>

የሶማሊያ የርስበርስ ጦርነት በሰው ልጆችና በአለም አቀፉ ጸጥታ ላይ ያስከተለው መዘዝ ( ደረጀ መላኩ - የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)

የሶማሊያ የርስበርስ ጦርነት በሰው ልጆችና በአለም አቀፉ ጸጥታ ላይ ያስከተለው መዘዝ

ደረጀ መላኩ ( የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)

Tilahungesses@gmail.com

መግቢያ

እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1991 ላይ የተጀመረው የሶማሊያ የርስበርስ ጦርነት የተካሄደው በተለያዩ የጦር አበጋዞች መሃከል እና በጎሳ መሪዎች ተከታዮቻቸው መሃከል ነበር፡፡ የርስበርስ ጦርነቱ የሶማሊያ ሪፐብሊክን አዳክሟት ቆይቷል፡፡ አንድ ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት እንዳይኖራትም አድርጓታል፡፡ ከመሃመድ ሲያድባሬ መውደቅ ወዲህ ይህቺ ሀገር የተረጋጋች ሀገር መሆን ተስኗታል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ለሶስት የመከፈል እጣ ፈንታ ገጥሟታል፡፡

በርስበርስ ጦርነቱ ምክንያት ይህቺ ሀገር ከኢትዮጵያና ኬንያ ጋር የሚያወስኗት ደንበሮች ሁሉ ክፍት እንዲሆኑ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን መጥቀሱ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከዚህም ባሻግር የአለም አቀፍ አሸባሪዎች መርመስመሻም ሆና ቆይታለች፡፡ በህንድ ውቅያኖስ ላይ የባህር ላይ ወንበዴዎች እና እንደ አልሸባብ የመሰሉ ጽንፈኞች መራኮቻም ሆናለች ሶማሊያ፡፡ በዛሬው ዘመን ደግሞ ለአለም አቀፍ ጸጥታና ለሰው ልጅ ደህንነት ስጋት ሆናለች፡፡ ሶማሊያ የግጭት ቀጠና መሆን የጀመረችው በዚያድ ባሬ ያገዛዝ ዘመን ሲሆን መሃመድ ዚያድባሬ ከወደቁ በኋላ ደግሞ ጸጥታዋ የበለጠ  ደፍርሶ ነበር፡፡

ሶማሊያ በሁሉም የሐገሪቱ ክፍል እውቅና ያለው መንግስት የላትም፡፡ በተቃራኒው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ስልጣን የጨበጡ የተለያዩ ቡድኖች ወይም የፖለቲካ ተዋናዮች አሉ፡፡ (there are many actors who took power in various regions of the country) በሌላ የሳንቲሙ ግልባጭ ደግሞ አለም አቀፉ ህብረተሰብ እውቅና የሰጠው  ‹‹ የሶማሌ ብሔራዊ የሽግግር መንግስት ›› በሚል ስያሜ የሶማሊያ ህዝብ ህጋዊ ወኪል እንደሆነ በአለም አቀፉ 

ህብረተሰብ የሚደገፍ መንግስት ቆሞ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ይህ ደካማ መንግስት የሀገሪቱን ሰላም ሙሉበሙሉ ለማረጋጋት አልተቻለውም፡፡ የጎሳ ፖለቲካ መጨረሻው ውድቀትና ትርምስ ነው፡፡ ሶማሊያ ለጎሳ ፖለቲከኞች ዩንቨርስቲ ካልሆነች ሌላ ምን ትምህርት ይሆናቸዋል ?

መንግስትና የመሀመድ ዜያድባሬ ውድቀት

የሶማሊያ ሪፐብሊክ ከጣሊያንና ታላቋ ብሪታኒያ ቅኝ አገዛዝ ቀንበር ነጻ የወጣችው እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1960 ሲሆን፣ እንደ ብዙ የአካባቢው የፖለቲካ ተንጣኞች ጥናት ውጤት ከሆነ ለዘጠኝ አመት ከቆየ የዴሞክራሲ ( ማለትም እ.ኤ.አ. 1960 እስከ 1969 ድረስ) በቀር ሶማሊያ እስከ ጭንቅላቷ ድረስ በሙስና የተዘፈቀች  እና በዚህም የተሰቃየች ሀገር ሆናለች፡፡ መሀመድ ዜያድባሬ በመፈንቅለ መንግስት የነበረውን ተራማጅ መንግስት ገልብጠው ስልጣን ከጨበጡ ወዲህ ራሳቸውን የሶማሊያ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መንግስት ፕሬዜዴንት አድርገው ከመሾማቸው ባሻግር የአምባገነን ስርአት አንብረዋል፡፡ መሃመድ የማርክሲስት ርእዮት ተከታይ የነበሩ ሲሆን ፣ ብሔራዊ አንድነት ማምጣት ዋነኛ ተልእኳቸውም ነበር፡፡ ይህም ማለት ባህላዊውን የሶማሊያ የጎሳ ስርአት ለማንኮታኮት አቅድ ነበራቸው፡፡ በቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት አይዞህ ባይነትም የሳይንሳዊ ሶሻሊዝም የሀገሪቱ አዲስ ርእዮት አለም እንዲሆን ወስነው ነበር፡፡

እንደ ጆናታን ኢማኑኤል ብራንድ ሪቫ (Jonathan Immanuel Brand Rivas) የተባሉ የፖለቲካ ተመራማሪ በጥናታቸው እንደደረሱበት ከሆነ በወቅቱ የዚያድ ባሬ ለውጥ በከፊል ውጤታማ ነበር፡፡ ለአብነት ያህል፡

