የእሳት ልጅ አመድ….!!!
ዘመድኩን በቀለ
“…እኒህ በፎቶው ላይ የምንመለከታቸው የዚያ የደፋርና ነውረኛው አንተነህ/ ኢያስጴድ ተብዬውና ደርሶ ኦሮሞ ኦሮሞ ለመጫወት የሚቃጣው የጃዋር አሽቄ በመሆን መታየት የሚፈልገው ኢትዮጵያን በመጥላት መንፈስ የተመታው ልጅ አባት የተከበሩት አቶ ተስፋዬ ታደሰ አበበ ናቸው።
…አቶ ተስፋዬ ታደሰ ወሎ ቦረና መካነ ሰላም የተወለዱ የዐማራ ሳይንት ሰው ናቸው። በጥብቅና ሙያ የሚተዳደሩና በነፃው ፕሬስ ዘመን የሉባርና የመስታወት ጋዜጦች ባለቤትም ነበሩ። እነ መለስ ዜናዊና ኦነግ እምዬ ሚኒልክን “የአፍሪካ ሂትለር” እያሉ ሲሰድቧቸው፣ ሲያዋርዱና ሲያንቋሽሿቸው ባዩ ጊዜ በፍጹም ብለው በጋዜጦቻቸው ላይ የምኒልክን ታላቅነት በብዕራቸው የሞገቱም አባት ናቸው። በዚህ ተግባራቸው የተበሳጨው መለስ ዜናዊ (ነአ) ከርቸሌ አስሮ አሰቃይቷቸዋል። ከእስር ሲፈቱም መዐህድን ተቀላቅለው ለጭቁኑ ዐማራ ታግለዋል።
…በአቶ ተስፋዬ ጽናት የበገኑት እነ መለስ ዜናዊና ኦነጎች አንድ ቀን ከቤታቸው ልጃቸውን የአሁኑን ኢያስጴድን ይዘው የእግር ጉዞ አድርገው ነፋስ ተቀብለው ሲመለሱ ከደጃፋቸው ላይ ጠብቀው በሳንጃ ዘክዝከውና አርደው፣ በገጀራም ጨፍጭፈው ገደሏቸው። ትንሹ አንተነህ/ኢያስጴድ እያየ አባቱ በአፄ ምኒልክ ምክንያት ሰማዕትነትን ተቀበሉ። ይሄን እያየ ያደገው የአቶ ተስፋዬ ልጅ ይኸው ጃዋር ከመጣ በኋላ ድንገት ተከርብቶ በእናቴ በኩል ኦሮሞና ጴንጤ ነኝ ብሎ፣ ምኒልክ ነፃ ባወጧት ሃገር ላይ ተዘፍዝፎ ወደፊት የምኒልክን ስም መጥራት በሕግ የሚያስጠይቅ ሀገር እንመሠርታለን የሚል የድፍረት ቃል ሲናገር ተሰማ።
ለጊዜውም ቢሆን መታሰሩ እየተነገረ ነዉ
…ወደፊት የምኒልክን ስም በክፉ የሚያነሣ በሕግ የሚጠየቅበት ዘመን ይመጣል።
ምኒልክ ዛሬም ንጉሥ ነው!!!