>

ብልፅግና ሆይ- በአዲሱ ዓመት እጅህ ከምን"!? (ልደቱ አያሌው)

ብልፅግና ሆይ- በአዲሱ ዓመት እጅህ ከምን”!?

ልደቱ አያሌው

ኢትዮጵያውያን ከተደጋጋሚው የውድቀት ታሪካችን መማር ከቻልን ውስጣዊ የፖለቲካ ችግራችንን በመፍታት ረገድ ጦርነት የመጀመሪያ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻ አማራጭ ሆኖ
የመቅረብ ዕድሉም እስከወዲያኛው መዘጋት አለበት። በሁሉም ዓይነት የውጤታማነት መመዘኛ ሀገራችንን እጅግ ኋላ-ቀርና የዓለም ጭራ እንድትሆን ባደረጋት የጦረኝነት ባህላችን ልንፈታው የምንችል የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ችግር የለም። በአሁኑ ወቅት የገባንበት ጦርነትም የመጨረሻ ውጤቱ ሁላችንንም የጋራ ተሸናፊ ከማድረግ ያለፈ የተለየ ፋይዳ አይኖረውም። ይህንን ጦርነት በማሸነፍ፤ በመሸነፍም ሆነ ሳይሸናነፉ በጦርነቱ በመቀጠል የምናሳካው አንድም ሀገራዊ ውጤት የለም። የወቅቱ ጦርነት ለአንድ ተጨማሪ ቀን
በቀጠለ ቁጥር መፍትሄውን የበለጠ ከማወሳሰብና ከማራቅ፣ የሕዝቡን እልቂት የበለጠ ከማባባስና የሀገር ፍርሰቱን ሂደት የበለጠ ከማፋጠን ውጪ ለችግራችን መፈታት ምንም ዓይነት አዎንታዊ አስተዋፅዖ የለውም። በአጭሩ፣ ጦርነት በጥላቻ የምንገዛና በአስተሳሰብ ደካማ የመሆናችን ውጤት
እንጂ በራሱ የችግራችን ምንጭ አይደለም፡፡ ጦረኝነትን በውይይትና በድርድር ባህል በመተካት እንጂ በጦርነት አሸናፊ በመሆን ችግራችን በዘላቂነት አይፈታም፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው አስቀያሚ ጦርነት ለተራዘመ ጊዜ የሚቀጥል ከሆነ ሂደቱ ሀገር ተረካቢውን ትውልድ በገፍ የሚቀጥፍ፣ ውጤቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን አሟጦ የሚያጠፋና ሀገሪቱን የሚበትን ከመሆን የተለየ ምንም ዓይነት በጎ ውጤት አይኖረውም፡፡
የሀገራችን የፖለቲካ ችግር አሁን ላይ ከደረሰበት እጅግ ውስብስብ የሆነ ደረጃ አንፃር ሁሉን-አቀፍ የሆነ አዲስ የሽግግር መንግሥት ከማቋቋም ባነሰ ሌላ ጥገናዊ ለውጥም ሆነ የጦርነት አማራጭ የመፈታት ዕድል የለውም። ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ አዋጪ አማራጭ ብሔርተኝነትና ጦረኝነት አሸናፊ አመለካከት ሆነው በነገሱበት በአሁኑ ወቅት በቀላሉ ተቀባይነት ሊያገኝ እንደማይችል ግልፅ ነው። ሆኖም አይቀሬ የሆኑ አስገዳጅ ሁኔታዎች ተፈጥረው ጥያቄው ተቀባይነት እስከሚያገኝ ድረስ የሚሆነውን ሁሉ በዝምታ ማየት የለብንም፡፡ ማለትም ከዋናው መፍትሄ በመለስ ያሉና መለስተኛ ውጤት ሊያስገኙ የሚችሉ ሌሎች የመፍትሄ ሃሳቦችንም ለማቅረብ መሞከር ጠቃሚና ተገቢ ይሆናል። ይህንን የዛሬውን ምክረ-ሃሳቤን ለማቅረብ የምሞክረውም
ከዚህ እሳቤ በመነጨ መሆኑን ለማስገንዘብ እወዳለሁ።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምትገኘው የወደፊት መፃዒ-ዕድሏን በሚወስን አደገኛ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው። ከመስቀለኛው መንገድ መካከል የመጀመሪያው ጦርነትን ወደ�ማሸነፍ፣ ሁለተኛው ጦርነትን ወደ-መሸነፍ፣ ሶስተኛው በተራዘመ የጦርነት ሂደት ወደ-መቀጠል፣
አራተኛው ጦርነቱን አቁሞ ወደ-ሰላማዊ የድርድር ሂደት ለመግባት የሚያስችል መንገድ ነው። ከእነዚህ አራት መንገዶች ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ሶስት መንገዶች የወቅቱን ችግር አጠናክረው የሚያስቀጥሉ የጥፋት መንገዶች ሲሆኑ ሀገሪቱን ከአጠቃላይ ውድመትና መፍረስ ለመታደግ
የሚያስችል ዕድል የሚፈጥርልን አራተኛው መንገድ ብቻ ነው። ወደዚህ መንገድ ለመግባት ግን ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ቅንነትና ዕውቀት ያለው፣ አርቆ-አሳቢና ሀገር ወዳድ የሆነ፣ ኢትዮጵያውያን ከተደጋጋሚው የውድቀት ታሪካችን መማር ከቻልን ውስጣዊ የፖለቲካ ችግራችንን በመፍታት ረገድ ጦርነት የመጀመሪያ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻ አማራጭ ሆኖ የመቅረብ ዕድሉም እስከወዲያኛው መዘጋት አለበት። በሁሉም ዓይነት የውጤታማነት መመዘኛ