– ለብሄራዊ ቋንቋ የሚስማማ ፊደል ማዘጋጀት

– የትምህርት ስርአቱ መሻሻል

– የጤና ስርአት መቋቋም

– የመዋእለ ንዋይ ግንባታ

– የሴት ልጅ ግርዛት እንዲቆም ይደረግ የነበረው ዘመቻ የመሃመድ ዜያድባሬ ስኬቶች ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ህብረተሰቡ በመሀመድ የፖለቲካ ርእዮት ደስተኞች አልነበሩም፡፡

በአጠቃላይ እብሪተኛው የሲያድባሬ ጦር እንደጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1977 ኦጋዴንን በመወረር ከኢትዮጵያ ጦር ጋር ጦርነት ገጥሞ በመጨረሻም የውርደት ሸማ ተከናንቦ በመመለሱ በሶማሊያ ላይ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ድቀት ደርሶባታል፡፡ የዚህ የኢኮኖሚ ድቀት ውጤት ደግሞ በመሀመድ መንግስት ላይ በርካታ አማጽያን ሀይሎች እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል፡፡ መሀመድ ዜይድባሬን ገርስሶ ለመጣል በርካታ ሙከራዎች ከተካሄዱ በኋላ እንደ ጎርጎሮሲኑ አቆጣጠር 1989 ‹‹ የሶማሊያ አንድነት ኮንግረስ ›› (United Somali Congress (USC) )የተባለ የፖለቲካ ድርጅት ነፍጥ አንስቶ መዋጋት እንደጀመረ ከታሪክ እንረዳለን፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና በተጠቀሰው ፖለቲካ ድርጅት ውስጥ የነበሩ የድርጅቱ አመራሮች ርስበርስ የተቃረኑ ሲሆነ፣ እ.ኤ አ. 1990 የሲያድባሬ ጦር ተቆጣጥሮ የነበረው የሀገሪቱን ርእሰ መዲና ሞቃዲሾን( capital Mogadishu) ብቻ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ የሶማሊያ ፕሬዜዴንት የነበሩት አንዱ ሰትራቴጂ የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖችን ርስበርስ በመከፋፈል አንድነት እንዳይኖራቸው ማድረግ፣ በጎሳዎች መሃከል የጥላቻ መርዝ መርጨት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ይሁንና ቢሆንም ቅሉ ዚያድባሬ መንበራቸው ላይ ዝንተ አለም መቆየት አልቻሉም ነበር፡፡ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በጥር ወር 1991 አንዳንድ የሶማሊያ አንድነት ኮንግረስ አማጽያንን በማስከተል ሞቃዲሾን በግድ ለቀው ወደ ደቡብ ሶማሊያ የጁባ ሸለቆ ሸሽተው ሄደዋል፡፡ ከዚህ ባሻግር በነበረው የጥላቻ ቅስቀሳ ምክንያት የዚያድባሬ ተቀናቃኝ የነበሩትን አማጽያን የበቀል ጥቃት ሊያደርሱብን ይችላሉ በማለት  ፍርሃት ውስጥ የተዶሉት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የዳሮድ ጎሳ አባላት መሃመድ ዜያድባሬን ተከትለው ሄደው ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ባሬ የተወለዱት ከዳሮድ ጎሳ ቤተሰብ ስለነበር ነው፡፡ ( Barre was a Darod, too )

በግዜው የነበሩት አለም አቀፍ መገናኛ ዘገባ ከሆነ የተለያዩ አማጺ ቡድኖች  በደረሱበት ድምዳሜ ወይም ስምምነት መሰረት ሁሉም የተስማሙበት አዲስ መንግስት ለመመስረት ወስነው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና  የሶማሊያ አንድነት ኮንግሬስ ተዋጊዎች አመራር የነበሩት  መሃዲ ሞሀመድ እና ሞሃመድ አይዲድ የባሬን መንግስት ገርስሰን የጣልነው እኛ ብቻ ስለሆንን ስልጣኑን መጨበጥ ያለብን እኛ ብቻ ነን በማለት አወጁ፡፡ ይሄን ተከትሎ ሌሎች ቡድኖች ይህን የግል ውሳኔ ባለመቀበል የራሳቸውን ነጻ ግዛት በሰሜን ሶማሊያ መሰረቱ፡፡ (they declared the independence of Somaliland (situated in the north of Somali )

እንዳለመታደል ሆኖ የተባበረችው ሶማሊያ ኮንግሬስ የአይዲድ ቡድን( Aidid-group )እና መሃዲ ቡድን (Mahdi-group,)በሚል ለሁለት ተከፈሉ፡፡ ምክንያቱም የሶማሊያ ፕሬዜዴንት ቢሮ ማን መቆጣጠር አለበት ለሚለው መሰረታዊ ጥያቄ በግዜው ማን ምላሽ መስጠት አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ ስምምነት ለይ ለመድረስ ባለመቻሉ ነበር፡፡ በግዜው መሃዲ ሞቃዲሾ ከተማ ውስጥ ስለነበር የሶማሊያ ፕሬዜዴንት እኔ ነኝ በማለት ሲያውጅ፣ አይዲድ በበኩሉ በደቡብ ሶማሊያ የሲያድባሬን ጦር እያሳደደ ነበር፡፡ ከአለም መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ለመረዳት እንደተቻለው የአይዲድ ወታደሮች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የሶማሊያ ዜጎችን ገድለው ነበር፡፡ በዚህ መሰረታዊ ምክንያት ነበር እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠሩ 1991 በሶማሊያ ምድር የርሰበርስ ጦርነት የተቀሰቀሰው፡፡

