ጎዳና ያእቆብ – አባይነህ ካሴ
የኢትዮጵያን ታላቅነት ካላወቅህ እነዚህን ጠይቅ:-
± ሊቀ ነቢያት ሙሴን ጠይቀው ከእነ መልክአ ምድሯ ይነግርሃል።
+ ነቢዩ ኤርሚያስን ጠይቀው ከእነ መልኳ ያስረዳሃል።
+ ቅዱስ ዳዊትን ጠይቅ ክንዷን ያሳይሃል።
+ ጠቢቡ ሰሎሞንን ጠይቅ በፍቅሯ መውደቁን ይገልጥልሃል።
+ ሐኪሙን ሐዋርያ ሉቃስን ጠይቀው መጽሐፏን ያስነብብሃል።
+ ከቻልህ ከቻልህ እንዲያው ከኾነልህ ጌታችንን ጠይቅ እምነቷን ያጸድቅልሃል።
+ እነዚህ ከራቁብህ መድረስም ከተሳነህ ሆሜርን ጠይቀው በደንብ ያስረዳሃል። ፑሽኪንን ጠይቀው ቆጥሮ ይነግርሃል።
+ መሐመድንም ጠይቅ አትንኳት ይልሃል።
ታናሽ የኾንህ ጊዜ ይህ ሁሉ ይከደንብሃል።
ወልዳ ባሳደገች: በድህነቷ ባስተማረችና ከውጭ ጠላት ይታደጉኛል ብላ እናንተን እንደ ስለት ልጅ ተንከባክባ ባሳደገች የልጅ ጠላት የሆናችሁባት የናት ጡት ነካሾች እግዚአብሔር የስራችሁን ይስጣችሁ::
በየትኛውም አለም በታሪካችን አለም አክብሮ አንገታችንን ቀናና ደረታችንን ነፍተን አድርገን እንድንሄድ ባደረገች አንገቷን ልታስትደፏት በከንቱ ትደክማላችሁ:: አንድ አባት እንዳሉትም ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣልችሁ!!
ታላቅ ያረጉኛል ስትል ተግታችሁ ልታሳንሷትሞከራችሁ:: በመልካችሁ እንደምሳሌአችሁ ወልዳችሁ ሀገር ጠል: ታሪክ ጥል ትውልድ አሳደጋችሁ::
እነ ጌታቸው ረዳ: እነ አብይ አህመድ: ታዬ ደንደአ የእጅ ስራችሁ ናቸውና ደስ ይበላችሁ:: በፍሬአችሁ ሀሴትም አድርጉ::
ትውልዱን ሀገር አልባ ያደረጋችሁት ሳያንስ አኩሪ ታሪኩንና ድንቅ ትዝታውን ልትወስዱበት የምትዳክሩ ደካሞች ሁላ ደስ ይበላችሁ:: የታሪክ አተላዎች እናም ትንሾች ስለሆናችሁ ታላቋን ሀገር አንሳችሁ ለማሳነስ ዛሬም ታጥቃችሁ ተነስታችኃል::
ኢህአዴግ መቼም አይለወጥምና ጌታቸው ረዳ ንግግር ጮቤ የምትረግጡ ሱሌማን ደደፎዎች ታዬ ደንደአዎችና ሽመልስ አብዲሳዎች እውነት ፈጣሪ ታሪክ አልባ ያድርጋችሁ!!
የወላድ መካን ያድርጋችሁ!!
እጃችሁን አመድ አፋሽ ያድርገው!!!
ሀገር ስትሰድቡ እናት ስታዋርዱ የማይሸክካችሁ ሁሉ ዘመናችሁ የስድብና የውርደት ይሁን!!!
ፈጣሪ ይፍረድባችሁ እናንተ የእፉኝት ልጆች!!!!
ይብላኝ ለእናንተ ዝናብ ለሌለው ዳመናዎችና ለልጆቻችሁ እንጂ ኢትዮጵያ እንደው ወደ ቀደመው ታላቅነቷ መመለሷ አይቀርም:: ኃይሏን ማደሷ አይቀርም::
ምኞቴ ያን ቀን ሳታዩና ቆሽታችሁ ሳያር እንዳትሞቱ ብቻ ነው::
እውነት ፈጣሪ የምለምነው እና ቢሰማኝ ደስ የምሰኝበት ሁለት ነገር ቢኖር ሀገሬን ወደቀደመ ክብሯ እንዲመልስና እናንተን ተመልካች እንዲያደርግ ብቻ ነው!!
መቼም በቀል የተቀላቀለው ፀሎት አይሰማም ግን እውነት ይህንን ብቻ እሺ ይበለኝና ኢህአዴግን የወለደን አስተሳሰብ ከነ ግብረአበሮቻቸው ፈጣሪ ፍትህ ሳይሆን የበቀል ዱላ ያሳርፋቸው!! ፈጣሪ ሁላችሁንም ከስራችሁ ይንቀላችሁ!! የተረሳችሁ ያድርጋችሁ!!!
አፈር አትቅለላቸው!!
ነብሳቸው እረፍት አታግኝ!!!