ሀገራችንን እጅግ ኋላ-ቀርና የዓለም ጭራ እንድትሆን ባደረጋት የጦረኝነት ባህላችን ልንፈታው የምንችል የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ችግር የለም። በአሁኑ ወቅት የገባንበት ጦርነትም የመጨረሻ ውጤቱ ሁላችንንም የጋራ ተሸናፊ ከማድረግ ያለፈ የተለየ ፋይዳ አይኖረውም። ይህንን ጦርነት በማሸነፍ፤ በመሸነፍም ሆነ ሳይሸናነፉ በጦርነቱ በመቀጠል የምናሳካው አንድም ሀገራዊ ውጤት የለም። የወቅቱ ጦርነት ለአንድ ተጨማሪ ቀን በቀጠለ ቁጥር መፍትሄውን የበለጠ ከማወሳሰብና ከማራቅ፣ የሕዝቡን እልቂት የበለጠ ከማባባስና
የሀገር ፍርሰቱን ሂደት የበለጠ ከማፋጠን ውጪ ለችግራችን መፈታት ምንም ዓይነት አዎንታዊ አስተዋፅዖ የለውም። በአጭሩ፣ ጦርነት በጥላቻ የምንገዛና በአስተሳሰብ ደካማ የመሆናችን ውጤት እንጂ በራሱ የችግራችን ምንጭ አይደለም፡፡ ጦረኝነትን በውይይትና በድርድር ባህል በመተካት እንጂ በጦርነት አሸናፊ በመሆን ችግራችን በዘላቂነት አይፈታም፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት
እየተካሄደ ያለው አስቀያሚ ጦርነት ለተራዘመ ጊዜ የሚቀጥል ከሆነ ሂደቱ ሀገር ተረካቢውን ትውልድ በገፍ የሚቀጥፍ፣ ውጤቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን አሟጦ የሚያጠፋና ሀገሪቱን
የሚበትን ከመሆን የተለየ ምንም ዓይነት በጎ ውጤት አይኖረውም፡፡ የሀገራችን የፖለቲካ ችግር አሁን ላይ ከደረሰበት እጅግ ውስብስብ የሆነ ደረጃ አንፃር ሁሉን-አቀፍ
የሆነ አዲስ የሽግግር መንግሥት ከማቋቋም ባነሰ ሌላ ጥገናዊ ለውጥም ሆነ የጦርነት አማራጭ የመፈታት ዕድል የለውም። ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ አዋጪ አማራጭ ብሔርተኝነትና ጦረኝነት አሸናፊ አመለካከት ሆነው በነገሱበት በአሁኑ ወቅት በቀላሉ ተቀባይነት ሊያገኝ እንደማይችል
ግልፅ ነው። ሆኖም አይቀሬ የሆኑ አስገዳጅ ሁኔታዎች ተፈጥረው ጥያቄው ተቀባይነት እስከሚያገኝ ድረስ የሚሆነውን ሁሉ በዝምታ ማየት የለብንም፡፡ ማለትም ከዋናው መፍትሄ በመለስ ያሉና መለስተኛ ውጤት ሊያስገኙ የሚችሉ ሌሎች የመፍትሄ ሃሳቦችንም ለማቅረብ
መሞከር ጠቃሚና ተገቢ ይሆናል። ይህንን የዛሬውን ምክረ-ሃሳቤን ለማቅረብ የምሞክረውም
ከዚህ እሳቤ በመነጨ መሆኑን ለማስገንዘብ እወዳለሁ።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምትገኘው የወደፊት መፃዒ-ዕድሏን በሚወስን አደገኛ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው። ከመስቀለኛው መንገድ መካከል የመጀመሪያው ጦርነትን ወደ�ማሸነፍ፣ ሁለተኛው ጦርነትን ወደ-መሸነፍ፣ ሶስተኛው በተራዘመ የጦርነት ሂደት ወደ-መቀጠል፣
አራተኛው ጦርነቱን አቁሞ ወደ-ሰላማዊ የድርድር ሂደት ለመግባት የሚያስችል መንገድ ነው። ከእነዚህ አራት መንገዶች ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ሶስት መንገዶች የወቅቱን ችግር አጠናክረው የሚያስቀጥሉ የጥፋት መንገዶች ሲሆኑ ሀገሪቱን ከአጠቃላይ ውድመትና መፍረስ ለመታደግ
የሚያስችል ዕድል የሚፈጥርልን አራተኛው መንገድ ብቻ ነው። ወደዚህ መንገድ ለመግባት ግን ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ቅንነትና ዕውቀት ያለው፣ አርቆ-አሳቢና ሀገር ወዳድ የሆነ፣ ኢትዮጵያውያን ከተደጋጋሚው የውድቀት ታሪካችን መማር ከቻልን ውስጣዊ የፖለቲካ ችግራችንን በመፍታት ረገድ ጦርነት የመጀመሪያ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻ አማራጭ ሆኖ የመቅረብ ዕድሉም እስከወዲያኛው መዘጋት አለበት። በሁሉም ዓይነት የውጤታማነት መመዘኛ ሀገራችንን እጅግ ኋላ-ቀርና የዓለም ጭራ እንድትሆን ባደረጋት የጦረኝነት ባህላችን ልንፈታው የምንችል የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ችግር የለም። በአሁኑ ወቅት የገባንበት ጦርነትም የመጨረሻ ውጤቱ ሁላችንንም የጋራ ተሸናፊ ከማድረግ ያለፈ የተለየ ፋይዳ አይኖረውም። ይህንን ጦርነት በማሸነፍ፤ በመሸነፍም ሆነ ሳይሸናነፉ በጦርነቱ በመቀጠል የምናሳካው አንድም ሀገራዊ ውጤት የለም። የወቅቱ ጦርነት ለአንድ ተጨማሪ ቀን በቀጠለ ቁጥር መፍትሄውን የበለጠ ከማወሳሰብና ከማራቅ፣ የሕዝቡን እልቂት የበለጠ ከማባባስና የሀገር ፍርሰቱን ሂደት የበለጠ ከማፋጠን ውጪ ለችግራችን መፈታት ምንም ዓይነት አዎንታዊ አስተዋፅዖ የለውም። በአጭሩ፣ ጦርነት በጥላቻ የምንገዛና በአስተሳሰብ ደካማ የመሆናችን ውጤት እንጂ በራሱ የችግራችን ምንጭ አይደለም፡፡
