>
5:13 pm - Friday April 19, 1354

ሕዝቤ ሆይ. . . እናትህን፣ ሚስትህን በልጆቿና በባሏ ፊት የሚደፍር ጠላት ወሮሀል...!!!!   (አቻምየለህ ታምሩ)

ሕዝቤ ሆይ. . . እናትህን፣ ሚስትህን በልጆቿና በባሏ ፊት የሚደፍር ጠላት ወሮሀል…!!!!  

አቻምየለህ ታምሩ

ፋሽስት ወያኔ በወረራ በያዛቸው የጎንደርና የወሎ አካባቢዎች አባወራውን የፊጥኝ አስረው ዐይኑ እያዬ ሚስቱን ከፊቱ በየተራ እየተፈራረቁ ደፍረዋል፤ አባትና እናትን አስቀምጠው ሴት ልጃቸውን ከፊታቸው በመድፈር ክብረ ንጽሕናዋን አጉድፈዋል፤ እናትን በልጆቿ ፊት ደፍረዋታል።
ብአዴን ግን ይህንን የፋሽስት ወያኔ አለማቀር ወንጀል ለአማራና ለተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ እስካሁን ድረስ አላሳወቀም። ዛሬ ክምር ድንጋይ፣ ትናንትና ሰቆጣ በፋሽስት ወያኔ ተይዘው ብአዴን ዛሬም በልሳኖቹ የሚለፈው “ተከበዋል፣ ሸሽተዋል፣ አፈግፍገዋ፣ ተቆርጠው ቀርተዋል፣ ወዘተረፈ. …” እያለ ነው።
ሕዝቤ ሆይ! አባወራውን የፊጥኝ አስሮ ዐይኑ እያየ ሚስቱን ከፊቱ በየተራ እየተፈራረቁ ሊደፍሩ፤ አባትና እናትን አስቀምጦ ሴት ልጃቸውን ከፊታቸው ለመድፈርና ክብረ ንጽሕናዋን ለያማጉድፉ፤ እናትን በልጆቿ ፊት ለመድፈር በአሁኑ ወቅት ፋሽስት ወያኔ ከደብረ ታቦር በ16 ኪሎ ሜትር፤ ከደሴ ደግሞ በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
እናቱን በልጆቿና በባለቤቷ ፊት ሊደፍር፤ እኅቱን በእናትና አባቷ ፊት ክብረ ንጽሕናዋን ሊያጎድፍ እየወረረ ያለው ፋሽስት ወያኔ የሚያደርስበትን ውርደት ተቀብሎ ላለመኖር የሚሻ ሁሉ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ተነስቶ በእናቱና በእኅቱ የመጣበትን አረመኔ እንደ ተርብ ለመንደፍ በየአካባቢው በየጎበዝ አለቃው ተደራጅቶ ከውርደር ራሱንና ቤተሰቡን ይታደግ ዘንድ ለሕዝብ ጥሪ መቅረብ አለበት!
ሕዝቤ ሆይ. . . እናትህን በልጆቿና በባሏ ፊት በመድፈር፤ እኅትህን በእናትና አባቷ ፊት ክብረ ንጽሕናዋን በማጉደፍ ሒሳብ ሊያወራርድ የተነሳ አረመኔ ጠላት እየወረረህ ስለሆነ ለእናትህ፣ ለእኅትህና ለሚስትህ ስትል ተነስ!
Filed in: Amharic