ድርድሩ ለኦሮምያ ሪፓብሊክ ምሥረታ ዋነኛው ግብኣት ነው!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ከሰሞነኛ ወሬዎች አንዱ በትግርኛ ሥነ ቃል “ዝአኽለን ጥኽነን በዓል ማርያም ትብላ” በሚባለው ምሣሌያዊ አነጋገር ሊገለጽ የሚችለው የሁለቱም የአማራና የኢትዮጵያ ጠላቶች ማለትም ምዕራባውያን መራሹ ትህነግና አቢይ መራሹ ኦነግ/ኦህዲድ ብል(ጽ)ግና ታላቅ ሤራ ገሃድ የወጣበት የድርድር ጉዳይ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ ብልጽግና የሚባል ፓርቲ አለ ብዬ አላምንም፡፡ ፓርቲ ተብዬው መመሥረቱ ቀደም ሲል በሚዲያ ከመነገሩ በስተቀር አንድም የፓርቲ ጠባይ አሳይቶን ስለማያውቅ የአንድ አባጨቡዴ ግለሰብ መሣሪያ እንጂ በፓርቲ ስም መጠራት የሚያስችለው አደረጃጀት በጭራሽ የለውም)፡፡ ይህ ድርድር በማንና በማን መካከል እየተካሄደ እንደሆነም የወሬ ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡ ውስጥ ለውስጥ እየተካሄደ ነው በሚባለው በዚህ ድርድር የጥቃቱ የመጀመሪያ ሰለባዎች የሆኑት የአፋርና አማራ ክልሎች የሉበትም – ማን እንደሰው ቆጥሯቸው! አሉበት ቢባልም እንኳን በተለይ የአማራው ክልል አማራን የሚወክል አስተዳደር ቀድሞውንም የሌለው በመሆኑ አማራን እንደወከሉት ተቆጥሮ በአቢይ ብልግና ፓርቲ ስለአማራ እንደአማራ ሆነው ድርድሩን ዳር ቆመው እንዲከታተሉ የተፈቀደላቸው እነአባ መሸ በከንቱ ደመቀ መኮንንና ተመስገን ጥሩነህ እንደሆኑ ተገልፆኣል፤ እነዚህ ደግሞ ለመጣ ለሄደው ሁሉ ደምበኛ የጭነት መጋጃ እንጂ እንደሰውም ሊቆጠሩ የሚገባቸው አይደሉም፡፡ እነዚህን መሰል ማይማን የብአዴን አመራሮች የሰጡትን መቀበል ከሚያስችል ሆድ ውጪ ማሰብ የሚችል ጭንቅላት አልፈጠረባቸውም፡፡ ይህ ድርድር ምናልባት ለኢትዮጵያ ነጻነት የመጨረሻው ምዕራፍ ሊሆን ይችላል ብዬ በበኩሌ እገምታለሁ፡፡ ምክንያቱም ስንጠብቀው የነበረው የነአቢይ ሤራና ተንኮል በይፋ ተገለጠ እንደማለት ነውና፡፡ አማራን ካስፈጁና ሀብት ንብረቱን ካስዘረፉ በኋላ ድርድር ውስጥ መግባት ተጨፈኑ ላሞኛችሁ ዓይነት የጅሎች ፈሊጥ ነው – ይህ ደግሞ የማይጠበቅ አልነበረም፡፡ ችግራችን በድርድር ቢፈታ ኖሮ ጥቅምት 24/2013 በወታደራዊ መኮንኖችና በወታደሮች ላይ የደረሰው ጥቃት አይደርስም ነበር፡፡ ችግራችን በድርድር ቢፈታ ኖሮ ወያኔና ትግራይ ላይ የደረሰው ዕልቂትና ያንንም ተከትሎ አማራና አፋር ላይ የተከሰተው ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ የንብረት ዘረፋና ውድመት እንዲሁም የእንስሳትና የእህል ቃጠሎ አይደርስም ነበር፡፡ አሁን ሁለቱም