ጦረኝነትን በውይይትና በድርድር ባህል በመተካት እንጂ በጦርነት አሸናፊ በመሆን ችግራችን በዘላቂነት አይፈታም፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው አስቀያሚ ጦርነት ለተራዘመ ጊዜ የሚቀጥል ከሆነ ሂደቱ ሀገር ተረካቢውን
ትውልድ በገፍ የሚቀጥፍ፣ ውጤቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን አሟጦ የሚያጠፋና ሀገሪቱን የሚበትን ከመሆን የተለየ ምንም ዓይነት በጎ ውጤት አይኖረውም፡፡ የሀገራችን የፖለቲካ ችግር አሁን ላይ ከደረሰበት እጅግ ውስብስብ የሆነ ደረጃ አንፃር ሁሉን-አቀፍ የሆነ አዲስ የሽግግር መንግሥት ከማቋቋም ባነሰ ሌላ ጥገናዊ ለውጥም ሆነ የጦርነት አማራጭ የመፈታት ዕድል የለውም። ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ አዋጪ አማራጭ ብሔርተኝነትና ጦረኝነት
አሸናፊ አመለካከት ሆነው በነገሱበት በአሁኑ ወቅት በቀላሉ ተቀባይነት ሊያገኝ እንደማይችል ግልፅ ነው። ሆኖም አይቀሬ የሆኑ አስገዳጅ ሁኔታዎች ተፈጥረው ጥያቄው ተቀባይነት
እስከሚያገኝ ድረስ የሚሆነውን ሁሉ በዝምታ ማየት የለብንም፡፡ ማለትም ከዋናው መፍትሄ በመለስ ያሉና መለስተኛ ውጤት ሊያስገኙ የሚችሉ ሌሎች የመፍትሄ ሃሳቦችንም ለማቅረብ መሞከር ጠቃሚና ተገቢ ይሆናል። ይህንን የዛሬውን ምክረ-ሃሳቤን ለማቅረብ የምሞክረውም
ከዚህ እሳቤ በመነጨ መሆኑን ለማስገንዘብ እወዳለሁ።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምትገኘው የወደፊት መፃዒ-ዕድሏን በሚወስን አደገኛ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው። ከመስቀለኛው መንገድ መካከል የመጀመሪያው ጦርነትን ወደ-ማሸነፍ፣ ሁለተኛው ጦርነትን ወደ-መሸነፍ፣ ሶስተኛው በተራዘመ የጦርነት ሂደት ወደ-መቀጠል፣
አራተኛው ጦርነቱን አቁሞ ወደ-ሰላማዊ የድርድር ሂደት ለመግባት የሚያስችል መንገድ ነው። ከእነዚህ አራት መንገዶች ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ሶስት መንገዶች የወቅቱን ችግር አጠናክረው የሚያስቀጥሉ የጥፋት መንገዶች ሲሆኑ ሀገሪቱን ከአጠቃላይ ውድመትና መፍረስ ለመታደግ
የሚያስችል ዕድል የሚፈጥርልን አራተኛው መንገድ ብቻ ነው። ወደዚህ መንገድ ለመግባት ግን ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ቅንነትና ዕውቀት ያለው፣ አርቆ-አሳቢና ሀገር ወዳድ የሆነ ብልህ እና ጠንካራ መሪ ያስፈልጋታል፡፡ ምክንያቱም ካለፈውና አሁን ከምንገኝበት አስቸጋሪ ሁኔታ በላይ የወደፊቱ የሀገራችን ሁኔታ የበለጠ በብዙ ፈተናዎች የተሞላ ስለሚሆን የጠንካራ አመራር መኖርን የግድ አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ሊባል በማይችል የምርጫ ሂደት ቢሆንም ብልጽግና ፓርቲ የዘንድሮውን ምርጫ አሸንፏል። ይህን ፓርቲ ብንወደውም ብንጠላውም ወታደራዊ አቅሙ እስከፈቀደለት ጊዜ ድረስ ዕድላችንን እየወሰነ በሥልጣን ላይ ይቀጥላል። ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ሶስት ዓመታት ካሳያቸው መሰረታዊ ድክመቶች ከልቡ ተምሮ የወቅቱን የሀገሪቱን ችግር ለመፍታት ከፈለገ መርህ-አልባ የሆነውን አካሄዱንና መዋቅራዊ የሆነውን የአመራር ሰጪነት ድክመቱን ወሳኝ በሆነ መጠን ማስወገድ ይኖርበታል።
ብልጽግና ፓርቲ በለመደው የሕገ-ወጥነት መንገድ አሁንም መቀጠል ካልፈለገ በስተቀር አዲስ መንግሥት ከመመስረቱ በፊት በቀሪዎቹ ሶስት ሳምንታት ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔውን ማካሄድ ይኖርበታል። ይህንን ጉባዔ ካካሄደም ከላይ የተጠቀሱትን ድክመቶቹን የመፍታትና አሁን ከሚገኝበት እንደሌለ ከሚያስቆጥር ድርጅታዊ ድክመቱ በተሻለ ተጠናክሮ የመውጣት ዕድል ሊያገኝ ይችላል። በዚህ ጉባዔም በሚከተሉት አራት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ለሀገሪቱ
የሚጠቅም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ሊይዝ የሚችልበት ዕድልም ሊፈጥር ይችላል።
እነዚህ አጀንዳዎችም፡-
 
1. የወቅቱን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዴት እናስቁመው?
 
2. ሀገሪቱን ከሻዕቢያ ጣልቃ-ገብነት እና ከሱዳን ወረራ እንዴት እንታደጋት?