በግጭት ውስጥ ተዱለው የነበሩ ቡድኖች

በሶማሊያ የርስበርስ ጦርነት በአንድም በሌላ መልኩ ተካፋይ የነበሩ በርካታ ቡድኖችን ማስታወስ ይቻላል፡፡ እነኚህ እኩይ ቡድኖች ሀገሪቱ ህግ አልባ እንድትሆን፣ደም መፋሰስ እንዲሰፍን፣አሸባሪነት እንዲሰፍንባት ሁነኛውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ ሀገሪቱ ህግ አልባ በመሆኗ ምክንያት እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1991 ጀምሮ ሱቆች፣የገበያ ስፍራዎች እና የመንግስት ተቋማትን ለመዝረፍ አመቺ ሁኔታዎች ተፈጥረው ቆይተዋል፡፡

በዛሬው ጽሁፌ ላይ የሀገሪቱን ማእከላዊ መንግስት ለመቆጣጠር ይፋለሙ የነበሩ ሁለት የጦር አበጋዞችን አማጺ ቡድኖችን ፍልሚያ በወፍ በረር ለማቀኘት እሞክራለሁ፡፡

ኮሎኔል አሊ ማሃዲ ሞሀመድ (Colonel Ali Mahdi Mohamed)

ኮሎኔል አሊ ማሃዲ ሞሀመድ የተወለዱት እንደ ጎርጎሮሲኑ አቆጣጠር 1939 ሲሆን ኮሎኔሉ የንግግር ችሎታ ያላቸው  ፖለቲከኛ የነበሩ እና የመሃመድ ዚያድባሬ አገዛዝ ከወደቁ በኋላ የሶማሊያ ፕሬዜዴንት እኔ ነኝ በማለት ያወጁ የጦር አበጋዝ ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን እርሳቸው የሶማሊያ አንድነት ኮንግሬስ መሪ የነበሩ ቢሆንም ፣ የመሃመድ ሲያድባሬን መንግስት ለመገርሰስ ሁነኛውን ሚና እንደተጫወቱ ቢታወቅም፣ በወቅቱ የነበሩት አማጺ ቡድኖች የኮሎኔሉን የሶማሊያ ፕሬዜዴንትነት አልተቀበሉም ነበር፡፡ ሌላው ተጨማሪ ነጥብ ደግሞ የተባበረችው ሶማሊያ ኮንግሬስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ የነበሩት መሀመድ አይዲድ ሳይቀሩ ለኮሎኔል አሊ ማሃዲ የሶማሊያ ፕሬዜዴንትነት በተመለከተ እውቅና ነፍገዋቸው እንደነበር ከታሪክ እንማራለን፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አኒሶም በመባል የሚታወቀው የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይል (The mission of the United Nations, called UNOSOM ) ሁለቱን ተፋላሚ ቡድኖች ወደ አንድነት፣ወደ ህብረትና መተባበር እንዲመጡ በብዙ መንገድ ጥረት ቢያደርገም ሊሳካለት እንዳልቻለ ከታሪክ እንማራለን፡፡ ከዚህ ባሻግር የተባበረችው አሜሪካ ወታደሮች የውርደት ሸማ ተከናንበው የሶማሊያ ዋና ከተማን ለቀው ከወጡ በኋላ መሃዲ እና አብዱላህ የሱፍ አህመድ የሀገሪቱን ካውንስል ሲመሰርቱ.፣ አይዲድ በበኩላቸው የሀገሪቱ መንግስት መሪ እኔ ብቻ ነኝ በማለት ዘውትር ይደሰኩሩ እንደነበር በግዜው መገናኛ ብዙሃን በሰፊው ሄደውበታል፡፡ እነዚህና ሌሎች ምክንያት ሶማሊያ ስርዓት አልበኝነት የሰፈነባት፣የጦር አበጋዞችና የተገንጣይ ቡድኖች መራኮቻ፣ የጎሰኞች መፈንጫ ሀገር ለመሆን በቅታለች፡፡

ጄኔራል ሞሀመድ ፋራህ አይዲድ General Mohamed Farah Aidid

አይዲድ የተወለዱት እንደ ጎርጎሮሲያን አቆጣጠር 1934 ሲሆን ፣ በሶማሊያ ታሪክ እና የርስበርስ ጦርነት ውስጥ አነጋጋሪ  የፖለቲካ መሪ (controversial political leader ) እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡ ጄኔራሉ የሶማሊያ አንድነት ካውንስል መሪ የነበሩ ፣ በተለይም የመሃመድ ሲያድባሬ መንግስትን ውድቀት ተከትሎ የሶማሊያ ፕሬዜዴንት ለመሆን ራሳቸውን የሰየሙ የጦር መሪም ነበሩ፡፡

በሶማሊያ የሰፈረውን እና አሚሶም በመባል የሚታወቀውን የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይል ወታደሮችን በማጥቃትና ከመገዳደር አኳያ ስመጥር ለመሆን በለስ ስለቀናቸው በግዜው አለም አቀፍ እውቅና ተችሯቸው ነበር፡፡ በዚህ በፈጸሙት ጀብዱ ምክንያት አይዲድ በተባበረችው አሜሪካ ዋነኛ ታዳኝ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ በነገራችን ላይ አይዲድ ስመጥር የጦር ሰትራቴጂስት ከመሆናቸው ባሻግር በቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት ሁነኛ ወዳጆች አፍርተው ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1977 በኦጋዴን በረሃ በተደረገው ጦርነት የሲያድባሬ ሁነኛ ወዳጅ በመሆን በጦርነት ውስጥ አዋጊ ከመሆናቸው ባሻግር በህንድ የሶማሊያ አምባሳደር ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና የጎሳ ፖለቲካ ባመጠው መዘዝ ምክንያት መሀመድ ሲያድባሬን በመክዳት የራሳቸውን የጎሳ ጦር ለማደራጀትና ለማስታጠቅ በቅተው ነበር፡፡ የጎሳ ፖለቲካ ምን ያህል አደገኛ የፖለቲካ ጨዋታ ከሶማሊያ ውድቀት መማር የሚቻል ይመስለኛል፡፡

እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ታህሳስ 1992 የሶማሊያ ህዝብ ድርቅና ጠኔ መደቆሱን ተከትሎ የብይነ መንግስታቱ ድርጅት በአኒሶም ስር  ወታደሮችን በመላክ የምግብ ስርጭቱ በችጋር ለሚሰቃየው የሶማሊያ ህዝብ እንዲዳረስ፣የሶማሊያ ህዝብ ጤንነቱ እንዲጠበቅ ጉልህ ድርሻ ተጫውቶ ነበር፡፡  ይህን ተከትሎ በጦር አበጋዙ ጄኔራል አይዲድ ይመራ የነበረው የጎሳ ጦር የእርዳታ ስርጭቱን ለማቋረጥ በከፈቱት የተኩስ እሩምታ 23 የፓኪስታን ዜግነት ያላቸውን የብይነመንግስታቱን ወታደሮች መግደላቸው ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎ አይዲድ በሶማሊያ ምድር ለተከሰተው ጦርነት እና ችጋር ዋነኛ ተጠያቂ ነው በተባባረችው አሜሪካ የጦር ሀይል እንዲታደኑ ትእዛዝ ተላለፈባቸው፡፡

በነገራችን ላይ ጄኔራሉ በሶማሊያ ምድር ስማቸው የገነነ የጦር መሪ ነበሩ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሰውየው አዲሶችን ቅኝ ገዢዎችን ስለተዋጉ ነበር፡፡ ከዚህ ባሻግር የህዝቡን ብሔራዊ ስሜት መቀስቀስ የቻሉ በብዙዎች ሶማሊያውያን እንደ ጀግና የሚቆጠሩም ነበሩ፡፡

እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በጥቅምት ወር 1993 ‹‹ አየርኒ ዘመቻ››(“Operation Irene) የሚል መጠሪያ ተልእኮ የተሰጣቸው የተባበረችው አሜሪካ ሬንጀር ለባሽ ስፔሻል ኮማንዶ (US-Rangers) ጦር አይዲድን ለመያዝ ሙከራ ቢደርጉም ውጤታማ መሆን አልተቻላቸውም ነበር፡፡  አለመሳካቱ ብቻ አልነበረም ዚቁ የአይዲድን እጅ ለመያዝ ከሄዱት ወታደሮች መሃከል 18 የተባበረችው አሜሪካ ወታደሮች እና አንድ የማሊዢያ ወታደር ተገድሏል፡፡

ይህን ተከትሎ በሶማሊያ ዋና መዲና ሞቃዲሾ ላይ በተካሄደው የጎዳና ላይ ጦርነት ከ1000 በላይ የሶማሊያ ዜጎች ህይወታቸው እንዳለፈ የሚሳዩ አሳዛኝ ዜናዎችን ከአለም መገናኛ ብዙሃ ተሰምቶ ነበር፡፡ይህ ጦርነት ‹‹ የሞቃዲሾ ጦርነት ›› በሚል በታሪክ ይታወቃል፡፡ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1995 የብይነ መንግስታቱ ወታደሮች በውርደት ሶማሊያን ለቀው ከወጡ በኋላ የጦር አበጋዙ ጄኔራል አይዲድ የሀገሪቱ መሪ እርሳቸው እንደሆኑ አወጁ፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ህይወታቸው እስከአለፈበት ግዜ 1996 ( እ.ኤ.አ.) አለም አቀፍ ተቀባይነትን ማግኘት አልቻሉም ነበር፡፡ እኚህ በሶማሊያ የርስበርስ ጦርነት ታሪክ ውስጥ ሁነኛ ሰፍራ የነበራቸው ወይም እፈሪና ሀይለኛ ተዋጊና የጦር አበጋዝ የነበሩት የጎሳ አምበል. ነሀሴ 1996 በጥይት ቆስለው መሞታቸውን ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

.የአለም አቀፉ ህብረተሰብ ጣልቃ ገብነት

አንድ ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት ለማንበር ባልሆነላት የርስበርስ ጦርነቱ ተፋፍሞ መቀጠሉ እውነት ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ በግዜው በሶማሊያ ምድር ድርቅና ጠኔ ተከስቶ ከ300000 እስከ 500000 ሶማሊያውያን እንደ ቅጠል መርገፋቸውን አለም አቀፉ መገናኛ ብዙሃን የዘገቡት መራር እውነት ነበር፡፡ አንዲት ሀገር በአክራሪ ጎሰኞች መዳፍ ስር ስትወደቅ ምን ያህል ወደ ምድራዊ ሲኦል ውስጥ እንደምትዘፈቅ ለማሳየት ሶማሊያ ታላቅ ዩንቨርስቲ ናት፡፡

ስለሆነም ኢትዮጵያውያን አፋጀሸኝ ከሆነው የጎሳ ፖለቲካ ለመገላገል በሰለጠነ መንገድ ቁጭ ብለው መነጋገር አለባቸው፡፡

በመጨረሻም እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1992 የብይነ መንግስታቱ ድርጅት ‹‹ የብይነ መንግስታቱ ተልእኮ በሶማሊያ ›› “United Nations Operation in Somalia” (UNOSOM) በሚል መጠሪያ የሰላም አስከባሪ ሀይል ወደ ሶማሊያ ለማላክ ወሰነ፡፡ እንደ አካባቢው የፖለቲካ ተንታኞች የጥናት ውጤት ከሆነ የብይነ መንግስታቱ ድርጅት የሰላም አስከባሪ ጦር ለመላክ የወሰነው በሚከተሉት ምክንያቶች ነበር፡፡

