>
5:18 pm - Friday June 15, 3049

ያልፈረሰችዋ የዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ የትኛዋ ናት..  ???? አቻምየለህ ታምሩ

ያልፈረሰችዋ የዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ የትኛዋ ናት..  ????
አቻምየለህ ታምሩ

ፋሽስት ወያኔ ከትግራይ ተምቤን በረሀ ተነስቶ አሸንጌን ተሻግሮ ወሎን አቋርጦ ሸዋን በመውረር ማጀቴ ውስጥ ከናዚ ኦነግ ጋር የዘር ፍጅት እያካሄደ ዐቢይ አሕመድ ግን አራት ኪሎ ተቀምጦ ኢትዮጵያ አትፈርስም ይለናል። እናቶቻችን፣ እኅቶቻችን፣ አያቶቻችና ልጆቻችን በፋሽስት ወያኔ ወራሪ አንበጣ አራዊት  በግፍ የተደፈሩባቸው፤ ንጹሑን ወጣቶች፣ ገበሬዎችና ሰርቶ አዳሪዎች በማንነታቸው ምክንያት ቤታቸው ውስጥ በተቀመጡበት ከትግራይ በመጡ ግፈኛ ወራሪዎች ቤት ለቤት እየታደኑ  የተፈጁባቸው፤ ከተሞችና ኢንዱስትሪዎቻቸው ከትግራይ በመጡ ወራሪዎች ተዘርፈው የተረፈው የወደሙባቸውና በሕይዎት የተረፉት ግፉሐን ደግሞ  የሚደርስላቸው አገርና መንግሥት አጥተው በፋሽስት ወያኔ ወራሪ አንበጣ ሠራዊት ስር በየዕለቱ የስቃይና የመከራ ኑሮ የሚገፉባቸው ወሎ፣ አፋር፣ ሰሜን ጎንደርና ሰሜን  ሸዋ ኢትዮጵያ አይደሉም? ያልፈረሰችዋ የዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ የትኛዋ ናት? ለወሎ፣ ለጎንደር፣ ለአፋርና ለሰሜን ሸዋ ሰዎች አገርና መንግሥት አላቸው? ዐቢይ አሕመድ በየዕለቱ እየፈረሰች ያለችዋን ኢትዮጵያን አትፈርስም የሚላት ከዚህ በላይ እንዴት ሆና እንድትፈርስለት ፈልጎ ነው?

Filed in: Amharic