3. ሀገሪቱን ከገጠማት አጠቃላይ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ችግሮች አውጥተን እንዴት አድርገን ወደዘላቂ የዴሞክራሲና የልማት አቅጣጫ እናስገባት?
4. ማንን የፓርቲያችንና የሀገራችን መሪ አድርገን እንምረጥ? የሚሉ ሊሆኑ ይችላሉ።
ከአንድ እስከ ሶስት የተጠቀሱትን አጀንዳዎች በተመለከተ ጉባዔው በቂ ውይይትና ግምገማ አካሂዶ የጠራ አቋም በመያዝ በየደረጃው ሊተገበር የሚችል ግልፅ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡ ጉባዔው በዚህ ረገድ ውጤታማ ከሆነ በፓርቲ ስም ጥቂት የፖለቲካ መሪዎች ያሻቸውን በመፈፀም በሀገር ላይ እየፈጠሩት ያለውን ችግር በተወሰነ ደረጃ ሊያቃልለው ይችላል፡፡ በአጠቃላይም ፓርቲው ካለፉት የሶስት ዓመታት ቅጥ-ያጣ አካሄድ በተሻለ የራሱን ውስጠ-ደንብና የሀገሪቱን ሕጎች አክብሮ የጋራ ውሳኔዎችን በተገቢው ጊዜና መዋቅር የመወሰንን አቅጣጫ መከተል ከጀመረ ኢትዮጵያን ከተጨማሪ ጥፋት የመታደግ አስተዋፅዖ ሊያበረክት ይችላል፡፡
በእኔ በኩል በዛሬው መጣጥፌ ላይ በተለየ ሁኔታ ላተኩር የፈለግሁት በቁጥር 4 ላይ በጠቀስኩት አጀንዳ ዙሪያ በመሆኑ በዚህ አጀንዳ ላይ ሊያዝ ይገባዋል ብዬ በማምንበት አቋም ላይ የግል አስተያየቴን ዘርዘር አድርጌ ለመስጠት ልሞክር። ባለፉት ሶስት ዓመታት በገሃድ ሲሆን እንደታየው በገዢው ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረው የሥልጣን ሽኩቻና ግብግብ ምክንያት ሕዝብ ከፍተኛ ተስፋ ጥሎበት የነበረው የለውጥ ሂደት እንዳይመለስ ሆኖ ከመክሸፉም በላይ ሀገሪቱ ወደለየለትና ዘግናኝ ወደሆነ የእርስ-በርስ ጦርነት ውስጥ ገብታለች። ኢሕአዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ጠብቆ በመቀጠል የጀመረውን የለውጥ ሂደት ውጤታማ ማድረግ ችሎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያና በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች በብዙ አስር ሺህዎች በሚቆጠሩ ዜጎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ
ማስቀረት በቻልን ነበር፡፡ ለዚህ ችግር መፈጠር ለረዥም ጊዜ ሲጠራቀሙ የቆዩና ተደማሪ የሆኑ የተለያዩ ምክንያቶችን መጠቃቀስ ቢቻልም የገዢው ፓርቲ መሪ ወይም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚና የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ በመሆኑ “የሚቀጥለው ጠቅላይ ሚኒስትር ማን
መሆን አለበት?” የሚለው ጥያቄ ወይም አጀንዳ የአንድ ፓርቲ ጉዳይ ብቻ ተደርጎ መታየት የለበትም። እጅ አውጥተን የመምረጥ መብት ባይኖረንም ጉዳዩ የጋራ ሀገራችንንና የእያንዳንዳችንን የዛሬና የነገ ህልውና የሚወስን በመሆኑ ሁላችንም በትኩረት ልንወያይበትና አቋማችንን ልንገልፅበት የሚገባ ነው።
በቀድሞዎቹ ንጉሣዊ ስርዓቶች፣ በደርግ፣ በኢሕአዴግም ሆነ በአሁኑ የብልጽግና ዘመን የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድም ጊዜ የሀገሩን መሪ በቀጥታ ምርጫ መርጦ የማያውቅ ቢሆንም ዕጣ-ፈንታውን በዋናነት ሲወስኑለት የኖሩት ግን የሀገር መሪዎች ናቸው። ለምሳሌ አሁን በሥራ ላይ ባለው የምርጫ ሕግ መሰረት ዶ/ር ዐቢይ አህመድን የመረጣቸው የአንድ ወረዳ ሕዝብ – ማለትም የበሻሻ ወረዳ ሕዝብ ብቻ ነው። የበሻሻ ሕዝብ ዶ/ር ዐቢይን የመረጣቸውም የሀገሪቱ መሪ እንዲሆኑ ሳይሆን ከሀገሪቱ 547 የፓርላማ አባላት መካከል አንዱ እንዲሆኑ ብቻ ነው። ነገር ግን ቀደም ሲል አባል የነበሩበት ኢሕአዴግ (ብልጽግና አይደለም) የፓርቲው መሪ እንዲሆኑ ስለመረጣቸው ብቻ እስካሁን ድረስ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን የገዢውን ፓርቲ አባላትና የበሻሻን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን 117 ሚሊዮን የሚገመተውን የሀገሪቱን ሕዝብ ዕጣ-ፈንታ የመወሰን ሥልጣን አግኝተዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ይህንን እውነታ በውል መገንዘብ ከቻለ ነው – በአንድ በኩል ስለሚመረጠው መሪ ሁላችንም ሃሳብ የመስጠት መብት ያለን መሆኑን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በፓርቲ ደረጃ እጅን አውጥቶ የሀገርን መሪ መምረጥ ከፓርቲ ጉዳይ በላይ የሆነ እጅግ ከፍተኛ ሕዝባዊ አደራ መሆኑን
