>
5:21 pm - Tuesday July 20, 3706

ጋዜጠኛ ተምሰገን ደሳለኝ በቅዳሜው ዕትም ፍትህ ጋዜጣው ላይ ስለ Jawar_Mohammed ተፅፎ ለገበያ ከቀረበው ላይ ቀንጨብ አድርጌ ላካፍላቹ!!" 

ጃዋርን አለማድነቅ ይቻላል፤ ጃዋርን መናቅም አይከለከልም ግን ያስገምታል…!!!
ጋዜጠኛ ተምሰገን ደሳለኝ በቅዳሜው ዕትም ፍትህ ጋዜጣው ላይ ስለ Jawar_Mohammed ተፅፎ ለገበያ ከቀረበው ላይ ቀንጨብ አድርጌ ላካፍላቹ!!” 

Mee Zaan


ጃዋርን የሚንቅ ሰው ይገርመኛል። ጃዋርን አለማድነቅ ይቻላል፤ ጃዋርን መናቅም አይከለከልም ግን ያስገምታል። ጃዋር ተራ ፖለቲከኛ አይደለም። የህወሓትን ሰንሰለት በጣጥሰው ለራሱ እግረሙቅ ከዳረጉት ቁልፍ ሰዎች ተርታ ይመደባል (በእርግጥ ህወሓት በራሱ ብስባሽ ተውጦ ማለቁ እንዳለ ሆኖ፤ አስከሬን ለማስወገድም ቢሆንም አቅም ይፈልጋል) ።
ተለዋዋጭ፤ ጎበዝ ተናጋሪ፤ አይገመቴ፤ የኢትዮጵያን የሚዲያም ሆነ የፌድራሊዝም ሃቲት ከሚያሾሩ ሶስት ዋና ዋና ቋንቋዎች ውስጥ ሶስቱንም ይችላል። አማርኛን ከአዴፓ ሰዎች አስበልጦ የሚያጣጥፍ፤ ኦሮሚኛን ከኦዴፓዎች በላይ የሚያራቅቅ፤ በእንግሊዝኛውም ከእነታምራት ወልደጊዮርጊስ ትንሽ አነስ የሚል ‘ልሳነ-ብዙ’ ነው። በእድሜም ቢሆን እነ በቀለ ገርባ ቢያምጡ የሚያደርሱት ወጣት ነው።
አንብቦ ለማደርም የማይሰንፍ፤ ዝናረ ሙሉ ወጣት ነው። “ማን ጋ እና የት ተማርክ?” ቢባልም፤ “ከሲንጋፖር እስከ ስታንፈርድ” ብሎ ቀልብ መግዛት የማይሳነው ፊት አውራሪ ነው። ከቀኃሱ የእነ መረራ ጉዲና ፕሮፌሰርሺፕ ይልቅ፤ የጃዋር አንደር ግራጁዌት ብዙዎችን ታስጎመዣለች። ለኪሱ ሩቅ ያልሆነ ቸር ብጤ እንደሆነም እነ ታምራት ነገራ አጫውተውናል (በእርግጥ በታምራት ነገራ እና በአባባ ታምራት መካከል ያለውን ልዩነት መግለጽ ከሚያዳግታቸው መካከል አንዱ ብሆንም፤ ይሄንን ግን አምኜዋለሁ።
መቻቻልን በመስበክም ሙስጠፌን አንደሚቀድመው በማስረጃ ልሞግት ዝግጁ ነኝ። ተሳስቆ እና ተተራርቦ ለማደርም ያን ያህል የማይሰንፍ፤ ከትልቅ ከትንሹ ጋር ሻይ ቡና መባባል የማይቸግረው ጮሌ ብጤ መሆኑን ከታማኝ ምንጮቼ ሰምቻለሁ (የተመስገን ደሳለኝን ታማኝ ምንጮች ብቻ ነው እንዴ የምታምኑት? አንዳንዴ ለእኛም ጊዜ ስጡን እንጂ ቂቂቂ!! )
ጮሌ ነው ብዬሃለሁ! በጮሌ ወረዳ ውስጥም ከሌንጮ ለታ በላይ ዝና አያጣም። የገጠሩን አፈርም ድሙጋን ጠርቶ ይወክላል። ለአየሩ የሚሆን ከበቂ በላይ ስንቅ የያዘ ፖለቲከኛ ነው።
በጥቅሉ፤ የልጁ ብራንድ ባናና ሪፑብሊክ ነው። የባነነ!!!!
ምን ጻፈና? ምን አሳተመና? ምን ተመራመረና? ብለው “ተመራማሪነቱን” ለማጠየቅ ለሚደክሙትም፤ ከ10 አመታት በፊት OPride ላይ የጻፋቸውን፤ በማጣቀሻ የዳበሩ ከኢኮኖሚክስ እስከከ ሶሺዮ ፖለቲኪስ የሚጠቃቅሱ አርቲክሎችን እጋብዘዋለሁ። እያዳሜ የናይልን ፖለቲካ ከናይል ፐርች በማትለይበት ዘመን፤ Ethiopia’s Internal Cohesion Key to Advancing Interest in the Nile የሚል ጽሁፉን በ24ዓመቱ ያስነበበ ጭንቄያም ነው። Why Oromos should care about the Nile Politics ሲል ለራሱ ጽሁፍ የሰጠውን የመልስ ምትም ተጋበዝ። ሌላውንም አስኪበቃህ ደርድሮልሃል። ከአሲምባ እስከ ሲምባ ፖለቲክስ ከ24አመት ልጅ በማይጠበቅ ብዕር አስኮምኩሞናል።
Filed in: Amharic