  • የጦር አበጋዝ የነበሩት አልመሃዲና አይዲድ መሃከል የነበረውን እውነት ለመገምገም
  • የስብዓዊ እርዳታ ለተጎጂው ህዝብ በተቃና ሁኔታ እንዲደርስ ለማገዝ
  • የብይነ መንግስታቱ ተልእኮ ሰብዓዊም ነበር (the mission was also humanitarian )

ሆኖም ግን ይሁንና የብይነ መንግስታቱ የሰላም አስከባሪ ሀይል በሁለት ምክንያቶች ችግር አጋጥሞት ነበር፡፡ አንደኛውና ዋነኛው የብይነ መንግስታቱ ሰላም አስከባሪ ሀይል በሁለቱ ዋነኞች የጦር አበጋዞች አኳያ እምነት ማግኘት አለመቻሉ ሲሆን፣ በህብረተሰቡ ዘንድ ደግሞ እንደ አዲስ ቅኝ ገዢ ሀይል ይቆጠር ነበር፡፡

ይህን ተከትሎ እንደ ጎርጎሮሲኑ አቆጣጠር ህዳር 1992 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዜዴንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ( ትልቁ ቡሽ)  ( US-President George H. W. Bush (Bush Sr.) )በተባበረችው አሜሪካ የሚመራ የብዙ ሀገራት ወታደሮች የተካተቱበት እና የተባበሩት የተልእኮ ሀይል (United task Force” (UNITAF) ( የሚል ስያሜ የተሰጠው የሰላም አስከባሪ ሀይል፣ ‹‹ ሰላም የማስፈን ዘመቻ› ሚል ተልእኮ በማንገብ  ወደ ሶማሊያ ለመላክ ወሰኑ፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ተልእኮ በብዙዎች ዘንድ ሰላም ያሰፍናል የሚል ተስፋን አችሮ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ተስፋው ተስፋ ሆኖ ቀርቷል፡፡ ይህ የሰላም አስከባሪ ሀይል ተልእኮውን በአሸናፊነት ለመወጣት ይከተል የነበረው  ስልት ወታደራዊ ሀይል በመጠቀም የጦር አበጋዞችን ለማንበርከክ እንደነበር ማስተወሱ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡

ከብዙ ችግሮች በኋላ የተጠቀሰው የሰላም አስከባሪ ሀይል በሌላ የብይነ መንግስታቱ የሰላም አስከባሪ ሀይል ( አሚሶም ሁለተኛ ይሰኝ ነበር) (by the peacekeeping mission of United Nations, UNOSOM )Iከተተካ በኋላ የሶማሊያን ምድር ለቆ ለመውጣት ተገዷል፡፡ ይህ ዘመቻ ቆይቶ የነበረወ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1995 ሲሆን ፣ በአንዳንድ የሶማሊያ ግዛቶች ጸጥታና ሰላም ማስከበር አኳያ፣ እንዲሁም የሶማያን የፖሊስ ሀይል እንደ አዲስ ለማዋቀር ችሎ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህ የሰላም አስከባሪም ቢሆን እረጅም ግዜ ሳይቆይ ሀገሪቱን ለቆ ወጥቷል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዘመቻ በሶማሊያ ዩኒሶም 1 ( እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ሚያዚያ 1992-  መጋቢት 1993) (, UNOSOM I (April 1992 – March 1993) ))

በተባባሩት መንግስታት ውሳኔ ቁጥር 751 መሰረት በሶማሊያ ምድር የሰላም አስከባሪ ሀይል የቆመው እ.ኤ.አ. 1992 ላይ ነበር፡፡ የዚህ የሰላም አስከባሪ ሀይል ዋነኛ ተልእኮ የነበረው በርሰበርስ ጦርነት ምክንያት ፍዳውን ለሚቆጥረው የሶማሊያ ህዘብ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያገኝበትን መንገድ ለማሳለጥ ነበር፡፡ ቢያንስ በድርቅና ጠኔ ምክንያት እየረገፈ የነበረውን 

ህዝብ ህይወት ለመታደግ ነበር፡፡

የመሃመድ ሰይድባሬ አገዛዝን መውደቅ ተከትሎ   ሀገሪቱ ማእከላዊ መንግስት ስላልነበራት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይል አስፈላጊነት በተመለከተ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡ ሀገሪቱ በስርአት አልበኝነት (the country was literary in an anarchy ) ውስጥ ተዱላ ነበር፡፡ አንደ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ከሆነ በሀገሪቱ በስተደቡብ ደርቅና ጠኔ ወደ 500000 የሚገመት ሶማሊዊ ዜጋ እንደ ቅጠል እረግፎ ነበር፡፡ ከሶማሊያ አጠቃላይ ህዝብ መሃከል ግማሽ ያህሉ ( 4.5 ሚሊዮን የሚገመተው) የሰብዓዊ እርዳታ ለማግኘት ሲል ሀገሪቱን ለቆ መሰደድ ግድ ብሎታል፡፡ ሶማሊያ በግዜው የገጠማትን ቀውስ ለመርዳት የብይነ መንግስታቱ ማህበር እና አለም አቀፉ ህብረተሰብ ተቸግረው ነበር፡፡ ስለሆነም የሰላም አስከባሪ ሀይል ወደ ሶማሊ ምድር መግባቱ ግድ ነበር፡፡ ስለሆነም በተባበሩት መንግስታት ውሳኔ ቁጥር 733 መሰረት በሶማሊያ ሙሉበሙሉ የጦር መሳሪያ ማእቀብ ተደረገባት፡፡ በውሳኔ ቁጥር 751 መሰረት ደግሞ ሰማያዊ ቀለም ያለው የብረት ሄልሜት ያጠለቁ ወደ 500 የሚጠጉ የሰላም አስከባሪ ሀይሎች ወደ ሶማሊያ ምድር እንዲገቡ ተፈቀደ፡፡ አጠቃላይ የአኑሶም ሰላም አስከባሪ ጦር ሀይል ብዛት 4500 የሚገመት ነበር፡፡ ዋና ማዘዣውን ሞቃዲሾ ከተማ አድርጎ የነበረው የሰላም አስከባሪ ሀይል ሱፐርቫይዘሮችን፣ ወታደራዊ ኤክስፐርት እና ሲቪል ሰራተኞችን ያካተተ ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የብይነ መንግስታቱ ማህበር በስፋት ካካሄዳቸው አንዱ በሆነው በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ዘመቻ 43 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ መደረጉን ማስተወሱ ተገቢ ሳይሆን