መገንዘብና ኃላፊነቱን በዚያ ደረጃ መወጣት የሚችለው።
ይህ እንዲሆን ግን – በቅድሚያ የብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ የማካሄድን ጉዳይ ሀገሪቱን ከገባችበት የፖለቲካ ቀውስ የማውጣት ሙከራ ለማድረግ ያለው የመጨረሻ ዕድል መሆኑን በመገንዘብ ምንም ዓይነት ሰበብ ሳይፈጥር አዲስ መንግሥት ከማቋቋሙ በፊት ጠቅላላ ጉባዔውን በአስቸኳይ መጥራት ይገባዋል። ከዚህ በተጨማሪም በሀገሪቱ የፓርቲዎች የማቋቋሚያ ሕግ መሰረት (ምርጫ ቦርዱ ባይገደውም) ብልጽግና ፓርቲ መሪውን በጉባዔ ሳይመርጥ በመጪው የአዲሱ ፓርላማ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚንስትር በዕጩነት አቅርቦ
ማስመረጥ ስለማይችል ከመስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም በፊት ጠቅላላ ጉባዔውን ጠርቶ ሕጋዊ ግዴታውንና ፖለቲካዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አለበት፡፡ ሀገሪቱ በከፍተኛ ጦርነት ውስጥ መሆኗም ሆነ ሌላ ማንኛውም ዓይነት ሰበብ ጉባዔውን ላለመጥራት ምክንያት ሆኖ ሊቀርብ
አይገባም፡፡ ምክንያቱም ለምንገኝበት አስከፊ ጦርነትም ሆነ ለአጠቃላዩ የሀገሪቱ የፖለቲካ ችግሮች አዲስ መፍትሄ ለመሻት የጉባዔው መካሄድና ውጤታማ መሆን በራሱ የማይተካ ሚና ስለሚኖረው ነው። ጉባዔው ሲካሄድም፤ የፓርቲው መሪ እና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆነውን ሰው ለመምረጥ በሚቀርበው አጀንዳ ላይ ግልፅነትና ድፍረት ያለው ውይይትና ክርክር በማካሄድ የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስቀድም ታሪካዊ ውሳኔ ማሳለፍ አለበት። ከብሔርተኝነት፣ ከተረኝነት፣ ከቡድን ጥቅም እና
ከግለሰብ ጭፍን አምልኮ ነፃ በሆነ መንገድ ብቃት ያለው መሪ ለመምረጥ የሚያስችሉ ግልፅ ሳይንሳዊ የአመራር መመዘኛዎች አስቀድመው ተቀምጠውና በቂ ቁጥር ያላቸው ተፎካካሪ ዕጩዎች ቀርበውለት ጉባዔው የራሱ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑትን ሰው ሊመርጥልን ይገባል። የራሱንም ሆነ የሀገሪቱን መሪ የመምረጥ ሙሉና ብቸኛ መብት ያለው ብልጽግና ፓርቲ መሆኑ ግልፅ ቢሆንም ከላይ ከፍ ሲል ለመግለፅ እንደሞከርኩት በአሁኑ ወቅት የሚኖረን የሀገር መሪ የዛሬውንና የነገውን ህልውናችንን በመወሰን ረገድ የሚኖረው ሚና እጅግ ከባድና ከፍተኛ በመሆኑ በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ከፓርቲም ሆነ ከመንግሥት በላይ የሆነ በማንኛውም ጉዳይ ላይ ውሳኔ የመስጠት ድርሻ ያላቸው በመሆኑ እንደ አንድ ጉዳዩ የሚመለከተው የፖለቲካ ሰውም ሆነ ዜጋ ርዕሰ-ጉዳዩን በተመለከተ ያለኝን የግል አቋም
እንደሚከተለው ለመግለፅ እወዳለሁ።
በእኔ አመለካከት ብልጽግና ፓርቲ እንደተለመደው በፍርሃት፣ በአድር-ባይነትና በጭፍን የግለሰብ አምልኮ ካልታወረ በስተቀር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን የሀገሪቱ መሪ አድርጎ ለማስቀጠል የሚያስችለው ምንም ዓይነት የፖለቲካ፣ የሞራልም ሆነ የብቃት አመክንዮ ሊያቀርብ አይችልም።
ካለፉት ሶስት ዓመታት የአመራር ታሪካቸው በገሃድ ለመረዳት እንደምንችለው ዶ/ር ዐቢይ ከእንግዲህ ለብልጽግና ፓርቲም ሆነ ለኢትዮጵያ ዕዳ (Liability) እንጂ እሴት (Asset) የመሆን ዕድል የላቸውም። ከልምድም ሆነ ከእውቀት አኳያ ዶ/ር ዐቢይ ሀገሪቱን የመምራት ብቃት እንደሌላቸው የወቅቱ የሀገራችን እጅግ አሳሳቢ የሆነ ተጨባጭ ሁኔታ ምንም አከራካሪ ባልሆነ መጠን በግልፅ አሳይቶናል። እዚህ ላይ ዶ/ር ዐቢይ በአለፉት ሶስት ዓመታት ቤተ-መንግሥቱንና ቢሮአቸውን በጥሩ ሁኔታ ማሳደሳቸው፣ አራት ኪሎና እንጦጦ አካባቢ የመናፈሻ ፓርክ መገንባታቸው፣ ብዙ ቢሊዮን ችግኞችን በዘመቻ ማስተከላቸው፣ ከፕሬዚደንት ኢሳያስ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መፍጠራቸው፣ ብዙ እህቶቻችንን በሚኒስትርነት መሾማቸው፣ ደም ሲለግሱና ደካማ አዛውንቶችን ሲጎበኙ መታየታቸው፣ ሥልጣን በያዙ ማግስት የፖለቲካ እስረኞችን መፍታታቸው፣ በስደት ላይ የነበሩ