ወገኖች በተለይ በአማራ ላይ የፈለጉትን ያህል ጥፋትና ዕልቂት ካደረሱ በኋላ እንደራደር ቢሉ የሚሰማቸው የለም፤ መጥኖ መደቆስ ቀድሞ ነበር፡፡ ይህ ድርድር ብአዴንንም ብልጽግናንም ወያኔንም እንዲሁም መላውን የኢትዮጵያ ጠላት እንደጎርፍ ጠራርጎ በማስወገድ ኢትዮጵያን በደርግኛ አገላለጽ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነፃ የሚያወጣ ትልቅ ምልክት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ይቺ “ድርድር” የምትባል የቀጣፊዎችና የመሠሪዎች የመጨረሻ ካርድ ለማንም ግልጽ ናት፡፡
አጭሩን ልንገርህ ወንድሜ፡፡ የኢትዮጵያ ችግር ከድርድር በላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በደም እንጂ በንግግር የሚፈታ ችግር የላትም፤ መጽሐፉም “ደም ትነጽሕ በደም” ይላል፡፡ ባለፉት ሃምሣ ዓመታት የተዘራው የቂም በቀልና የጥላቻ ዘር በቅሎና ጎምርቶ አገር ምድሩን እያነደደ ባለበት ሁኔታ ድርድር ማንሳት ፋይዳው ጥላቻና ቂም በቀሉን ለዘሩት ከይሲዎች እንጂ ተጎጂዎችን በፍጹም ሊጠቅም አይችልም፡፡ እንዲያውም ለጠላቶች ፋታ በመስጠት የአማራ ጄኖሳይዳቸውን አሻሽለውና አዘምነው እንዲመጡ ዕድል ያመቻችላቸዋል፡፡ አማራው ማድረግ ያለበት ለመቶዎችና ለሽዎች ዓመታት ወግጦ የያዘውን የጠላት መጥፎ አስተሳሰብ ከሥሩ ነቃቅሎ መጣል ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ በቀጣይ ዘመናት የኅልውናው ሥጋት እንዳይሆን ማድረግ ይኖርበታል፡፡ እንደወትሮው ተዋደውና ተፋቅረው በጋብቻና አምቻም ተሳስረው ለመኖር የመጡትን ተጋሩ ሳይሆን እንደግሪሣ ‹ሆ!›፣ እንዳንበጣ ግርርር… ብለው ሊያጠፉትና ንብረቱን ሊዘርፉት ቀየው ድረስ የዘመቱበትን ወያኔዎች ልክ ልካቸውን በመስጠት ዋጋቸውን መክፈል ካልቻለ ዝንታለሙን ሲያለቅስ ይኖራል፡፡ ከዚህ በዘለለ በየዘመናቱ የሚነሱ የሰሜን ወራሪዎች “ቆዳየን ገፈፉት፤ ባልቴት እናቴን እየተፈራረቁ ተኟት፤ ሀብት ንብረቴን አቃጠሉት፤ ሚስትና ልጄን እፌቴ ደፈሯቸው፣ መንደሬን አወደሙት፤ ወዘተ.” እያሉ ማላዘኑ ዋጋ የለውም፡፡ “ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው” ወንድማለም፡፡
ድርድር ምንድን ነው? በማንና በማን መካከልስ ይካሄዳል? ተደራዳሪ ወገኖች ምን ዓይነት ባሕርይ ሊኖራቸው ይገባል? ተሸንፎስ ድርድር አለ ወይ? አካባቢን ወዶና ፈቅዶ በአሻጥር ለጠላት ካስረከቡ በኋላ ቢደራደሩ ውጤቱ ምን ሊሆን ይችላል? ተጎጂዎችን በመወከል ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ያደረገ ኃይል ተጎጂዎችን በመወከል ራሱ ሊደራደር ይችላል ወይ? እንጠይቅ፡፡ መጠየቅ ክፋት የለውም፡፡
