>
5:13 pm - Tuesday April 19, 4935

*የመንግስትነት ለዛና ጣእም ልናገኝብህ ስላልቻልን ድንጋይ ነው ብለን እንጥልሀለን...!!!"(ጎዳና ያእቆብ)

*የመንግስትነት ለዛና ጣእም ልናገኝብህ ስላልቻልን ድንጋይ ነው ብለን እንጥልሀለን…!!!”*
ጎዳና ያእቆብ


ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ: አንተ እራስህ ጽንፈኛ ፓለቲካ እያራመድክ ሌሎችን ፅንፈኛ የማለት ብሎም መካሪ ለመሆን ለመነሳት የስነምግባርም ይሁን የሞራል ብቃት የለህም:: እውነት ለመናገር ስራህ ከነጃዋ. እና ከመሰል “ፅንፈኞቹ” የከረረ ፅንፈኛ እንደሚያደርግህ ያለፉት ሁለት አመት ከመንፈቅ የቁልቁለት ጉዞህ አመላካች ብቻ ሳይሆን ገላጭም ነው::

እንደመንግስት ገለልተኛ (impartial) አለመሆንህን ስራህ እና ፓሊሲዎችህ ግልፅ አድርጎ ስላሳየን ዛሬም ከቅቤ በሚለሰልሱ ቃላቶችን የኢትዮጵያን ህዝብ አሳምናለሁ ወይም አደናግራለሁ ብለህ መነሳትህ አንድም የራስህን የማሳመን ብቃት ከመጠን በላይ አድርጎ ማየት ሲሆን: ሌላው ህዝብን መናቅ ነው::

የኢህአዲግ ቀዳማዊ ( ዳግማዎው አሁን አንተ ብልፅግና የምትለው ከመልከ ጥፉን በስም ይደግፉ ያላለፈ ለውጥ ሳይሆን ልውውጥ ማለት ነው) ቅጥ ያጣ ህዝብን ንቀት ዛሬ የት እንዳደረሰው አለማየት እና ከዛም አለመማር የግንዛቤ ችግር ሁሌም የሚያደርሰው ወደአንድ መንገድ ነው – ውድቀት:: እባብ እባ የፓለቲካ ፓርቲ መበስበስ የሚጀምረው ከራሱ ነውና ግብዝነት የተሞላበት ምክር ትተህ እራስህን ቆም ብለህ መመርመር ይኖርብሀል:: ወንበሩ ሲሞቅህ የህዝብ ውገልጋይ መሆንህን ረስተት ጌታ የመሆን ባህሪያት ስለሚንፀባረቁብህ እራስህን አራም -ካልሆነ አንተንም ካንተበፊት እንደነበሩት እንተፋሀለን::

የመንግስትነት ለዛና ጣእም ልናገኝብህ ስላልቻልን ድንጋይ ነው ብለን እንጥልሀለን::

ፅንፈኛው አንተ ነህና በስምህ እንጠራሀለን:: ኦነግ ሸኔ እና ህዋሀት የምትላቸው የጦስ ዶሮዎችህ ዛሬ እያስከተሉት ካሉት ጉዳት ይልቅ ሀገራችንን አደጋ ላይ እየጣሉ ያሉት አንተ እና ያንተ ሹም ሽሮች ናቸው እና ወደራስህ ተመልከት::

የኢትዮጵያ ፓለቲከኞች እንደሰፈር አራዶች ናቸው ምን ሰርቼ ላሳምን ሳይሆን በምን አጭበርብሬ ላደናግር ነው ሁሌ የሚሉት ያልከውን የራስህን ንግግር አድምጥ::

ጆሮ የሌለው አፍ ብቻ አትሁን:: እግዚያር ሁለት ጆሮ እና አንድ አፍ ለፍጡሮቹ የሰጠው ከሚያወሩት እጥፍ እንዲያደምጡ ነውና አድምጥ::

አዲስ አበቤን የግፍ መድረክ እና የእምባ መናሀሪያ ያደረገው ያንተ ፓርቲና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አድርገህ የሾምከው ታከለኡማ ነው:: ቢያንስ ቢያንስ የሽወዳ ታክቲክ ቀይር:: አደብ ይኑርህ:: ፍትህ እወቅ:: በወንበርህ እና ለስልጣንህ የሚገባ ስነምግባር እና ዲሲፒሊን ይኑርህ:: አሁን ላይ ህዝብ የምትሰራውን እንጂ የምታወራውን ስለማይሰማ ወሬ ይብቃ!

Filed in: Amharic