የፖለቲካ ድርጅቶችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረጋቸው፣ ኢሕአዴግን በብልጽግና ፓርቲ መተካታቸው፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ማዛወራቸው ወዘተ እና ከሁሉም በላይ ሕወሓት እና “ኦነግ ሸኔ”ን በሽብርተኝነት ፈርጀው ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት እየተዋጉ
መሆናቸውን እንደ ጠንካራ ጎን በመቁጠር በሥልጣን ላይ መቀጠል የሚገባቸው መሪ እንደሆኑ ተደርጎ በደጋፊዎቻቸው ዘንድ መከራከሪያ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ሆኖም በእኔ በኩል እነዚህ የዶ/ር ዐቢይ ክንውኖች ምን ያህል የአንድን ሀገር ጠቅላይ ሚኒስትር ጥንካሬ የሚያሳዩ ስለመሆናቸው ለመገምገምና ለመረዳት ባደረግሁት ሙከራ አጥጋቢ መልስ
አላገኘሁለትም፡፡ ይልቁንም ከእነዚህ ክንውኖች ውስጥ ከዘጠና-በመቶ በላይ የሚሆኑት ጉዳዮች ዶ/ር ዐቢይ ምን ያህል የጠቅላይ ሚኒስትርነት የስራ ድርሻቸውን በውል ያልተረዱና የሀገሪቱ መሰረታዊ ችግሮች በክብደት ቅደም ተከተል ምን ምን እንደሆኑ በውል መገንዘብ የተሳናቸው
መሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡ በእርግጥም ዶ/ር ዐቢይ አብዛኛውን ትኩረታቸውንና ጊዜአቸውን በምን ላይ ሲያባክኑ እንደሚውሉ ለምንታዘብ ሰዎች – ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩትን ሀገርና የሕዝቡን አንገብጋቢ ችግር ለይተው ያውቁታል? የሚል
ጥያቄ እንድናነሳ ያስገድደናል፡፡ እንዲያውም የአንድ ሀገር ስኬታማነት በሚለካባቸው ዋና ዋና መስፈርቶች መሰረት ለመመዘን ከሞከርን የዶ/ር ዐቢይን የአመራር ብቃት በብዙ ርቀት ከደረጃ በታች ሆኖ እናገኘዋለን።
በዶ/ር ዐቢይ የአለፉት ሶስት የአገዛዝ ዓመታት፡ –
1. ሀገራችን በብዙኃን የጋራ አስተሳሰብ በማይመራና ‘መሪ የመሆን መለኮታዊ ተልዕኮ አለኝ’ ብሎ በሚያምን ግብዝ መሪ እጅ በመውደቋ ወደ ዴሞክራሲ የመሸጋገር ዕድሏን አጥታለች፤
2. ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፋፋይ እና ፅንፈኛ በሆነ የብሔርተኝነት ፖለቲካ ውስጥ በመውደቋ የሀገር እና የሕዝብ አንድነቷ የመፈራረስ አደጋ ገጥሞታል፤
3. ሀገራችን በታሪኳ አይታው በማይታወቅ መጠን አውዳሚ የሆነ የእርስ-በርስ ጦርነትና እልቂት ውስጥ በመግባቷ ሰላምና መረጋጋት አጥታለች፤
4. ሀገራችን በሻዕቢያና በሱዳን መንግሥት ግዛቷ በመወረሩ ሉዓላዊነቷን አጥታለች፤
5. ዓለም ሀገራችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የቀጠናዊ ሰላም ስጋትነት ቋሚ አጀንዳው አድርጎ ሲነጋገርባት የሚውል ሀገር በመሆኗ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ክስረት ውስጥ ገብታለች፤
6. ሀገራችን ቀዳሚና ወቅታዊ ትኩረቷ በጦር መሣሪያ ግዢ እና በወታደራዊ ኃይል ምልመላና ስልጠና ላይ በመሆኑ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ክስረት ውስጥ ወድቃለች፤ በአጠቃላይና በአጭር አነጋገር በዶ/ር ዐቢይ እየተመራች ያለችው ሀገራችን በከፍተኛ ፍጥነት በመፈራረስ ላይ የምትገኝ የከሸፈች ሀገር ሆናለች። ሀገሪቱ ወደዚህ ዓይነቱ ሁለንተናዊ ጥልቅ ውድቀት ውስጥ ለምን እንደገባች በሂደት እየተጠራቀሙ የመጡ በርካታ ተደማሪ ምክንያቶችን መጠቃቀስ የሚቻል ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እንደ አንድ ራሱን ከፓርቲና ከመንግሥት ሚና በላይ አግዝፎ የሚያይ መሪ ለአለፉት ሶስት ዓመታት ያሳዩት የአመራር ድክመት የአንበሳውን ድርሻ የሚያስወስዳቸው ነው። ኢትዮጵያ በአመራር ድክመት ምክንያት ምን ያህል በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ ውስብስብና ጥልቅ ወደሆነ የህልውና አደጋ እንደገባች በገሃድ እያየን ከዚህ እውነታ በተፃራሪ አሁንም በተመሳሳይ አመራር እየተመራን ችግራችን ይፈታል ብለን የምንጠብቅ ዜጎች ካለን በማይጨበጥ የህልም ዓለም ውስጥ እየተጓዝን መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል።
