>
5:18 pm - Sunday June 15, 1406

 የኪነጥበብ ባለሙያዎች አስፈላጊ ከሆነ ግንባር ድረስ ለመዝመት ዝግጁ  ነን...!!! ” ( አርቲስት ደበበ እሸቱ)

 የኪነጥበብ ባለሙያዎች አስፈላጊ ከሆነ ግንባር ድረስ ለመዝመት ዝግጁ  ነን…!!! ” –
አርቲስት ደበበ እሸቱ
(ኢ ፕ ድ)

የኪነጥበብ ባለሙያዎች በሙያቸው ከሠራዊቱ ጎን መሆናቸውንና አስፈላጊም ከሆነም ግንባር ድረስ ለመዝመት ዕድሜ ፣ጾታ፣ ሃይማኖት እና የፖለቲካ አመለካከት ሳይገድባቸው ዝግጁ መሆናቸውን አርቲስት ደበበ እሸቱ አስታወቀ።
“ሀገር ተደፈረች ሲባል እኛ ነን የተደፈርነው፤ እኛ ነን የተጎዳነው” ማንም ኢትዮጵያዊ ከዚህ ሊያፈገፍግ አይችልም ብሏል።
የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አጋርነታቸውን ለመግለጽ ባዘጋጁት መድረክ ላይ አርቲስት ደበበ እሸቱ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጸው፤ የኪነጥበብ ባለሙያዎች የህዝብ አገልጋዮች ናቸው፤ ህዝብን ማገልገል የሚቻለው ደግሞ ሀገር ሰላም ስትሆን ነው።
የኪነጥበብ ባለሙያዎች እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በሀገር ሉአላዊነት የተቃጣን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት ከሠራዊቱ ጎን በመቆም አለኝታነቱን ሊያረጋግጥ እንደሚገባ አመልክቷል።
“ሠራዊቱ የማይተካ ህይወቱን የሚሰዋው ሌላው የህብረተሰብ ክፍል በሰላም ተኝቶ እንዲያድር በመሆኑ ሠራዊቱ ህይወቱን ከሰዋ የኪነት ባለሙያው የዚህን ግማሽ ማድረግ አለበት“ ያለው አርቲስት ደበበ፤ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ከኋላ መሆን እንደማይፈልጉና ከሠራዊቱ ጎን በመሆን ይሄንን ጦርነት መካፈል እንደሚፈልጉ አስታውቋል።
ሠራዊቱን ማነቃቃት ፣ማነሳሳት እና የሠራዊቱ ደጋፊ መሆኑን ማረጋገጥ ከአርቲስቶች እንደሚጠበቅ ያመለከተው አርቲስት ደበበ ፣ አሁን የተጀመረው የአርቲስቶች ሥራ ጦርነቱ ሳያበቃ እንደማያቆም አመልክተዋል።
Filed in: Amharic