አይቀርም፡፡

      እንደ ቀደሙት የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪዎች ተልእኮ ሁሉ

የአሁኑም የተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ዋነኛ ተልእኮ የጦር አበጋዞቹን እውነተኝነት ለማረጋገጥ እና ጦርነት በመሃከላቸው እንዳይካሄድ ለማቆም፣ በሶማሊያ ምድር ሰብዓዊ እርዳታ ለተቸገረው ህዝብ የሚደርስበትን መንገድ ለማሳለጥና ሰላም ለማስከበር ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ታህሳስ 1992 የሶማሊያ የሰላም ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ ተዶለ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በጦር አበጋዞቹ አሊመሃዲ እና አይዲድ የጎሳ ሚሊሻዎች መሃከል ከባድ ውጊያ በመቀስቀሱ ነበር፡፡

በግዜው በሞቃዲሾ ከተማ ሃያል የነበሩት ሞሃመድ አይዲድ የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይል ሶማሊያን በፍጥነት ለቆ እንዲወጣ አስገድደው ነበር፡፡ በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይሎችን የሶማሊያ ህዝብ በጀግንነት እንዲመክታቸው ብሔራዊ ጥሪ አድርገው ነበር፡፡

በመጨረሻም እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1992 በአለሙ የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ቁጥር 794 ሌላ ቁጥሩ ከ25000 እስከ 30000 የሚገመትና የካናዳ፣ ታላቋ ብሪታኒያ፣አውስትራሊያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይና ከሌሎች ሀገራት የተወጣጣ የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይል በሶማሊያ እንዲሰፍር ተደርጎ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ይህ የብይነ መንግስታት ሰላም አስከባሪ ጦር ይመራ የነበረው በተባበረችው አሜሪካ ማእከላዊ እዝ እንደነበር ከብይነ መንግስታቱ የሰላም ማስከበር ታሪክ እንመራለን፡፡

እንዲህ አይነት የብዙ ሀገራትን ወታደሮች ያካተተ የሰላም ማስከበር ሀይል ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲገባ በርካታ ተግዳሮቶች ሊገጥሙት እንደሚችል ኢትዮጵያውን ሁሉ ልብ ልንል ይገባል፡፡ ዋነኛው ችግር የነበረው የመገናኛ ችግር ነበር፡፡ ለአብነት ያህል የኢጣሊያን ሰላም አስከባሪ ሀይል ፍላጎት የነበረው፣ የሶማሊያን ሚሊሻ ሀይል በማሰልጠን ሰላም እንዲያስከብሩ ነበር፡፡ የተባበረችው አሜሪካ በበኩሏ በምንም አይነት መልኩ ከሀገሬው ጦር ጋር ተቀራርባ መስራት አትፈልግም ነበር፡፡ በፈረንሳይ እዝ ስር የነበሩት የፈረንሳይ፣ ህንድ፣ ፓኪስታን እና የሞሮኮ ወታደሮች ሲቪሊና ጠላትን ለመለየት ተቸግርው ነበር፡፡ ይህም ብቻ አይደለም አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች ሳይቀሩ የተባበረችው አሜሪካን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በእጅጉ ኮንነውት ነበር፡፡

ውድ ወገኖቼ አንዲት ሀገር በርስበርስ ጦርነት ከታመሰችና ከደማች በኋላ የተባበሩት መንግስታት ጦር ሰላም ማስከበር አይሆንለትም፡፡ የባሰ ትርምስና ሁካታ ነው የሚፈጠረው፡፡ ኮንጎ፣ሶማሊያ እና ሶሪያ ትምህርት ሊሆኑን ይገባል፡፡ ሀገራችንን ከርሰበርስ ጦርነት መጠበቅ ምንም አማራጭ የለውም፡፡ በተባበሩት መንግስታት ሰላም ማስከበር ስም የማንም መፈንጫ መሆን የለብንም፡፡

የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ በሶማሊያ (አሚሶም እ.ኤ.አ. 2007) 

(The “African Union Mission to Somalia, AMISOM (since 2007) )