ስማኝ እስኪ – አይሲስ የሚባለው ሽብርተኛ ድርጅት ወይም አልቃኢዳ የሚባለው ጓደኛው ከየትኛውም ወገን ጋር ለድርድር ተቀምጠው አይተህ ወይ ሰምተህ ታውቃለህ? ቦኮሃራም ከናይጄሪያ መንግሥት፣ አሜሪካን ከቢን ላደን ጋር ተደራደሩ ሲባልስ ሰምተህ ታውቃለህ? እርግጥ ነው ሁለት ሽብርተኞች በጥቅም ምክንያት ለድርድር ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ ከዚህ አኳያ አይሲስና ቦኮሃራም ወይም አልሻባብና አልቃኢዳ … ለድርድር ቢቀመጡ አይገርምም – እውነታው እንደዚህ ከሆነ ዘንድ የወያኔና ብልጽግና ድርድርም ልክ እንደነዚህኞቹ ነው፤ “ይህን ለኔ ተው ያን ላንተ ውሰድ” ለመባባል ይጠቅማቸዋልና የነዚህ ጭራቃውያን ቡድኖች ድርድር አሳማኝ ነው፡፡ በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ዜጎችን በሸኔ-ብልጽግና ከወለጋና መላው ኦሮምያ የሚባል አካባቢ እስከ ትህነግ-ባይደን ከወሎና ሸዋ ግዛቶች የሚገኝን አማራ በጅምላ የሚጨፈጭፍ፣ የቤት ውስጥ እህልና የእርሻ ላይ ክምር የሚያቃጥል፣ እርሱ ራሱ ከፈረደባቸው ሞት የሚተርፉ የሚጠላቸው ወገኖች ወደፊት እንዳይጠቀሙባቸው በማሰብ የቤት እንስሳትን ሣይቀር በቀይ ሽብር የጥይት ዶፍ የሚረፈርፍ፣ አማራን በአማራነቱ ብቻ ተመርኩዞ ከአድማስ ወዲያ ማዶ ሰው ይቅርና ሀገር መኖሩን እንኳን የማያውቅ ንጹሕ ባላገር በመትረየስና በመድፍ የሚፈጅ፣ ከሰው ተራ ወጥቶ ከዐውሬነት ደረጃም ወርዶ ከሰይጣንም እጅግ አንሶ ሰማይና ምድር የማይችሉትን ግፍና በደል የሚፈጽም አካል በምን ሒሳብ ነው ለድርድር የሚቀመጠው? ከማንስ ጋር? በምን ተለይተው? ለመሆኑ ወያኔ ቋንቋ መጠቀም የሚያስችል የሰውነት ክፍል አለው ወይ? “እባክህ ማለኝ!” በማለት እያለቀሰች የምትለምነውን በቅጡ አፍ ያልፈታች ሕጻን ከአማራ ወላጆች ስለተገኘች ብቻ እየሳቀ በጥይት አረር የሚቆላ ብዔል ዘቡል የአጋንንት ውላጅ እንዴት አድርገህ ነው በውይይት አሳምነህ ሰው የምታደርገው? ምን ዓይነት ቀልድ ነው? ብልግና ፓርቲ ተብዬውስ ራሱ እያስታጠቀና ስንቅና አስተዳደራዊ ድጋፍ እያደረገ፣ አማራው ራሱን እንዳይከላከል በሸርና በሸፍጥ እያደናቀፈ የክልሉን በርካታ አካባቢዎች ካስወረረ በኋላ ከዚህ ራሱ በቁልምጫ ጁንታ ብሎ ከሚጠራው ኃይል ጋር ለመደራደር የሞራል ብቃት አለው ወይ? በአቢይ ቤት፣ በሽመልስ አስተሳሰብ፣ በብርሃኑ ጁላ ግምት፣ በጃል መሮ ዕይታ፣ በኦነግ ግንዛቤ … በኦሮሙማ የዕውር ድምብር ሩጫ የሚያደርጉት ቅጥ ያጣ ኢትዮጵያን በኦሮምያ የመቀየር እንቅስቃሴ ከኛ የተደበቀ፣ ከፈጣሪም የተሠወረ ይመስላቸዋል፡፡ ሞኞች!!
