>

ወልቃይት የአማራ የግፍ ጥግ ማሳያ ...!!! (መአዛ መሀመድ እና ብርሀኑ ተክለአረጋይ)

ወልቃይት የአማራ የግፍ ጥግ ማሳያ …!!!

መአዛ መሀመድ

ወልቃይት የግፍ መጋዘን …!!!

ብርሀኑ ተክለአረጋይ
ወልቃይት የ”ጥርስን ነክሶ ትግል” መገለጫ…!!!

 በወልቃይት  ዘመናቸውን ሙሉ በግፍ እና በጭቆና  ጫንቃቸው የጎበጠ  አይናቸው እያየ ልጆቻቸው የታረዱባቸው እናቶች የባሎቻቸውን የተቆራረጠ አካል የቀበሩ ሚስቶች የአባታቸው ሰውነት ሲበለት የተመለከቱ ህፃናትን መስማት እንዴት ያማል
መስማት ብቻም ሳይሆን በአይን የሚታዩ የግፍ ቅሪቶችን መመልከት ከአእምሮ በላይ የሆነ ስብራት ነው። በአንድ ጉድጓድ ከ40-50 ንፁሐን በተቀበሩበት በማይካድራ የጅምላ መቃብር መቆም ዘመንን ሙሉ የማይረሳ ስቃይ ያሸክማል። ስለራሳቸው ልጆች ብቻ ሳይሆን ስለማያውቋቸው በግፍ ስለተገደሉ ቀን ሰራተኞች ጭምር በየቀኑ አመሻሽ ላይ በመቃብር ስፍራው እየተገኙ “እናቶቻችሁ ምን ይሉ ይሆን” እያሉ ስለሚያለቅሱ እናቶች መስማት ደግሞ ከአዕምሮ በላይ ነው።
በህመም ላይ ሳሉ አልጋቸው ላይ የታረዱ፣ ልጆቻቸው ፊት የተቆራረጡ፣ በህይወት እያሉ እሳት የተለቀቀባቸው፣ አጥንታቸው ተለቃቅሞ የተቀበሩባት ምድር ማይካድራን በሀዘን ተሰናበትናት።
ይህ ሁሉ ግፍ ከጥቂት ቀናት ፕሮፖጋንዳ ውጪ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ ሚዲያዎች ሊናገሩት ያልደፈሩና ይልቁኑ ሆን ብለው የሸፈኑት እውነት መሆኑ ከልብ ያስቆጫል፤ያንገበግባል፤ያስተዛዝባልም፤ እሳትን በልብስ ውስጥ ሸሽጎ መኖር ይቻላል?
ወልቃይት የግፍ መጋዘን …!!!
 
ወልቃይት የ”ጥርስን ነክሶ ትግል” መገለጫ…!!!
 
በጥቂት ቀናት የወልቃይት ቆይታችን ብዙ ነገር ታዝበናል። በዚህ መካነ ስቃይ ዘመናቸውን ሙሉ በግፍ ሰንሰለት ተይዘው ጫንቃቸው የጎበጠ፣ልጆቻቸው በወጡበት የቀሩባቸው፣ባሎቻቸው አይናቸው እያየ የተገደሉባቸው፣ሲናገሩ ከእምባ የሚጀምሩ እናቶችን ማየት እጅግ እጅግ ያሳቅቃል።
መስማት ብቻም ሳይሆን በአይን የሚታዩ የግፍ ቅሪቶችን መመልከት ከአእምሮ በላይ የሆነ ስብራት ነው። በአንድ ጉድጓድ ከ40-50 ንፁሐን በተቀበሩበት በማይካድራ የጅምላ መቃብር መቆም ዘመንን ሙሉ የማይረሳ ስቃይ ያሸክማል። ስለራሳቸው ልጆች ብቻ ሳይሆን ስለማያውቋቸው በግፍ ስለተገደሉ ቀን ሰራተኞች ጭምር በየቀኑ አመሻሽ ላይ በመቃብር ስፍራው እየተገኙ “እናቶቻችሁ ምን ይሉ ይሆን” እያሉ ስለሚያለቅሱ እናቶች መስማት ደግሞ ከህሊና በላይ ነው።
በህመም ላይ ሳሉ አልጋቸው ላይ የታረዱ፣ ልጆቻቸው ፊት የተቆራረጡ፣ በህይወት እያሉ እሳት የተለቀቀባቸው፣ አጥንታቸው ተለቃቅሞ የተቀበሩባት ምድር ማይካድራን በሀዘን ተሰናበትናት።
ይህ ሁሉ ግፍ ከጥቂት ቀናት ፕሮፖጋንዳ ውጪ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ ሚዲያዎች ሊናገሩት ያልደፈሩና ይልቁኑ ሆን ብለው የሸፈኑት እውነት መሆኑ ከልብ ያስቆጫል፤ያንገበግባል፤ያስተዛዝባልም፤ እሳትን በልብስ ውስጥ ሸሽጎ መኖር ይቻላል?
ዝርዝሩ ይቆየን!!!
ከሁሉ በላይ እንቅልፍ አጥተው ከስቃዩ ጋር እየታገሉ ዞኑን ሰላም ለማድረግ የሚታትሩ የዞኑ አመራሮችንና የፀጥታ ኃይሎችን ማየትና ከነክፍተቱ ወልቃይት ከስቃይ የተመለሰች ሰላማዊት ምድር መሆኗን መመልከት ተስፋን ያጭራል።
ሰላም ዋጋዋ ውድ ነው!!
 
ዝርዝሩን በ Abbay Media
Filed in: Amharic