የአፍሪካ ህብረት ሚሽን በሶማሊያ ወይም በምህጻረ ቃሉ ‹‹አሚሶም›› ወደ ሶማሊያ ምድር በአፍሪካ ህብረት የተላከ የሰላም አስከባሪ ሀይል ሲሆን ዋነኛ ተልእኮ የነበረው የሶማሊያ የሽግግር መንግስት በሁለት ይቆም ዘንድ የሀገሪቱን ሰላምና ጸጥታ ማስከበር ነው፡፡ በመጀመሪያዎቹ አመታት የሰላም አስከባሪው ሀይል ቁጥር ወደ 3000 ይጠጋ እንደነበር ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡ በሂደት ግን በ10000ዎች የሚቆጠሩ የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሀይል በሶማሊያ ምድር እንደሰፈረ ይነገራል፡፡ በነገራችን ላይ የአፍሪካው ህብረት ጦር እንዲሰፍር የተደረገው የብይነ መንግስታቱ ሰላም አስከባሪ ሀይል በሶማሊያ ምድር ሰላም ማስከበር ባለመቻሉ እና በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ቁጥር 1725 ነበር፡፡ ታሪክ አይሸፈጥም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፍሪካው ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር በሶማሊያ መስፈሩ አስፈላጊ አንደነበር በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች የሚስማሙበት ጉዳይ ነበር፡፡ የአለም ነበራ ሁኔታ ተቀይሯል፡፡ በርካታ የእስልምና አሸባሪ ቡድኖች እንደሚያምኑት ከሆነ ሶማሊያ ‹‹ ለእንቅስቃሴያቸው ብቻ ሳይሆን ወደ ሌሎች ሀገራት ተሻግረው የሽብር ተግባራቸውን ለማቀጣጠል እንደ ገነት ትቆጠራለች›› ( ለአብነት ያል በሞዛምቢክ፣ማሊ…አክራሪ የሙስሊም ጽንፈኛ አሸባሪዎች የሚፈጽሙትን ግፍ ልብ ይሏል፡፡) በግዜው የሙስሊም ህብረት ፍርድ ቤት( the Union of Islamic Courts) የተሰኘው የሙስሊሞች ጽንፈኛ ቡድን በአለም፣ በተለየም በምስራቅ አፍሪካ የደቀነውን ከፍተኛ ስጋት ማስታወሱ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ይሄን ተከትሎ በብሔራዊ የጸጥታ ስጋት ችግር ምክንያት የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ህብረትን ውሳኔ የደገፈችው ኢትዮጵያ በኢስላሚክ ህብረቱ ላይ ጦርነት ማወጇ የሚታወስ ነው፡፡ የአፍሪካው ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል  በበኩሉ ኢትዮጵያ የሶማሊያን የሽግግር መንግስት ለመርዳት መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ድጋፉን ችሯት ነበር፡፡ በሶማሊያ ህዝብ ዘንድ ግን ከኢትዮጵያ ጋር ሶማሊያ በነበራት ታሪካዊ ቁርሾ ምክንያት የተነሳ ለኢትዮጵያ ጦር የነበራቸው አቀባበል በጥላቻ የተሞላ ነበር፡፡

እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 2007 ላይ ወደ ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የመጣው የአሚሶም ሰላም አስከባሪ ሀይል 1600 የሚገመት የኡጋንዳ ጦር ሲሆን በኡጋንዳው ሙሲቪኒ ገለጻ መሰረት የኡጋዳ ወታሮች ዋነኛ ተልእኮ የነበረው ፖሊስ እና ወታደሮችን ለማሰልጠን ነበር፡፡ ብቻውን ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት መሆን ያቃተው የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ከ8000 በላይ የአፍሪካ ህብረት ጦር ድጋፍ ተደርጎለት ነበር፡፡ የአሚሶም ሰላም አስከባሪ ሀይል ዋነኛ አላማ የነበረው ህገወጥ የጦር መሳሪያዎችን ከጎሳ ሚሊሻዎች ማስፈታት፣ የአየር ማረፊያ እና ወደቦችን መቆጣጠር፣ የሽግግር መንግሰቱ ፕሬዜዴንት መቀመጫ የሆነውን ቤተመንግስት the ( “Villa Somalia) መጠበቅ ፣ እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ ለተቸገረው ህዝብ በሰከነ መንፈስ እንዲዳረስ ማድረግ ነበር፡፡

በቁጥር 80000 የሚገመተው የአሚሶም የሰላም አስከባሪ ሀይል የተወጣጣው  ብሩንዲ፣ጋና ከኡጋንዳ፣ እና ናይጄሪያ ሀገራት የተወጣጣ ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የታንዛኒያ መንግስት 1000 የሶማሊያ ወታደሮችን ለማሰልጠን ቃል ሲገባ፣ እ.ኤ.አ.2007 ላይ የሩዋንዳ ፕሬዜዴንት ፖልካጋሚ በበኩላቸው የሶማሊያን የጦር ሀይል ለማቋቋም ወስነው ነበር፡፡ በመጨረሻም የተባበሩት አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ለአሚሶም የሰላም ማስከበር በስኬት መጠናቀቅ ይረዳ ዘንድ ከ60 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወረት ቸረዋል፡፡( ለግሰዋል)

 በሶማሊያ የሽግግር መንግስት መመስረት ( እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 2000)

በሶማሊያ ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር የሚከተሉት ጥረቶች ተደርገው ነበር፡-

አንደኛውና ዋነኛው ቁመነገር የነበረው በዲጁቢቲ ሪፐብሊክ ፕሬዜዴንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ (Djibouti’s President Ismail Omar Guelleh.) አነሳሽነት በዲጂቡቲ መዲና እንደ ጎርጎሮሲያ አቆጣጠር 2000 የሶማሊያ የሰላም ኮንፈርንስ ከተካሄደ ወዲህ የሶማሊያ የሽግግር መንግስት መመስረቱ የአለም መገናኛ ብዙሃንን ቀልብ ስቦ ነበር፡፡ ይህ ስብሰባ ወይም ኮንፍረንስ ሊካሄድ የበቃው  በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣በተባበረችው አሜሪካ እና በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጎማ ነበር፡፡ ይህ እጅግ ጠቃሚ ነበር፡፡ ምክንያቱም ይህ ጉባኤ ሁሉንም የሶማሊያ የጎሳ አምበሎች፣የሶማሊያ ሊህቆች፣የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣የሃይማኖት አባቶች እና የጦር አበጋዞች ተወካዮች ( የጦር አበጋዞች የተጋበዙት እርቅ ሰላም እንዲያወርዱ ነበር) ያካተተ(የወከለ) ስለነበር ነው፡፡ በዚህ ጉባኤ በቀድሞው የመሃመድ ሲያድባሬ አገዛዝ የሀገር ውስጥ ሚንስትር የነበሩት አብዲቃሲም ሳላት ሀሰን (Abdikassim Salat Hassan) የሶማሊያ ብሔራዊ የሽግግር መንግስት ፕሬዜዴንት እንዲሆኑ ተመርጠዋል፡፡ ይህም ማለት ሶማሊያ በርስበርስ ጦርነት ውስጥ ከተዘፈቀችበት 1991 (እ.ኤ.አ.) ወዲህ ዳግም አለም አቀፍ እውቅና ያለው መንግስት እንድታገኝ ታሪክ እድል ሰጥቷት ነበር፡፡

