>
5:21 pm - Saturday July 20, 3196

የፕሮፈሰር ገላውዲዮስ አርኣያ ነገር ...!!!  (አቻምየለህ ታምሩ)

የፕሮፈሰር ገላውዲዮስ አርኣያ ነገር …!!! 

አቻምየለህ ታምሩ

ሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኒዮርክ (City University of New York) ውስጥ ታሪክና ፖለቲካል ሳይንስ የሚያስተምሩት የፋሽስት ወያኔው “ምሑር” ፕሮፈሰር ገላውዲዮስ አርኣያ “ብዙ አጥንቸዋለሁ፤ ከኔ በላይ የሚያውቀው የለም” ባሉት በወልቃይት ታሪክ ዙሪያ ክርክር ለማድረግ ከአስር ወራት በፊት የሜዲያ ቀጠሮ ተይዞላቸው ነበር።
ሆኖም ግን የታሪክ ክርክሩን የሚያደርጉት ከኔ ጋር እንደሆነ ሲነገራቸው የሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኒዮርክ የታሪክ ምሑሩ ፕሮፌሰር ገላውዲዮስ አርአያ “በሉ.. በሉ.. ይቅርብኝ፤  ከአቻምየለህ ጋርማ ክርክር አላደርግም” ብለው በመፈርጠጣቸው ለረጅም ጊዜ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው  የታሪክ ክርክር ሳይካሄድ ቀረ።
የታሪክ ፕሮፈሰር ሆነው ታሪክን አንብቦ ለማወቅ ከሚፍጨረጨር አንድ ፍሬ ልጅ ጋር ሞያቸው በሆነው የታሪክ መስክ መከራከር እንደማይችሉ ተናግረው የፈረጠጡ ፕሮፈሰር ገላውዲዮስ አርኣያ ከፍርጠጣቸው መልስ የውሸት ቋታቸው በሆነው ትግራይ ሜዱያ ሀውስ ቀርበው [በትግርኛ የሚያደርጉትን ንግግር የሚሰማ ሰው የለም ብለው በማሰብ ይመስላል] “ሓደ ትምኽተኛ አቻምየለህ ዝበሀል” በማለት እየሰደቡን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።
የፋሽስት ወያኔና የናዚ ኦነግ የታሪክ ዶክተሮችና ፕሮፈሰሮች [የተረት አባቶች ብላቸው ይቀለኛል] በእውቀት ላይ የሚደረግን ክርክር እንደጦር ነው የሚፈሩት። እንደ ፋሽስት ወያኔው ፕሮፈሰር ገላውዲዮስ አርኣያ ሁሉ በርካታ የናዚ ኦነግ የታሪክ ዶክተሮችና ፕሮፈሰሮችም የታሪክ ክርክር ለማድረግ ቀጠሮ ካስያዙ በኋላ የሚከራከሩት ከኔ ጋር መሆኑን ሲያውቁ “ኧረረረ ከሱ ጋርማ አንከራከርም” በማለት ስለፈረጠጡ ቀጠሮ የተያዘላቸው ብዙ የታሪክ  ክርክሮች ሳይደረጉ ቀርተዋል።
ኦነጋውያኑ እነ ዶክተር በያን አሶባ፣ ፕሮፈሰር ሕዝቃኤል ጊቢሳ፣ ሌንጮ ለታ፣ ዶክተር መስፍን አብዲ፣ ዶክተር ዲማ ነገዎ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባ፤  የግንቦት ሰባቱ አንዳርጋቸው ጽጌ፤  ኢሕአፓዎቹ ኢያሱ አለማየሁ፣ ክፍሉ ታደሰና ታደለች ኃይለሚካኤል [የብርሀነ መስቀል ረዳ ባለቤት]፤ የማሌሪዱ መሪ ተስፋዬ መኮንን፣ ወዘተ ክርክር ሊያደርጉ ቀጠሮ አስይዘው የሚከራከሩት ከኔ ጋር መሆኑ ሲነገራቸው ክርክሩን ሰርዘው ከፈረጠጡ ያ ትውልዴዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
የሆነው ሆኖ አንድ ሰው አወቀ የሚባለው የመረመረውን፣ ያጣራውን፣ ያረጋገጠውንና አለኝ የሚለውን እውነት ፊት ለፊት ይዞ ቀርቦ ሲከራከር እንጂ ፕሮፈሰር ገላውዲዮስ አርኣያ እንዳደረጉት ከማን ጋር እንደሚከራከር ሲነገረው ፈርርጦ ከሄደ በኋላ የሚናገረውን ማንም አይሰማም ብሎ በማሰብ በጓዳ በር ተደብቆ ሲሳደብ ሲውል አይደለም!
Filed in: Amharic