>

በ«አንድነት» ጭምብል ተሸፍኖ ያለ የመርዘኛ ፖለቲካ የመጨረሻን ምእራፍ ማሳያ ነው (ወንድወሰን ተክሉ)

በ«አንድነት» ጭምብል ተሸፍኖ ያለ የመርዘኛ ፖለቲካ የመጨረሻን ምእራፍ ማሳያ ነው
ወንድወሰን ተክሉ

ክሱ በሁለት ግለሰብ መካከል የሚካሄድ ክስ ሳይሆን በለውጥ ፈላጊው ህዝብና በለውጥ አፋኙ ተረኛ ባለጊዜ መካከል የሚካሄድ ክስ ነው።
የቀድሞ የኢሳት ሳተላይት ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረው ጋዜጠኛ አበበ ገላው በባልደረባው ኤርሚያስ ለገሰ ላይ የከፈተውን ክስ ስንሰማ የሚታየን በርካታ እውነታዎች ጎልተው ይወጣሉ። ሁለቱ በአንድ ድርጅት ስር  ሆነው የወያኔን ስርዓት በመታገል የሚታወቁ ሰዎች እንደመሆናቸው መጠን ያየተሰለፉለትና የተሰባሰቡበት የትግል ዓላማ ማለትም የአንድነት ጎራው እንኩትኩቱ መውጣቱን የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን የተገነባበትም የድቡሽት ካብ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ጉዳዩን የበለጠ በስክነት እይን ስናየው በዚህ ወቅት የሀገራችን በርካታ አጀንዳዎች የህዝባችንን አይንና ቀልብ መያዝ በቻሉበት ወቅት የአበበ ገላው በኢትዮ360ሚዲያው ኤርሚያስ ላይ የከፈተው ክስ አግባብና ተገቢ ነው ብለን ስንመለከት የክሶቹ ጭብጥ የሚያሳዩን ሀቅ ግለሰቡ ማለትም አበበ ገላው ተበድሎ የመሰረተው ክስ ሳይሆን ለሌሎች ሀይሎች (አቢይ መራሹ ብልጽግና እና የለውጥ ድምጽ አስተጋቢው ኢዜማም ጭምር) ብሎ የከፈተው ክስ ሆኖ እናገኘውና የክሱ መሰረታዊ ዓላማ ኤርሚያስንና ኢትዮ360ሚዲያን ዛሬ ከሚያስተጋቡት ሀገራዊ አጀንዳ ላይ ማፈናጠር ሆኖ ይታየንና አጠቃላይ የክሱን መሰረተ ሀሳብ ፍትሃዊ ያልሆነ ብቻ ሳይሆን ሴራዊ የሆነ መርዘኛ ክስ መሆኑን ማየት እንችላለን።
ይህ ሁኔታም ነው የሁለቱ ሰዎች የፍርድ ቤት ሙግት በሁለቱ መካከል ብቻ የሚካሄድ የግለሰቦች ክስ ሳይሆን በእኛ (ሰፊው ህዝብ ማለቴ ነው) በእውነተኛ ለውጥ ፈላጊ ኋይሎችና በጸረ ለውጥ ተረኛ ኋይሎች መካከል የሚካሄድ የክስ ሙግት ነው ለማለት ያስቻለን።
፠ የአበበ ገላውን ክስ ጭብጥ ስንመለከት፦
፨ 1ኛ- በሰኔ 2018 ላይ ኤርሚያስ ለገሰ በኢሳት ቴሌቪዥን ባስተላለፈው ምስል የኦሮሞን ህዝብ የሚጎዳ በመሆኑ ኢሳት እንደተቌም የተጎደበትን ድርጊት በመፈጸም እኔ አበበ ገላውን የመላው ኦሮሞ ጂሃድ እንዲታወጅብኝ በማድረጉ እስከዛሬ በነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ፍርሃታዊ ጭንቀት ውስጥ እንድገባ ያደረገ በደል ፈጽሞብኛል።
