>

በየአውደ ግምባሮቹ ጦርነቱ ሲጋጋል ድል ሲቃረብ ፤ "ውጊያ አቁሙ፤ አፈግፍጉ..." የሚለው ማን ነው? ለምን?  (እንግዳ ታደሰ)

ሁሌም በየአውደ ግምባሮቹ ጦርነቱ ሲጋጋል ድል ሲቃረብ ፤ “ውጊያ አቁሙ፤ አፈግፍጉ…” የሚለው ማን ነው? ለምን? 
እንግዳ ታደሰ

*….. አየህ! ዴሜንሽያ የሚሉት የመጃጀት በሽታ ካልተጫነኽ በቀር ወያኔ’ ያኔ ወደ አዲስ አበባ ስትመጣ ጎንደርን ስትሻገር ቴዎድሮስ የመከላከያ ጦር፥ ጎጃምን ስትዘልቅ ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ፥ ወሎ ስትገባ ዋለልኝ ብርጌድ እያለች እንደነበር አስታውስ። አፋሮችን’ እንዴት ሊያሞኙ እንደፈለጉ ያዝልኝ። ይህ የአገዛዝ ጥበብ ነው። በመንግሥትነት ወደ ሰላሳ ዓመት ግድም ስለኖሩ ማጃጃሉን ተክነውበታል።
የዐብይ ደጋፊ’ ካድሬዎች ለጭብጦ ምስራቸው ሲሉ ውነቱን እያዛቡ በሚጽፉበት ወቅት፥ ሀገሪቱም በህወሃት ጠላቶች እጅ በምትታመስበት ሰዓት’ እውነተኛ መረጃዎችን አውጥቶ መጻፉ አገሪቱን ለአደጋ ያጋልጣል በሚል ዝምታን’ የመረጡ ነገር ግን እውነተኛ መረጃ ያላቸው ወገኖች በሁኔታዎች ግራ’ በመጋባት What
Is going on እያሉ ነው።
ካድሬ ሆይ! ወደድክም ጠላህም ይህ የከተብኩልህ ጽሁፍ ከፈረሱ አፍ’  የተገኘ ነው። ከፈለግህ ተቀብለህ እንደ ግብአት ወስደኽው የሃገሪቱን ደካማ አሠራር አርቅበት።በተረፈ ለጭብጦው ምስርህ ስትል ባዶ ፕሮፓጋንዳ እየነዛህ ጠላቶቻችን እንደ ጤዛ’ ይረግፋሉ እያልክ  ስትሞነጫጭር አትዋል። ህዝብህን ግን አታዘናጋ! #በፉፋ_ቱሻ ዝም ብለኽ አትቀላምድ።
ትላንት ሠመራ ላይ ከስር ከፎቶው ላይ የምታያቸው ከፍተኛ የሀገሪቱ የጦር መሪዎችና የደህንነት ሹሞች ከአፋር ክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አወል ሀርባ ጋር’ ሲመክሩ ውለዋል። በዚያ መሃል ከህወሃት ጋር’ ከፍተኛ ውጊያ ላይ የነበረው የሪፓብሊካን አርሚ ጦርነቱን አቁሞ እንዲያፈገፍግ ተደርጓል። ለምን? ማን አዘዘው?
ሁሌም በየ አውደ ግምባሮቹ ጦርነቱ ሲጋጋል ድል ሲቃረብ ፤ “ውጊያ አቁሙ፤ አፈግፍጉ…” የሚለው ማን ነው? ለምን?
የብልጽግና አፋሮችን ጭምር ግራ’ ያጋባ ጉዳይ ነው። ዞን አራት’ ተብሎ በሚጠራው አማራን፥ትግራይን፥እና አፋርን ከሚያገናኘው ስፍራ ላይ ነው ወያኔዎች ውጊያ ያካሄዱት። ሪፓብሊካን ጦሩ ተኩስ ሲያቆም ግን’ ተመልሰው አንዳንድ ቦታዎችን የያዙት የህወት ጦር ተዋጊዎች፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አውርደው #የአፋሩን ሳይነኩ  አገኘን ባሉት ድል እንኳ የህወሃትን ባንዲራ’ ሳይሰቅሉ ነው ያሉት።
አየህ! ዴሜንሽያ የሚሉት የመጃጀት በሽታ ካልተጫነኽ በቀር ወያኔ’ ያኔ ወደ አዲስ አበባ ስትመጣ ጎንደርን ስትሻገር #ቴዎድሮስ የመከላከያ ጦር፥ ጎጃምን ስትዘልቅ ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ፥#ወሎ ስትገባ ዋለልኝ ብርጌድ እያለች እንደነበር አስታውስ። አፋሮችን’ እንዴት ሊያሞኙ እንደፈለጉ ያዝልኝ። ይህ የአገዛዝ ጥበብ ነው። በመንግሥትነት ወደ ሰላሳ ዓመት ግድም ስለኖሩ ማጃጃሉን ተክነውበታል።
ጽህፉ በዝቱኣል ግን ከትክክለኛው የመረጃ አፍ የተገኘ መረጃ ስለሆነ እንደ #እንቆቆ እየመረመረጃ  ቢሆን ካድሬ ሆይ ተጋተው።#አፋር’ በራሱ መሳርያ ነበር ወያኔዎችን ከሪፓብሊካን ጦር ጋር በጋራ በመቆም እየተጋተራቸው የነበረው። ጠላት ደስ አይበለው እንጂ’ ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎበታል።
በዛሬው ቀን’ የተሻለ መሳርያ ይታደላችኋል ተብለው ከተጠሩ በኋላ የአፋር ሚልሽያዎች’ ለታማኞች ብቻ ነው የምናድለው ብለው ብዙዎቹን መልሰዋቸዋል። ግን ለምን? አፋሮች What is going on? እያሉ ነው! ይህ ከራሳቸው አፋሮች የተገኘ መረጃ ነው ጀባ’ ያልኩህ።ራሳቸው የአፋር ብልጽግና ሰዎች ጭምር ለምን እያሉ ነው። ካድሬዎች እንደማያስደስታችሁ ባውቅም’ ከፋዮቻችሁን ግን ለምን ብላችሁ ጠይቋቸው እስቲ ።
Filed in: Amharic