>

አሜን ለኢትዮጵያ እንበል አሜን! (ዘምሳሌ)

አሜን ለኢትዮጵያ እንበል አሜን!

አሜን ለኢትዮጵያ አሜን


ልጆችሽ ሰባዊነታቸውን ትተው የአናብስቱን ቦታ
ነጠቁ
አራዊቶችሽ ተሽለው አንድነታቸውን  ጠበቁ
ምናል ፡ ነበር ፡ ለሰዎችሽ ፡ የሰጠሽው ፡
ክብር
ቢሆን ፡ ለአራዊቶችሽ
ሳትደፈሪ ፡ ያኖሩሸ ፡ ነበር ፡ በክብርሽ
ማንም እየተነሳ  ዘር መዝዞ ላይጋፈፍሽ
አንቺማ ፡ በዘመን ፡ ዘረኝነት ፡ነግሶብሽ
ልጅ ሀብት ልማትሽን ሲያረግፉብሽ

የማይነጋ፡ ቢመስልም ቀኑ
የተሰራሽበት ፡ የአንድነት ፡ ውጥኑ
ፈተው ፡ ላይጨርሱት ፡ ሲፋጠኑ
ቅጥረኛን በዘር አቧድነው ሲያሰለጥኑ
በግለኝነት ጥቅም  ታስረው
ልብ አዕምሮአቸውን ሰውረው
ከፍተውና ብሰው የተለወጠ ባህሪይ  ተላብሰው
ከዘመን ዘመን ተሻግረው
በክፋት ምግባራቸውም ብሰው

ዙሪያ ገባሽ በነርሱ ተንኮል ታጥሮ
የንፁሀን ልጆችሽን ጥሬት አሳርሮ
የመኖር ተስፋቸውን ነጥቆና ሰብሮ
በእስር እንግልት ዕድሜያቸው አሳጥሮ
ይህን ሁላ ግፍ  በላይሽ ሲከምሩ
ምን ይሆን ኢትዮጵያ የመኖርሽ ሚስጥሩ
ከውጪ ጠላቶችሽ ሊያጠፉሽ ሲጥሩ
የነርሱን ሰንደቅ ይዘው የገዛ ልጆችሽ ሲኖሩ

ወዳጆችሽ ስላንቺ የሚኖሩት
በከሀዲያን ገፊዎችሽ የተማረኩት
ኑሮ ከፍቶባቸው እድሜያቸው የሚቆጥሩት
እነኛ ትጉሀን አርማሽን ያነገቡት
ድንበር ጠባቂዎችሽ በዘረኝነት በተቧደኑት
በገዛ ወገናቸው የተከዱት
ላንች ሕልውና የወደቁት

ጠባቦች እጣፈንታሽ  ወስነው ሲከፉ
ወሰን ድንበርሽን ሲያስገፉ
ታዳጊዎችሽን  መርጠው ሲያስረግፉ
መርገም እዳሽ ሆነው በነውራቸው ሲጣደፉ
የእናትና የወጣት ሴቶችን ክብር ሲጋፈፉ
በየዜና አውታሩ ስምሽን ሲያስጠፉ
ከዚያም አልፈው የተቃወማቸውን ሲሰይፉ
ብቅ ብቅ ብለው የነበሩትን ተሟጋቾች

አንገት ሲያስደፉ
ከልካይ ሆሽ የሚላቸው የጠፋሽ
ከገባሽበት አዘቅት የሚያወጣሽ
አለሁ የሚል መሪ ከዚህ የሚታደግሽ
ስላንቺ ክብር የሚኖርልሽ ጠፍቶሽ
በየለውጡ ማግስት ነውጥ የሚፋጅሽ

እስከመቼ  ይሆን ኢትዮጵያ
የምትሆኝው የሲኦል አምላኪዎች ማጎሪያ
ልንቁጥ ጭቃ መንከባለያ እንደ እሪያ
የታጀልሽ በአድሮ ጥጃነት ማብሊያ
እንዳናጥብልሽ የክፍውን ዘመን ክርፋት
የልጆችሸን እስር እንግልትና ግርፋት
ጡንቾቻችን በመራር ትግል ውድቀት
ዳግም እየተኮሳመኑ የሚዳርጉን ለክደት

በጥቂቶች አንጃ ጩኸታችን መክኖ
ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል ሆኖ
እንዴት ይኑር  ኢትዮጵያ ህዝቡ ባዝኖ
እምነት ወጌን ባህሌን ሀገሬን  ባለ
በየስፍራው በሴረኞች እየተገደለ
የወገኑን ተረኛ አስከሬን እየተቀበለ

ሞትን ለምዶ እያማረጠ ይኸኛው ከፊተኛው
የተሻለ አሟሟት ነው እየተባለ
አስከሬን በዘር ልጥ አስሮ እየደበለ
አይንም እንደተፈጥሮ ማንባቱን ትቶ
ማሰብ ማሰላሰል የተሳነው ግንባር ላይ ተሰክቶ
በማየትና በማስተዋል መፍረድንም ዘንግቶ
መሬትና ልጆችሽን አስበልቶ

መቼም በዘመኑ እንክርዳድሽ ቢበዛም
ህዝብአዳምሽ መላጠፍቶት በየማጀቱ
ቢያልጎመጉምም
አንደ ቴዎድሮስ ወይ  ሚኒሊክ እንደሁ አይጠፉም
ምሬት ሀዘን ጉዳትሽን ጠግኖ የሚያክም
መምጣት  መከሰቱ አይቀርም
ለዘላለም አለም እስኪሆንልን ሰላም
አሜን አሜን
ለኢትዮጵያ አንበል አሜን  ዛሬም!

Filed in: Amharic