>
7:02 am - Friday March 31, 2023

"መጤና ሰፋሪ"  ከተባለው ወገን በቀጣዩ ምርጫ ተብዬ ኢዜማን የሚመርጥ  ቢኖር  ሙሉ በሙሉ የተሸጠና ባንዳ ነው...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

 “መጤና ሰፋሪ”  ከተባለው ወገን በቀጣዩ ምርጫ ተብዬ ኢዜማን የሚመርጥ  ቢኖር  ሙሉ በሙሉ የተሸጠና ባንዳ ነው…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

የኢሕአፓው አስኳድ፣ የጉራጌ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር  የበላይ ጠባቂ፣ የቀስተ ደመናው አምበል፣ የቅንጅቱ ፊታውራሪው፣ የግንቦት ሰባቱ ሊቀመንበር፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ጠቅላይ አዛዥ፣ የአገር አድን ንቅናቄው ሰብሳቢና የኢዜማ መሪው ብርሀኑ ነጋ ኦሮሞ ኢትዮጵያን ከመውረሩ እልፍ አእላፍ ዘመናት በፊት አማራ ባለ ርስት ሆኖ ለኖረበት፣ አማርኛ ተወልዶ ላደገበትና ካለፉት 30 ዓመታት ወዲህ ግን ኦሮምያ እየተባለ ለሚጠራው ምድር መጤና ሰፋሪ ማለቱን ተከትሎ በቀጣዩ ምርጫ ተብዮ ኢዜማን የሚመርጥ አማራ ቢኖር  ሙሉ በሙሉ የተሸጠና ባንዳ እንደሆነ በሰጠሁት አስተያየት የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች ተቆጥተዋል። የእነዚህ ሰዎች ቁጣ አማራ የሆነ ሁሉ ኢዜማን ሊመርጠው አይገባም በመባሉ እንጂ ብርሀኑ ነጋ ኦሮሞ ኢትዮጵያን ከመውረሩ እልፍ አእላፍ ዘመናት በፊት አማራ ባለ ርስት ሆኖ ለኖረበትና አማርኛ ተወልዶ ላደገበት ምድር መጤና ሰፋሪ በመባሉ አይደለም። የእነዚህ ሰዎች ውግንና አማራን ጠላት ላደረጉ አካላት ሳይሆን የአማራ ሕዝብ ባለ ጉዳይ ቢሆኑ ኖሮ ቁጣቸው እንደ ኦነጋውያንና ወያኔዎች ሁሉ አማራን እልፍ አእላፍ ለኖረበት አጽመ ርስቱ መጤና ሰፋሪ አድርጎ አገር አልባ ባደረገው በኢዜማው መሪ በቄስ ሞገሴ ላይ እንጂ ዛሬ ኦሮምያ የሚባለው ክልል ኦሮሞ ኢትዮጵያን ከመውረሩ እልፍ አእላፍ ዘመናት በፊት አማራ ባለ ርስት ሆኖ የኖረበትና አማርኛ ተወልዶ ያደገበት ምድር መሆኑን በማውሳት ይህን የታሪክ እውነት ክዶ  አማራን አገር አልባ ያደረገውን ኢዜማን አትምረጡ ባልሁት በኔ ላይ መሆን አልነበረበትም።

Filed in: Amharic