አዎ፣ ቀልድ በአግባቡ ሲሆን ፈገግታን ያጭራል፡፡ እንጨት እንጨት የሚል ቀልድ ግን በሰው ላይ እንደማፌዝ ነው፤ ይህ ደግሞ ያናድዳል፡፡ ስለሆነም የሚባለው ድርድር በሤረኞች መካከል የሚደረግ የንብረት ክፍፍል እንጂ እውነተኛ ድርድር ሊሆን አይችልም፡፡ “ከአንፆኪያ ወዲህ ለኔ፣ ከውጫሌ ወዲያ ለእንትና፣ ከባቲ በታች ለእገሌ….” ዓይነት ኢትዮጵያን በማያውቁ ህልመኞች የሚካሄድ ቅርጫ፡፡ ወንበሩ መድረሻ አጥቶ፣ የሚቀመጥበት ትክክለኛ ሰው ጠፍቶ እነሱ መቀመጫ ሥር ስለተገኘ ሁሉም ነገር እንዳቀዱት የሚፈጸም መስሏቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ቤተ መንግሥቱንም ይዘው እንዲህ ቅብጥ የሚሉትና የሚሠራቸውን የሚያሳጣቸው፡፡ ወንድሜ – ሥልጣን ጥበብን ትሻለች፤ ሥልጣን ማስተዋልን ትፈልጋለች፤ በቂም በቀልና በጥላቻ ያበደና በሤራ ፖለቲካ ተኮትኩቶ ያደገደ ሰው ሥልጣንን ቢይዛት ራሱንም ሀገርንም ለተወሰነ ጊዜ ይጎዳል እንጂ የተንኮል ዕቅዱ አይሠምርለትም፡፡ እነዚህ ይሠሩትን ያሳጣቸው የኦሮሙማ ኅሊናቢስ ጉዶችም የቀባጭ ምሣቸውን በቅርቡ ያገኛሉ፡፡ ያኔ እነሱን አያድርገኝ!! ሒሣብ ማወራረድ የሚባለው አዲሱ ዘይቤ በደምብ የሚታዬው የዚያኔ ነው፡፡ ኢትዮጵያን የነካ ብቻ ሣይሆን ያስነካም አሣሩ ብዙ ነው፤ ታሪክን ይመልከቱ፡፡ ታሪክ ደግሞ ራሱን ይደግማል፤ ይደጋግምማል፡፡
አማራው ይበልጡን ይጠንቀቅ፡፡ ብአዴንን በአፋጣኝ ይቅበር፡፡ ይህንን ማድረግም ቀላል ነው፡፡ መጃጃል ይብቃው፡፡ ቀንደኛ ቀንደኛ አማራ ሻጮችን በገቡበት እየገቡ ሂሳባቸውን መስጠት ለነገ የሚተው አይደለም፡፡ በዱሮ ዘመን መንጃ ፈቃድ ያወጣችሁ ሰዎች ታስታውሱታላችሁ – 60 ሰው ጭነህ እያበረርከው ባለኸው መኪና በፊት ለፊትህ አንድ ሰው ድንገት ቢገባብህና ሌላ አማራጭ ብታጣ ሰውዬውን ገጭተህ 60 ሰው ታተርፋለህ እንጂ አንድ ሰው ለማዳን ብለህ አውቶቡስ ሙሉ ሰው ይዘህ ገደል አትገባም፡፡ ስለሆነም የአማራ ይሉኝታና “ፍርሀት” ከአሁን በኋላ ማብቃት አለበት፡፡ በምልዓቱ ከ40 እና 50 ሚሊዮን የማያንስ ሕዝብ በጥቂት የጠላት ምንደኞች ተታልሎና በይሉኝታ ገመድ ታስሮ እያሳረዱት በሚገኙ የወያኔና የኦነግ/ኦህዲድ ሠርጎ ገቦች ኅልውናውን ሊያጣ አይገባምና እነዚህን አጋሰሶች በቶሎ ያሰናብት፡፡ ለዚህም የሀዲስ ዓለማየሁ የምናብ ፍጡራን በሻህ ዘለሌንና