>
5:13 pm - Saturday April 18, 5807

አታጭበርብር...!!!! (ኤርሚያስ ለገሰ)

አታጭበርብር…!!!!

ኤርሚያስ ለገሰ

*…. አንድ አመት ሙሉ ውስጥ ለውስጥ የምትሰራውን ሰርተህ፤ ዓብይ አህመድ “መንግስት መስርቷል፣ የሚነቀንቀው የለም” ብለህ ስታስብ ጥገናዊ የፕሮፓጋንዳ አቅጣጫ ልትቀይር ስትወስን እስክንድርን መናጆ ልታደርገው መጣህ። እስከዛሬ የት ነበርክ ብትባል መልስህ ምን ይሆን? አዎ እንጠይቅሃለን… አንድ አመት ሙሉ የት ነበርክ?
1) እነ እስክንድር ነጋ የወንጀል ሳይሆን በዓብይ አህመድ በአደባባይ “ግልፅ ጦርነት” የታወጀባቸው የግሉ የሕሊና እስረኞች ናቸው። ወንጀለኛው አንተ ተደግፈህ የተደመርክበት ድፍን ዓለም ያወቀው፣ አጭበርባሪ፣ ውሸታም፣ ፀረ-ኢትዮጵያው ዓብይ አህመድ እንጂ እነ እስክንድር ነጋ አይደሉም! … አታጭበርብር!
2) እነ እስክንድር ነጋ የአዲስ አበባ ህዝብ መከራውን ሲበላ የግንባር ስጋ ሆነው በመታገላቸው ምክንያት በተረኞች ውሳኔ እግረ ሙቅ የጠለቀባቸው የፓለቲካ እስረኛ የሆኑ ናቸው።…አታጭበርብር! ንገሩኝ ባይ አትሁን!
3)  እነ እስክንድር ነጋ ተረኛው ያሰማራቸው ኃይሎች የእምነት ተቋማትን በማፍረስ አዲስአበቤን በመከፋፈል የማያባራ የሐይማኖት ግጭት ሊፈጥሩ ሲሉ ቀድመው በማንቃታቸው በዓብይ አህመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የሕሊና እስረኛ የሆኑ ንጽሃን ናቸው።… አታጭበርብር!
4) እስክንድር እንዲታሰር ያላለውን አለ በማለት አጣመህ ስትናገርና ለተረኞቹ ቅቤ የጠጣ ዱላ ስታቀብል ኖረህ ዛሬ “ፍትሕ ዘገየ” ብለህ የምታነሳበት ሞራል የለህም።…እናም አታጭበርብር!
5)  አንድ አመት ሙሉ ውስጥ ለውስጥ የምትሰራውን ሰርተህ፤ ዓብይ አህመድ “መንግስት መስርቷል፣ የሚነቀንቀው የለም” ብለህ ስታስብ ጥገናዊ የፕሮፐጋንዳ አቅጣጫ ልትቀይር ስትወስን እስክንድርን መናጆ ልታደርገው መጣህ። እስከዛሬ የት ነበርክ ብትባል መልስህ ምን ይሆን? አዎ እንጠይቅሃለን… አንድ አመት ሙሉ የት ነበርክ? የቤተ መንግስት ብቅል ስትፈጭ? … እናም አታጭበርብር!
6) የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጫፍ እስከ ጫፍ የሕሊና እስረኞች ይፈቱ ብሎ በመነቃነቁ ምክንያት አፍረህ የጣትህን ጥፍር ማስነካትህ የማይታወቅብህ ከመሰለህ ተነቅቶብሃል።…እናም አታጭበርብር!
ቢያንስ አዲስአበቤዎች መሆናችንን አትርሳ!
Filed in: Amharic