የወቅቱ የሀገራችን ችግር በሰላምም ሆነ በጦርነት መንገድ መፈታት ይገባዋል ብለን የምናምን ዜጎች በጋራ ልንረዳው የሚገባ አንድ እውነታ ቢኖር በዶ/ር ዐቢይ ዙሪያ የሚታየው የአመራር ድክመት የሀገሪቱን ወቅታዊ ችግሮች በሰላምም ሆነ በጦርነት መፍታት የማይችልበት ተስፋ አስቆራጭ ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑን ነው። ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ በተደጋጋሚ ለመግለፅ እንደሞከርኩትና በተግባርም ሲሆን እንደታየው ኢትዮጵያ በዶ/ር ዐቢይ አመራር ከአንድ ቀውስ
ወደሌላ የባሰ ቀውስ የመሸጋገር እንጂ ለችግሮቿ መፍትሄ የማግኘት ዕድል አላገኘችም። የምናየው የአመራር ድክመት በዚህ ደረጃ የሚገለፅና ሀገሪቱን ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ባይሆን ኖሮ ዶ/ር ዐቢይ ከነድክመታቸው ለረዥም ጊዜ በሥልጣን ላይ ቢቀጥሉ ያን ያህል ባላሳሰበን ነበር፡፡ ነገር
ግን የእርሳቸው በሥልጣን ላይ መቀጠልና አለመቀጠል ከብሔራዊ ደህንነታችን ጋር እጅግ የተሣሠረ ጉዳይ ስለሆነ ጉዳዩን እንደ አንድ ግለሰብ ጉዳይ ቆጥረን በዝምታ ልናልፈው አንችልም፡፡ ይህንን እውነታ በመቀበል ከተቻለ ራሳቸው ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ዕጩ ተወዳዳሪ ሆነው ባለመቅረብ አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ሊያደርጉት እንደሞከሩት ራሳቸውን የሀገሪቱ የመፍትሄ አካል ቢያደርጉ ጥሩ ይሆናል። ዶ/ር ዐቢይ እውነተኛ ፍላጎታቸው ከግል
የሥልጣን ጥም እና ዝና በላይ ሀገርንና ሕዝብን ማገልገል ከሆነ በሌላ ውጤታማ ሊሆኑ በሚችሉበት የሥልጣን ቦታ ላይም ተመድበው አገልግሎታቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ። ይህን በማድረግም ራሳቸውን እንደ-ግለሰብ፣ ብልጽግናን እንደ-ፓርቲ፣ ኢትዮጵያን እንደ-ሀገር ከህልውና ጥፋት የሚታደግ አዲስ የተስፋ ጭላንጭል ሊያሳዩን ይችላሉ። ከወዲያኛው የዋሻ ጫፍ የብርሃን ብልጭታ በንግግር ሳይሆን በተግባር ሊያሳዩን የሚችሉት እንዲህ ዓይነቱን ከልቡ ሀገሩን ከሚወድ መሪ የሚጠበቅ ደፋር እርምጃ በመውሰድ ነው፡፡
እኔ የዚህ መጣጥፍ አቅራቢ በዶ/ር ዐቢይ ላይ ይህንን አስተያየት እንድሰጥ ያስገደደኝ በእርሳቸው ላይ የተለየ የግል ጥላቻ ኖሮኝ ሳይሆን ጉዳዩ የሀገር ጉዳይ ስለሆነና ማንኛውም ሰው በሆነ የታሪክ አጋጣሚ አሁን ዶ/ር ዐቢይ የሚገኙበት አጣብቂኝ ቦታ ላይ ቢገኝ ሀገሩን፣ ራሱንም ሆነ ልጆቹን ለመጥቀም ሲል የሚወስደው እርምጃ ሥልጣንን መልቀቅ እንደሚሆን ስለምገምት ነው፡፡ የእርሳቸው በሥልጣን ላይ መቀጠል ለሀገር ይጠቅማል ብዬ ባሰብኩበት ወቅትማ በሀገራችን እንዲቋቋም በመከርኩት የሽግግር መንግሥት ውስጥ እርሳቸው የሽግግር መንግሥቱ መሪ ሆነው እንዲቀጥሉ ሃሳብ አቅርቤ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ሆኖም የያኔውና የዛሬው የሀገራችን ሁኔታ በብዙ ርቀት የተለያየ ስለሆነና ስለ ዶ/ር ዐቢይ የነበረኝ አመለካከትም በእጅጉ የተለወጠ በመሆኑ የዛሬው የመፍትሄ ሃሳቤም በዚያው መጠን የተለየ ሊሆን ችሏል፡፡
እንደአለፉት አምባገነን መሪዎቻችን ዶ/ር ዐቢይም ይህንን ታሪካዊና ምናልባትም የመጨረሻ ዕድላቸውን ሊጠቀሙበት ካልቻሉ ግን በእሳቸው ላይ የመወሰን ሕጋዊ መብት ያለው ብልጽግና ፓርቲ ከርሳቸው የተሻለ መሪ በመምረጥ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል። ብልጽግና ፓርቲ እውነተኛ ድርጅታዊ ህልውና ያለውና ከግልና ከቡድን ጥቅም በላይ የሕዝብን አደራ የመወጣት ሚና ያለው ፓርቲ መሆኑን ማሳየት የሚችለው እንዲህ ዓይነቱን ደፋርና ተገቢ የሆነ ውሳኔ
መስጠት ሲችል ነው። ከዚህ ውጪ ብልጽግና ፓርቲ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ምንም ዓይነት ጉባዔ ሳያካሄድ፣ አመራሩንም በጉባዔ ሳይመርጥ የቀድሞውና ህልውናው ከስሟል የተባለው ኢሕአዴግ የመረጣቸውን አመራሮች ይዞ አዲስ መንግሥት ለማቋቋም የሚሞክር ከሆነ “ሕገ-ወጥ ነህ” የሚለው መንግሥታዊ አካል ባይኖርም እንኳ ሕዝባዊ ቅቡልነት ያለው ፓርቲ ሊሆን እንደማይችል መገንዘብ አለበት፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ከዶ/ር ዐቢይ የበለጠ ወይም የላቀ ግለሰብ በውስጤ አለ ብሎ የማያምን ከሆነም ቢያንስ የአቅሙን ውስንነት የሚያውቅና በጋራ ውሳኔ አሰጣጥ የሚያምን፣ የዜጎች መፈናቀልና እልቂት የሚያስደነግጠው፣ እውነትን የመናገር በጎ ስብዕና ያለው አዲስ መሪ በመምረጥ ለሀገሪቱ