አበጀ በለውን የመሰሉ ጀግኖች ተፈጥረው ሥራቸውን በአፋጣኝ ይጀምሩ፡፡ እሹሩሩ ይብቃ፡፡ አንዳንድ ውሳኔዎች ጨከን ካላሉ አስቸጋሪ መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ የአማራ ሥነ ልቦና ደግሞ ለዚህን መሰሉ እርምጃ ልቡ ስስ ነው፡፡ ለዚህም ነው ወያኔዎች የሴቶቻቸውን ሆድ ጨርቅ በመጠቅጠቅና ወገባቸው ላይ አሻንጉሊት በማሳዘል እርጉዝና እመጫት እያስመሰሉ ጦር ሜዳ በማዝመት አማራው “ውይ የኔ እህት! ይህችንስ አልገድልም” እያለ ሲተዋት እርሷ ግን ደብቃ በያዘችው ጠበንጃ ስትቀነድበው የሚስተዋለው፡፡ አማራ ለሞኝነቱና ለርህራሄው ልክ ሊያበጅለት ይገባል፡፡ ጠላት ምን ጊዜም ጠላት ነው፡፡ ልጅህም ሊገድልህ ከመጣ ቅደመው እንጂ አይቅደምህ፡፡ ይህ ጭካኔ አይደለም – ተፈጥሯዊ ራስን የመከላከል ጠባይ ነው፡፡ ያለንበት ዓለም የፈተናና የመስዋዕትነት ነው፤ ገነት ወይም መንግሥተ ሰማይ አይደለም፡፡ ራስን ከጥቃት መከላከል ደግሞ ሃይማኖታዊም ሆነ ህጋዊና ሞራላዊ ድጋፍ ያለው ነው፡፡ ይሉኝታንና ሀፍረትን ሸጠው የበሉ ጥቂት ሚሊዮኖች በይሉኝታና በሀፍረት ተተብትበው የሚገኙ ብዙ ቢሊዮኖችን ያንበረከኩበት ምሥጢር እዚህ ላይ የምጠቃቅሰው በአላስፈላጊ የዋህነትና ትግስት የመሸነፍ ጉዳይ ነውና አማራው ከአሁን በኋላ እንደርግብ የዋህ እንደእባብም ልባም መሆን ይኖርበታል – መጽሐፉም እኮ “ኩኑ የዋሃነ ከመርግብ ወልባማተ ከመዐርዌ ገዳም” የሚለው ለዚህ ነው፡፡ አለበለዚያ የአማራ ሕዝብ ልክ እንደስካሁኑ ሁሉ ወደፊትም በጥቂቶች ተንኮልና በራሱ ልጆች ሆዳምነት እስከወዲያኛው ፍዳውን ሲያይ መኖሩ ነው፡፡ ገዳዮቹን አቅፎ እዬዬ ቢል መፍትሔ የለውም፡፡ ለማለት ያህል ይህን አልኩ እንጂ ነገ ምን እንደሚሆን በሚገባ እረዳለሁ፡፡ እየነደደኝ ግን “እንደማላውቅ” እሆንና አሁን ያልኩትንና ምናልባትም ወደፊት የምለውን ሁሉ እላለሁ፡፡ እንጂ አይዞን!! የብሥራት ጫፍ ላይ ነን፡፡ ጨለማው ሊገፈፍ የቀረን ጊዜ በጣም ትንሽ ነው፡፡ ተስፋችንም አንድዬ ነውና ከ120 ሚሊዮን ሕዝብ አሥር የእግዜር ሰዎች እንኳን ብትገኙ አጥብቃችሁ ጸልዩ፡፡ ከፓትርያርክ እስከ ተራ ዲያቆን፣ ከኢማም እስከ ደረሳ፣ ከፓስተር እስከተራ አጨብጫቢ ምዕመን በዓለም የሥጋ ገበያ በጠፋበት በዚህ አስቀያሚ ዘመን “እገሌ ያድነኛል፤ በዚህና በዚያ ‹ቸርች› ከበሽታየ እፈወሳለሁ – ሀብት ንብረትም አገኛለሁ …” ብለሽ ደግሞ ተስፋ አታድርጊ እህቴ፡፡ ከኃጢኣት መታቀብ፣ ከተፈጥሮና ከፈጣሪ ህግጋት አለማፈንገጥ፣ የሰው ሃቅ አለመውሰድ፣ ፍትኅን አለማዛባት፣ በአግባቡ ነግዶ ማትረፍ፣ የሰውን ላብ በከንቱ አለማስቀረት፣ በንጹሕ ገቢያችን መኖር፣ ከሙስና መራቅ፣ ለቅጥር ሠራተኛህ መኖር የሚያስችለው ተገቢ ክፍያና ጥቅማ ጥቅም መመደብ፣ የሆድን መጠንና የፍላጎትን ድንበር ማጥበብ … የባሕርይ ገንዘቦቻችን ልናደርጋቸው ከሚገቡን ዋና ዋና የጽድቅ መንገዶች ጥቂቶቹ ናቸውና የምንገኝበትን የነፍስና የሥጋ ግንኙነት በሚገባ እንመርምር፡፡ ሁላችንም ብንተዛዘንና ተሳስበን ብንኖር ፈጣሪ ፊቱን አያዞርብንም፡፡ ክፉዎች ከሆን ግን ይጠየፈናል፡፡ ለሚያልፍ ዓለም የማያልፍ ጠባሳ ለኅሊናችንና ለአእምሯችን አናትርፍ፡፡ በሰላም ውለን በሰላም ለመግባታችን እርግጠኛ ልንሆን በማንችልባት ብልጭልጭ ዓለም ክፉ አንሁን፡፡ ክፋትን እንጠየፍ፡፡ ሃይማኖትን ለጊዜው እንተወው – ከፈለግን፡፡ ግን አንዳችን ለአንዳችን ጥሩ ለመሆን፣ አንደኛው ለሌላኛው ጥሩ ለማሰብ እንሞክር፡፡
ከበደ ሚካኤል “ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም፤ ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም” ያሉትን እናስታውስና በሰው ልጅነታችን ብቻ እንተሳሰብ፡፡ ዐረመኔነት በእንስሳትም አያምርምና እኛ ሰዎች፣ ሰዎች ለመሆን እንጣር፡፡
በመጨረሻም በመግያየ የጠቀስኳትን የትግርኛ ምሣሌያዊ አነጋገር በአማርኛ ላፍታታት፡፡ “ዝአኽለን ጥኽነን በዓል ማርያም ትብላ” ማለት በነፃ ትርጉም “የሚበቃትን ያህል ከፈጨች በኋላ ‹ውይ በሞትኩት! ለካንስ ዛሬ ማርያም ናት› ትላለች” ማለት ነው – በዕለተ ማርያም በተለይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተለይም በዱሮው ዘመን በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ሥራ መሥራት እንደ ዕርም የሚቆጠር ነበር – እንደኃጢኣትና ነውር፡፡ የዛሬውን ተውት፡፡ ዕድሜ ለወያኔ ሃይማኖቱንም ባህሉንም ባንዲራውንም መተሳሰቡንም … አጥፍቶ ትግራይን ብቻም ሣይሆን ሌላውንም የኢትዮጵያ ክፍል ሁሉ የአጋንንት መጨፈሪያ ምድረ በዳ አድርጎታል፡፡ ግን ማልፋቱ ከፋ እንጂ ይህም ያልፋል፡፡