>

"የነውጡ መንግሥት" በድሬዳዋ ያመጣው "ለውጥ" (አቻምየለህ ታምሩ)

የነውጡ መንግሥት” በድሬዳዋ ያመጣው “ለውጥ”

አቻምየለህ ታምሩ

 

*… የነውጡ መንግሥት”ከሁለት ቀናት በፊት የተመሰረተው የዐቢይ አሕመድ የድሬዳዋ አስተዳደር የነበረውን የፋሽስት ወያኔን የአፓርታይድ ቀመር “በማሻሻል” የአፓርታይድ ቀመሩን ወደ 50-40-10 ከፍ አድርጎ በመስቀል የአፓርታይዱን ክብረ ወሰን ተቀዳጅቷል
ፋሽስት ወያኔ ድሬዳዋን ይገዛባት የነበረው የአፓርታይድ ቀመር 40-40-20 ነበር። በዚህ የፋሽስት ወያኔ የአፓርታይድ ቀመር ከ65% በላይ የሚሆነው የከተማው ሕዝብ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የነበረው ድርሻ 20% ሲሆን ከ30% በታት የሚሆነውን የከተማውን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉት እነ ኦሕደድ እና ሶኢዴፓ ግን የከተማ አስተዳደሩን 40% – 40% ተጫርተውት ነበር።
በነውጡ መንግሥት ከሁለት ቀናት በፊት የተመሰረተው የዐቢይ አሕመድ የድሬዳዋ አስተዳደር የነበረውን የፋሽስት ወያኔን የአፓርታይድ ቀመር “በማሻሻል” የአፓርታይድ ቀመሩን ወደ 50-40-10 ከፍ አድርጎ በመስቀል የአፓርታይዱን ክብረ ወሰን ተቀዳጅቷል። የነውጡ መንግሥት በፋሽስት ወያኔ ዘመን የነበረውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 40-40-20 የአፓርታይድ ቀመር  ወደ 50-40-10 በመለወጥ በአፓርታይድ አጋዛዝ ፋሽስት ወያኔን አስንቆታል።
ባጭሩ መጣ በተባለው ለውጥ “የለውጡ መንግሥት” ፋሽስት ወያኔ ለከተማው ሕዝብ ከወሰነው 20% ድርሻ ላይ 10%ቱን ነጥቆ ድርሻውን ወደ 50% ከፍ ሲያደርግ ሶኢዴፓ የነበረውን 40% ድርሻ አስጠብቆ ሲቀጥል ሕዝቡ ግን በፋሽስት ወያኔ ዘመን ከተፈቀደለት ድርሻ ግማሹን አጥቶ ድርሻው ከ10% በታች እንዲሆን ተወስኗል።
Filed in: Amharic