ሆኖም ግን ይሁንና ሳላት ሀሰን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር፣በመላው ሀገሪቱ ስልጣን ለመያዝ ብቁና ጠንካራ መሪ መሆን አልቻሉም ነበር፡፡ በርካታ የጎሳ አምበሎች አመጽ ቀስቅሰውባቸው ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ እ.ኤ.አ. 2002 የሽግግር መንግስት ሃሳብ በመሬት ላይ መታየት ተጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ ድጋፍ ያገኙት የፋራህ አይዲድ ልጅ የሆኑት ሁሴን መሀመድ ፋራህ እ.ኤ.አ. 2001 ‹‹ የሶማሊያ እርቅ እና መልሶ ማቋቋም ጉባኤን ›› ፡፡ “Somalia Reconciliation and Restoration Council ›› 

እ.ኤ.አ. 2003 የሶማሊያ የሽግግር መንግስት እና ሌላ አንድ ድርጅት በሶማሊያ ሰላም ለማስፈን ይረዳ ዘንድ አንድ ድርጅት መሰረቱ፡፡ ይህ ጥረት ትንሽ ፍሬ ለማፍራት ችሎ ነበር፡፡ ሰላም ለማስፈን በመጠኑም ቢሆን ተሳክቶለት ነበር፡፡

የሶማሊያ የሽግግር መንግስት መሰረታዊ ችግር

1.የሽግግር መንግስቱ መሰረታዊ ችግር የህጋዊነት ጥያቄ መልስ አለማግኘት ይመስለኛል፡፡ የሽግግር መንግስቱ የተመረጠው በሶማሊያ ህዝብ ሳይሆን ‹ የተመሰረተው በጉባኤ ነው፡፡

  1. እንደ ብዙ የሶማሊያ ፖለቲካ አዋቂዎች የጥናት ውጤት ከሆነ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የሶማሊያ ዜጎች በሽግግር መንግስቱ ላይ ጥላቻ አድሮባቸዋል፡፡ የዚህ መሰረታዊ ምክንያቱ ደግሞ የሶማሊያ የሽግግር መንግስት የኢትዮጵያ ወዳጅ በመሆኑ ነው

3.እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1992 ነጻነቷን ያወጀችው የሰሜን ሶማሊያ ግዛት ‹‹ ሶማሌላንድ››(Somaliland) ለሽግግር መንግስቱ እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኗ

  1. በርካታ የንግድ ሰዎች በሶማሊያ ምስቅልቅል ፖለቲካዊ ህይወት አትራፊ በመሆናቸው ሌላው ምክንያት ነው፡፡ እነኚህ የቀን ጅብ የሆኑ ነጋዴዎች ታክስ አይከፍሉም፡፡ የፈለጉትን ሸቀጥ ያለ መንግስታዊ ቁጥጥር ወደ ሀገር ውስጥ አስገብተው በፈለጉት ዋጋ ይሸጣሉ፡፡ ወደ ውጭ ሀገር ይልካሉ፡፡
  2. ሌላው መሰረታዊ ችግር የሶማሊያ ህዝብ አወቃቀር ነው፡፡ የሶማሊያ ህዝብ በአንድ ማእከል እዝ መምራት እጅጉን አስቸጋሪ ነው፡፡ በጭቆና ካልሆነ በቀር በማእከላዊ መንግስት ትእዛዝ ብቻ የሶማሊያን ህዝብ ማስተዳደር አስቸጋሪ ነው፡፡ በርግጥ መሃመድ ሲያድባሬ የሶማሊያን ህዝብ በአንድነት ለመግዛት ችለው ነበር፡፡ ምክንያቱ ግን መሀመድ ዴሞክራት ስለነበሩ አይደለም፡፡ መሃመድ በሃይል እና የራሳቸውን ጎሳ የበላይነት በማስጠበቅ ነበር የሶማሊያን ህዝብ ጨፍልቀው ለመግዛት የቻሉት ፡፡ የሶማሊያ ህዝብ አንድነት ሊጠበቅ የሚቻለው በደፌዴራል ዲሞክራቲክስርአት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች የሚስማሙበት አቢይ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬም ቢሆን የሦማሊያ የሽግግር መንግስት ተግዳሮት እየገጠመው ያለው አቢይ ጉዳይ የቀድሞውን አይነት አገዛዝ ሊያስቀጥል ይችላል በሚል ጥርጣሬ ነው፡፡

As we know, traditional society in Somalia was and is decentralized. There are many federative elements inside it and it is practically impossible, to organize it in a centralized form, without repression. Siad Barre tried it, and well, he was able to do it, because of dictatorial elements and clientelism with respect to his own clan. That is the reason, why people do not have any confidence to the TNG, yet.

ክፍል ሁለት ሳምንት ይቀጥላል

Filed in: Amharic