የፖለቲካ ችግሮች የመፍትሄ አካል ለመሆን የሚያስችለውን የመጨረሻ ዕድል መሞከር ይኖርበታል። ብልጽግና በሕዝቡ፣ በተቀናቃኝ ኃይሎች እና በዓለም-አቀፉ ሕብረተሰብ ዘንድ የተሻለ ቅቡልነት አግኝቶ ዕድሜውን ማራዘም የሚችለውም ቢያንስ ይህንን አዲስና የተሻለ መሪ የመምረጥ ኃላፊነቱን በአግባቡ በመወጣት ነው። በሆነ ተዓምር ብልጽግና ፓርቲ የሀገሪቱን ችግሮች በወሳኝ ሁኔታ ወደመፍታት አቅጣጫ ሊሸጋገር ይችላል ብለን መጠበቅ አንችልም፡፡ ቢያንስ ግን ከላይ ለመጥቀስ የተሞከረው ዓይነት አዲስና የተሻለ መሪ በእውነተኛ የዴሞክራሲ አካሄድ በመምረጥ አውዳሚውን ጦርነት በሰላማዊ ድርድር ለመፍታትና የብዙ አስር-ሺህዎችን የሕዝብ እልቂት ለማስቀረት የሚያስችል አንድ ዕድል
ሊፈጥርልን ይችላል። ከሁሉም በላይ ብሔራዊ ደህንነታችን ዋስትና ሊኖረው የሚችለው ችግራችንን በብዙ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያባባሱት የመጡትን ዶ/ር ዐቢይን በመሪነት በማስቀጠል አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህ ላይ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገር ሉዓላዊነትና በጦርነት ሰበብ ሥልጣን ላይ ለረዥም ጊዜ መቀጠላቸው የኤርትራን ሕዝብ ምን ያህል መራር ዋጋ እንዳስከፈለው ልንማርበት ይገባል፡፡ ለሕዝብ የሚጠቅም እውነተኛ ስራ በመስራት እንጂ ማስፈራሪያ ጠላት እየፈጠሩና ሕዝብን ከሕዝብ እያዋጉ የሥልጣን ዕድሜን ለማራዘም መሞከር የስህተት ሁሉ ስህተት ነው፡፡
በመጨረሻም ይህንን ምክረ-ሃሳብ እያቀረብኩ ያለሁት ብልጽግና ፓርቲ በሆነ ተዓምር ተብትቦ ከያዘው የገነገነ መዋቅራዊ ድክመቱ ድንገት ተላቆ እንዲህ ዓይነት ትክክለኛ እርምጃ የመውሰድ ድፍረትና ፈቃደኝነት ይኖረዋል ብዬ የማመን የዋህነት ኖሮኝ አይደለም። ይልቁንም ይህንን
ማድረግ የፈለግሁት በአንድ በኩል እንደ አንድ ሰላማዊ የፖለቲካ ታጋይ እስከመጨረሻው ድረስ ከችግር ለመውጣት አለን ብዬ የማምንበትን አማራጭ ሃሳብ የመጠቆም ኃላፊነት አለብኝ ብዬ ስለምገነዘብ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዶ/ር ዐቢይም ሆኑ ሌሎች አንዳንድ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች
አዲስ ታሪክ የመስራት ተነሳሽነት እንዲኖራቸው የሞራል ግፊት ለማድረግ በማሰብ ነው። እነርሱ ቢቀበሉትም ባይቀበሉትም ተገቢውን ምክረ-ሃሳብ በተገቢው ጊዜ በዚህ መልክ ማቅረብ መቻል ፖለቲካዊና ታሪካዊ ፋይዳውም ቀላል አይመስለኝም፡፡ አንድ የሀገር መሪ ወይም ስርዓት በሀገር ላይ በቀላሉ የማይመለስ ጉዳት አስከትሎ ከሥልጣን ከወረደ በኋላ ወቀሳ ከማቅረብ ይልቅ ችግሩንና ድክመቱን እንዲያርም አስቀድሞ በተገቢው ጊዜ ማሳየት በሁላችንም ዘንድ መለመድ ያለበት ጥሩ ባህል ይመስለኛል፡፡ የሆነው ሆኖ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከዚህ የኔ አመለካከት በተለየ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመቀጠል ጠንካራ ፍላጎት ካላቸው (እንደሚኖራቸውም እገምታለሁ) ሕጋዊ ጉባዔ ተጠርቶ፣ በጉባዔው ላይ
በቂ ዕጩዎች ቀርበውና በቂ ውይይትና ክርክር ተካሂዶ፣ ከተቻለም ሂደቱ ለሕዝብ በግልጽ የሚታይበት ሁኔታ ተመቻችቶ መመረጥ ቢችሉ ለሂደቱም ሆነ ለእርሳቸው በእጅጉ ይጠቅማቸዋል የሚል አመለካከት አለኝ፡፡ በአጭሩ ለማለት እየሞከርኩ ያለሁት ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ
ሆነው እንደ ሌሎቹ የአፍሪካ አምባገነናዊ መሪዎች በጦርነት ወይም በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣኑንና ህልውናውን ከማጣት ይልቅ በራስ ወይም በፓርቲ ዴሞክራሲያዊ አሰራር በክብር ከሥልጣን መውረድ ወይም በሥልጣን መቀጠል የተሻለ ነው የሚል ነው፡፡ ከዚህ የተሻለ የወዳጅ ምክር ያለ አይመስለኝም፡፡
የርዕሰ-ጉዳዩን ወቅታዊነትና ጠቃሚነት የምትረዱ ሌሎች ወገኖችም በጉዳዩ ላይ በመወያየት የየራሳችሁን ግፊት ለማድረግ ብትሞክሩ ተገቢ ነው እላለሁ።
                     መልካም አዲስ ዓመት…!
                           ልደቱ አያሌው
                     መስከረም 1, 2014 ዓ.ም
Filed in: Amharic