፨ 2ኛ – በመጋቢት 2019ላይ ኤርሚያስ በኢሳት ቴሌቪዥን ላይ በምስጢር ተቀርጾ የተቀመጠን የአቢይ አህመድን የኢንሳ ውስጥ ምስጢራዊ ስራን በድንገት ለህዝብ ይፋ በማድረጉ ህይወቴን ለአደጋ በማጋለጥ ከባድ በደልና ጥፋት ፈጽሞብኛል።
፨ 3ኛ- በመስከረም 2020 ላይ ኤርሚያስ በኢትዮ360ሚዲያ በኢሳት ኤዲቶሪያል ቦርድ እንዳይተላለፍ ታግዶ ያለውን የአቢይን የኢንሳ ውስጥ ስራን የሚገልጸው ምስጢራዊ ድምጽ እንድለቅ በመጠየቁ እኔን የጭንቀት ቅርቃር ውስጥ  አስገብቶ በፍርሃት ርጄ ተንቀጥቅጬ እንድደበቅ አድርጎኛል።
፨ 4ኛ- ኤርሚያስ በትራንስፖርት ምኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ጉዳይ ላይ የሰጠሁትን የትምህርት ማስረጃ ባለመጠቀሙ በደል ፈጽሞብኛል
፨ 5ኛ- ኤርሚያስ ለገሰ የአቢይ አህመድን የትምህርት ደረጃን አዛብቶ በማቅረብ ከፍተኛ የሆነ የጭንቀት በደል ፈጽሞብኛል የሚሉ አይነት ክሶች ናቸው አጅሬ አበበ ገላው በኤርሚያስ ለገሰ ላይ የከፈተው የክስ ጭብጥ ሲታይ።
እዚህጋ ልብ ብለን ማየት ያለብን አምስቱንም ክሶች ኤርሚያስ ለገሰ ሙሉ በሙሉ ፈጽሟቸዋል ብለን ብንቀበል የአምስቱም ክስ ከሳሾች ፦
1ኛ- የኦሮሚያ መንግስት
2ኛ -አቢይ አህመድና እሱ የሚመራው የብልጽግና መንግስትና
3ኛ- ኢሳት መሆን ይገባቸዋል እንጂ አንድ የኤርሚያስ ለገሰ የቀድሞ የስራ ባልደረባ ምን አግብቶት ነው በእነዚህ አምስት የክስ ጭብጦች ምክንያት የ950,000$ ዶላር ካሳ ይገባኛል ብሎ ለመክሰስ የቻለው ብለን ስንጠይቅ ነው በአጠቃላይ የዚህን ክስ ሂደት በአንድ አበበ ገላውና በቀድሞ ባልደረባው ኤርሚያስ ለገሰ መካከል የሚካሄድ የፍርድ ሙግት ሳይሆን በአንድ እራሱን በህወሃት እግር ተክቶ አንዳችም ስርዓታዊና ህገመንግስታዊ ለውጥ ሳያመጣ እራሱን የለውጥ ሃዋሪያ አድርጎ በተነሳው ናርስሲስቱ ፋሺስቱ አቢይ መራሹ ተራኛ ቡድን በአንድ ጎራ ሆኖ በሌላ ጎራ ደግሞ ለትክክለኛ ለውጥ እየታገለ ባለው ሰፊው የኢትዮጲያ ህዝብ መካከል እየተካሄደ ያለ ሙግት መሆኑ የሚገባን።
ይህ ክስ ከይዘቱ እስከ አጠቃላይ የተከፈተበት ወቅት ሲታይ መቶ በመቶ ተረኞቹ የኦሮሙማ ኋይሎች ከአጋሮቻቸው ጋር ሆነው የለውጥ ፈላጊውን ኋይል ለመድፈቅ የከፈቱት ዘመቻ መሆኑን የሚያስረዳ ሲሆን በተጨማሪም ኤርሚያስም ሆነ ኢትዮ360ሚዲያ እንደተቌም በአማራ ጉዳይ ላይ እያስተጋቡት ያለው ነባራዊ ሀቅ ይህንን አይነቱን ክስ ሊያስከፍትባቸው የቻለ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ በአጽንኦት የምንገልጸው እውነታ ነው።
፠ የአበበ ገላው ክህደታዊ ጥግ ምንጭና መንስኤስ ምንድነው ??
