>

ያልተሰሙ የሰቆቃ ድምጾች በወሎ ምድር...!!! (ጌታቸው ሙላት)

ያልተሰሙ የሰቆቃ ድምጾች በወሎ ምድር…!!!

ጌታቸው ሙላት

ተፈናቃዮን፣ እርዳታ አሰባሳቢዉንና እርዳታ አሰጣጡን በሚመለከት። ይህ የአፈናቃይ ተፈናቃይ ታሪክ በአገራችን የተለመደ፣ የተደጋገመና የተሰለቼ ነዉ። በመሆኑም ተፈናቃዩን ለመርዳት ህዝብ እርዳታ ያሰባስባል፣ ከአገር ቤት እስከ ዉጭ አገር ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአቅሙን ከፍተኛ አስተዋፆ ያደርጋል። ታዲያ ይህ እርዳታ በትክክል እየዋለ ነዉ ወይ? ከሚል ዝርዝር ዉስጥ አልገባም፣ ሆኖም ይህ መቆሚያ ያጣ መፈናቀል፣ ያዉም የተፈጥሮ አደጋ ያስከተለው ችግር ያልሆነ መንግስት ባለበት አገር በታጣቂ ሰዉ ሰራሽ ወንበዴ የሚፈፀም መሆኑና ዝም ተብሎ መታየቱና መቀጠሉ ነዉ አስገራሚ የሚያደርገዉ። ይሄ መፈናቀል የሚቆመዉ መቼ ነዉ? እንዴት ነዉ? ካልን አፈናቃዮች በቁጥጥር ሥር ሲዉሉ ወይም ሲዎገዱ ብቻ ነዉ። ይሄን ማድረግ የሚችለዉና ግዴታም ያለበት ደግሞ መንግሥት ነዉ። በመንግስት ላይ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተፅኖ መደረግ አለበት። መንግስት የኃይል እጥረት ካለበት እንኳ ተፈናቃዮችን አሰልጥኖ እንዲያስታጥቅ ራሳቸዉን እንዲከላከሉ ድጋፍ እንዲሰጥ፣ ሌላዉ ተፈናቃዩ በተተኮሰ ቁጥር ቀየዉን ለቆ ከመሸሽና ከመሮጥ ይልቅ በዚያው ባለበት መመከት እንዲችል እንዲዘጋጅ ማድረግና አፈናቃይ ሲመጣበት እንዲመክት ማድረግ ነዉ። ስለዚህ ሩጦ ወደ መጠለያ ለሚገባ አካሉና አይምዕሮዉ ጤነኛ እድሜው ከ18 ዓመት በላይ ለሆነ እርዳታዉ በመጠለያ እንዳይሰጥ፣ ሰፈሩን መንደሩን በመከላከሉ ላይ እንዲሳተፍ እንዲደረግ መሆን አለበት። ሌላዉ አፈናቃዩ እስካለ ድረስ መፈናቀል ስለማይቆም ትኩረቱ ሁሉ አፈናቃዩን ከማስወገዱ ላይ ነዉ መሆን ያለበት፣ በዚህ ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት ያለበት።
ይህ ካልሆነ ግን መፈናቀሉም አይቆምም እርዳታዉም በቂ አይሆንም፣ እንዲያዉም ከአፈናቃዩ ጋር ለሚደረገዉ ትግል ሪሶርስ ያባክናል፣ መጨረሻዉም አያምርም።
Filed in: Amharic