን ማርከናል…!!!
አቶ ደምስ ደበበ – የአጣዬ ከተማ ከንቲባ

 

“የአጣዬውን የሰላማዊ ሰዎች ፍጅት ከመሩት የኦሮሞ ልዩ ዞን አመራሮች ውስጥ ቢያንስ ከሃላፊነቱ የተነሳ አመራር አለመኖሩ እጅግ ያሳዝናል” –
ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ
 
አብይ አህመድ እንዳይሰደብ ከፈለገ ስራውን በአግባቡ ነው መስራት ያለበት። ከዚያ ውጭ አማራን በማቄም ለውጥ አመጣለሁ ማለት ግን ዘበት ነው። ቢያንስ ቢያንስ መንግስት መር የሆነው የአማራ ሞት መቆም አለበት።
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን አመራሮች ከሃላፊነታቸው አልተነሱም። የአጣዬን ጦርነት የመሩት ግን እነዚህ አመራሮች ናቸው። ተሽከርካሪ በማቅረብ፣ ከኦሮሞ ብልፅግና አመራሮች ጋር በመምክርም ሙሉ ከተማ አውድመዋል። የጠየቃቸው አካል ግን የለም። ይሄ የሚያሳየው የአማራ ክልል አመራሮች አቅመ-ቢስ መሆናቸውን ነው።
*… የገደሉን በመንግስት መኪና ተጭነው የመጡ ተስፋፊዎች ናቸው”
የአጣዬ ከተማ ሙሉ በሙሉ በወራሪዎች ተቃጥሏል። የግለሰቦች ይዞታ እንኳን በአዲስ ልኬታ ካልሆነ አይታወቅም። የፀጥታ ሁኔታው ከተስተካከለ አዲስ ከተማ ነው የምንገነባው።
ታጣቂዎቹ በመንግስት መኪና እና በአምቡላንስ ከሌላ አካባቢ ነው የመጡት። አካባቢውን በሚገባ አያውቁትም። አጣዬ ከተማን እንኳን በአካል በስም እንኳን የማያውቋት ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ታጣቂዎች ማርከናል። እነዚህን ተስፋፊዎች መንገድ እየመሩ ያመጧቸው ግን የምናውቃቸው የጎረቤት ዞን ሰዎች ናቸው። የኦሮሞ ልዩ ዞን አመራሮችም እጃቸው አለበት።
ከሞት የተረፈው ነዋሪም በየትምህርት ቤቱ ተጠልሎ ነው የሚገኘው። መንግስት በቂ ጉርስና ልብስ እያቀረበልን አይደለም። በአለም ዙርያ ያለ የአማራ ህዝብና ወዳጆች አለንላችሁ ልትሉን ይገባል።
Filed in: Amharic