ለመሆኑ አበበ ገላው በዘረዘራቸው አምስት ክሶች ውስጥ በቀጥታ እሱን ማለትም ህይወቱ ላይ ያስከተሉት ጉዳትም ይሁን ጥፋት አለ ወይ ብለን ስንመረምር ከላይ እንዳሰፈርኩት አምስቱም ክሶች ስለሌላ ሁለተኛ ኋይል የሚዘበዝብ ከመሆኑ ባሻገር ግለሰቡ (አበበ በለው ማለቴ ነው) የጭንቀት ሰለባ ሆኛለሁ ከሚለው በስተቀር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የደረሰበት ነገር እንደሌለ በግልጽ ያሳያል።
ለምሳሌ ያህል ኤርሚያስ ስለአቢይ ትምህርት ማስረጃ ስለኢንሳው ምስጢራዊ ድምጽና ስለዳግማዊት ሞገስ የትምህት ማስረጃ ዋሽቶ እና አዛብቶ የሀሰት መረጃ  አስተላልፏል  ብለን ብንቀበል ይህ ዘገባ ታዲያ አቢይንና ዳግማዊትን የሚመለከት እንጂ አበበ ገላውን የሚመለክት አስጭንቆ የሚያኮሰምን እንዴት ሊሆን ይችላል? ወይንስ አበበ ማለት አቢይ አቢይ ማለት አበበ ማለት ተብሎ ካልተገለጸ እንዴት ሆኖ ነው ቦጅቧጃው አበበ በሰው ጉዳይ ላይ ጭንቀት ውስጥ ስለገባሁ ካሳ ይሰጠኝ ብሎ ሊነሳ የቻለው ብለን እያንዳንዳችን መጠየቅ ይገባናል።
የአበበ ገላው እርምጃ ሳር ሳሩን እያየ ገደል ከገባው በሬ ታሪክ ጋር ይመሳሰልብኛል። አጅሬው ታገኛለህ ተብሎ ከተነገረው ይፋዊው 950,000$ ገንዘብ ውጪ  ለክሱ ስራ ማስኬጃና ሞራል መጠበቂያ ተብሎ የተሰጠውን ገንዘብ ብቻ በመመልከት እራሱ ተሸናፊ ሆኖ በታላቅ ውርደትና ቅሌት ሰለባ በሚሆንበት የክስ ድራማ ላይ የዋና መሪ ተዋናይነቱን ሚና ልጫወት ብሎ በመስማማት በጣም ሲያከብረው በነበረው በስራ ባልደረባው ላይ ክስለመመስረት የተረኞቹ መጠቀሚያ እቃ (ኮንዶም) ሆኖ ብቅ ማለቱን ነው በተጨባጭ ሁኔታ ማረጋገጥ የሚቻለው።
ለመሆኑ አበበ ገላው በራሱ ሀሳብ አስቦ አውጥቶ አውርዶና ከመሰል ጔደኞቹ ጋር መክሮበትና ዘክሮበት በራሱ ግልገንዘብ አውጥቶ ይህንን ክስ ከፍቷል ብላችሁ የምትገምቱና የምታስቡ የዋኋን አላችሁን??
ይህንን ሀሳብ እርግፍ አድርጋችሁ እርሱት። ከሀሳብ ጀምሮ እስከ ገንዘብ ድረስ ያለውን ሙሉ አጀንዳ አሽሞንሙኖና አዘጋጅቶ ያቀረበለት በአምስቱም ክሶች ሙሉ በሙሉ ስሙ ተጠቅሶ ተጠያቂ ከሆነውና ስሙም ስያጠቀስ በተዘዋራሪ ተጠያቂነቱ እሱ ላይ የሚያነጣጥረው አቢይ አህመድ አሊ በኩል ታስቦና ተወስኖ የተላከለት አጀንዳ ሲሆን በአበበ በኩል ያለው ሚና ግን የዚህ ተልእኮ ዋና ባለቤት መስሎ በመቅረብ በግንባር ቀደምትነት ጉዳዮን ለማንቀሳቀስ መስማማቱ ላይ ብቻ ነው እንጂ  ጉዳዩ ከ«ሀ» እስከ «ፐ» የአምስቱም ክስ ዋና ባለቤት የሆነው የአቢይና ግብረአበሮቹ ሀሳብና ውሳኔ ነው።
በእርግጥ እዚህ ላያ የአበበ ገላውን እጅግ የወረደና ለሰው ያውም ለባለጊዜ ጨቌኝ ተረኛ ቡድን ሙሉ በሙሉ መጠቀሚያ እቃ መሆን ደረጃ ላይ የሚያደርስ ስብእና እንዳለው እራሱን ያጋለጠበት የመሆኑም ጉዳይ ሊሸሸግ እማይገባ ሀቅ ነው።
አበበ ገላው ከኤርሚያስ አቌሞች ጋር ፈጽሞ የማይቀራረብ አቌም ሊኖረው ይችላል። ይህም ተፈጥሮአዊ ስለሆነ የሚጠበቅና ፈጽሞም እንደችግር የሚታይ አይደለም። አበበ ገላው በዚህ በኤርሚያስ ለገሰ አዳዲስ አቌሞች የቱንም ያህል ባይስማማና ቢበሳጭም ግን ቅሉ የኤርሚያስ ለገሰ እያንዷንዷ ስራ ጸረ አበበ ገላው ሳይሆን ጸረ ጨቌኝ ጸረ ሀሰት ጸረ ኢ-ፍትሃዊነት ላይ ያነጣጠረ ስራ ሆኖ ሳለ እንዴት ሆኖ ነው አንድ አበበ ገላው የመንግስት ህጋዊ ቃል አቀባይ ያልሆነ ወይም የመንግስት ውክልናን በይፋ ያልተቀበለ ሰው ስለመንግስት ጥፋት በተዘገበ ዘገባ ላይ -የተላለፈው ዘገባ እውነትና ፍትሃዊ ነው አይደለም ውስጥ ስይገባ- ተመርኩዞ ልክ በግል እሱ ላይ ያነጣጠረ የስም ማጥፋት ዘገባ ነው የቀረበብኝ ብሎ ክስ ሊመሰርት ይችላል??
