>

"ትግሬነቴን በ0.01 ዶላር ልሸጠው ወስኜ ነበር! አሁን ግን ሃሳቤን ቀይሬአለሁ፤ ትግሬነቴን ከፍዬው የሚወስድልኝ አለ?" (ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ)

“ትግሬነቴን በ0.01 ዶላር ልሸጠው ወስኜ ነበር! አሁን ግን ሃሳቤን ቀይሬአለሁ፤ ትግሬነቴን ከፍዬው የሚወስድልኝ አለ?”
ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ

 
*…. “እኔ እና ልጄ ሔርሜላ በኢትዮጵያ ጉዳይ እውነትን ይዘን  ገለልተኛ አቋም ስላለን [ህወሓትን ባለመደገፋችን] በውጪ በሚኖረው አብዛኛው (95%) የትግራይ ማህበረሰብ ዘንድ መገለል እና ዛቻ ደርሶብናል። እራሳችንን ሆነንም ገለልተኛ ሆነን እንድንኖር አልፈቀዱልንም
የሔርሜላ እናት  – ፕሮፌሰር ሐረገወይን አሰፋ
 
28 አመት በውጭ ሃገር ስኖር ጥቁር እንደሆንኩ እንጂ ማንም ብሄሬን ጠይቆኝ አያውቅም። እኔ ልጆቼ ነፃ ሰው ሆነው ለህሊናቸው እና ለእውነት እንዲኖሩ አድርጌ ነው ያሳደግኳቸው።
እኔ ልጆቼን በነፃነት የፈለጉትን እንዲሆኑ ነዉ ያሳደኩት ፤  ሔርሜላ የፈለገችዉን ሐሳብ ማራመድ መብቷ ነዉ። ሔርሜላ ነፃና ገለልተኛ ሆና እውነትን ይዛ እየተጓዘች ነው ያለችው። ለዛም እደግፋታለሁ። ልጄ ሔርሜላ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይዛ በዓል ስታከብር መተዉ አዋከቧት ሰደቧት አገለሏት። ኢትዮጵያዊ መሆኗን በመናገሯ አሸማቀቋት።
እኔ የማስበዉ እንደ ግለሰብ እንደ ነፃ ሰው ፤ የአለም ዜጋ ነዉ። ፕሮፌሽናል ኢንትግሪቴዬን አሳልፌ አልሰጥም። ያላመንኩበትንም ነገር ፈፅሞ አልቀበልም። ያላመንኩበትን ነገር ሳደርግ እንቅልፍም አይወስደኝም። ትግርኛ ስለተናገርኩ ብቻ ሰዉ ከሚደፍር እና ጥላቻን ከሚሰብክ ጋር አንድ ሳጥን ዉስጥ ልገባ አልችልም።
አሁን እኛ ተደብቀን ነዉ የምንኖረዉ። ደግነቱ ካሜራ ምናምን አለ። ቢያገኙን ሊሰቅሉን ነዉ የሚፈልጉት። በጥላቻ የናወዙ ሰዎች ናቸዉ። ልክ እንደ እነሱ እንድናስብ ነዉ የሚፈልጉት።ከሁሉ በላይ የሴኩዉሪቲ ኢሹ ያሳስበናል  እንጂ ወደ ኢትዮጵያ መሄድ እፈልጋለሁ።
በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ልጄን ለጎረቤት ኤርትራዊ ሰጥቼ ነዉ የሄድኩት። እኔ አንድ ቀን ይህ ጊዜ ያልፋል ብዬ አስባለዉ። እስከዛሬ ከነዛ ጎረቤቴ ጋር በፍቅር ነዉ ያለነዉ። ኢትዮጵያዊያና ኤርትራም ይኸዉ አሁን አንድ ሆነዉ ነዉ ያሉት። ሰዉን በዘሩና በሚናገረዉ ቋንቋ ሳይሆን በሰዊነቱ ነዊ የማየዉ።
እኛ የአለም ዜጎች ነን ፣ ጥቁር አፍሪካዊ ኢትዮጵያዊ ነን፤ ለልጆቻችን ስናሳድግ አንድነት እና ፍቅርን እንጂ የራሳችንን ጥላቻን ልንጭንባቸው አይገባም።
ወላጆች ልጆችን ፍቅር እያስተማሩ ማሳደግ አለባቸዉ። እኔ ለልጆቼ ስለ ሰውነት ከዛ ካለፈ ጥቁር አፍሪካዊነቷ ዝቅ ሲል ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ ነዉ እየነገርኳት ያሳደኳት። እባካችሁ ልጆችን ስለ ጥላቻ አታስተምሯቸዉ።
ጥላቻ አይጠቅመንም። ጥላቻ የሚነዙ እንዳሉ ሁሉ አንድነት እና ፍቅርን የሚመኙ ጥሩ ሰዎችም አሉ። ስለዚህ እኛ መሰባሰብና ጥሩ ዘር መትከል አለብን። አሁን ያ ቀስ በቀስ እየተፈጠረ ይመስለኛል። ብዙ የሚያሳዝን ነገር ቢኖርም ተስፋ የሚሰጥ ነገርም አያለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ ፤ ጥበብና በረከትን ያብዛልን !”
ፕ/ር ሐረገወይን አሰፋ የኬሜስትሪ ሳይንቲስት ስትሆን ትውልዷ ከትግራይ ክፍለ ሀገር የሆነ ለረጅም አመታት በአሜሪካ የኖረችና በ2019G.C በአሜሪካን ሀገር የሚሰጠውን ‘Heros of Chemistry Award’ ተሸላሚ ነበረች።
ሔርሜላን የመሰለች የማትበገር የእውነት ጠበቃ ልጅ ወልደሽ ስለሰጠሽን እናመሰግናለን !
ምንጭ፦ ግዕዝ ሚዲያ
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች !
Filed in: Amharic