ኤርሚያስ ለገሰ በምን መልኩ ነው የአበበ ገላውን ስም ያጠፋው ?? ወይንስ የአቢይ ስም መጥፋት የአበበ ገላው ስም መጥፋት ነው የተባለውስ መቼ ነው??
ዛሬ አበበ ገላው በባልደረባው ኤርሚያስ ለገሰ ላይ የከፈተውን ባለአምስት ነጥብ የስም ማጥፋት ክስ ጭብጥ ዝርዝሩን ስንመለከትና እራሱ አበበ ገላው ለዓመታት ታግዬለታለሁ የሚለንን የትግሉን ዓላማና መንስኤን  በንጽጽር ስንመለከት ክሶቹ እውነተኝነት እንኴን ቢኖራቸው የሚያመላክቱት በስርዓቱና ስልጣን ላይ ባለው ተረኛው መንግስት ተብዬው ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውን ያሳዩናል እንጂ አንድ ተራ ጅላንፎ አበበ ላይ ያነጣጠሩ አለመሆናቸውን ስንመለከት የአበበ ገላውን ክስ ግላዊ ክስ ሳይሆን አቢያዊ ክስ መሆኑን እና ለዚህም ህሊና ቢሱና ማስተዋል የተሳነው አበበ መጠቀሚያ መሆኑን ነው ማወቅና መረዳት የሚቻለን።
አበበ ገላው በታዋቂው ጀግናችንና ምሁሩ ፕ/ር አስራት ወልደየስ ግድያ ላይ ያለውን ሚና ሳያጠራና ብሎም እሱም እስከዛሬ በአማራ ጉዳይ ላይ ትንፍሽ ብሎ ሳይናገር ዛሬ ይባስ ብሎ የአማራው፣የአዲስ አበቤውና ብሎም በአጠቃላይ የሀገረ ኢትዮጲያ ህልውና ድምጽ ለምን ሆናችሁ በተባሉት የኢትዮ360ሚዲያና  በኤርሚያስ ላይ አጀንዳ የሚያስቀይርን መንግስታዊ ጥቃት ዋና መሪና አስፈጻሚ ሆኖ ብቅ ማለት በዝምታ የማይታለፍ ቀይ መስመር ማለፉን ሁላችንም በግልጽ ቌንቌ ልንነግረው ይገባል።
አበበ ገላው ስለአማራውና በአጠቃላይ ስለተጨቆኑ ኢትዮጲያዊያን ድምጽ የሆኑትን ኤርሚያስ ለገሰን ጨምሮ አጠቃላይ ኢትዮ360ሚዲያን ለመክሰስ መጠቀሚያ መሳሪያ ከመሆኑ በፊት እሱ እራሱ ስለአማራና በግፍ ስለተጨቆኑ ኢትዮጲያዊያን ጉዳይ መጀመሪያ ድምጹን ማሰማት ይጀምር።
በእርግጥ ለአቤ እሚታየው ልክ እንደ በሬው ሳር ሳሩ እንጂ ገደሉ አይታየውምና የአማራ ህዝብ ስቃይ የእነእስክንድር አይነቱ የህሊና እስረኞች ጉዳይ ፈጽሞ አይታየውምና ይህንን አይነቱን self ceneterd ግለሰብ
ለግል ጥቅማቸው ብለው የሀገርና የህዝብን ህልውናዊ ጥቅም የሚሸቅጡትን ተጠይፈን ማራቅና ብሎም ማውገዝ አለብን።
ሀገራችንና ህዝባችን በዚህ አስጨናቂ ሰዓት የግል ኢጎን ማሳጅ እንዲደረጉ ለሚቃትቱ ሀሳበ ድኩማኖች ቦታ የላትም።
በአጠቃላይ ክሱ በአንድ አበበ ገላውና በአንድ ኤርሚያስ ለገሰ መካከል የሚካሄድ ሙግት ሳይሆን በአንድ ጸረ ለውጥ ኋይልና በእኛ (በለውጥ ፈላጊው ህዝብ)መካከል የሚካሄድ መሆኑን አውቀን ሁለንተናዊ ድጋፋችንን በኤርሚያስና በኢትዮ360ሚዲያ ጋር በማድረግ ይህንን የተረኞችን አይን ያወጣን ዘመቻን መስበር ይገባናል።
Filed in: Amharic