>

“የአማራ ኢሊቶች..”? (ጌታችው አበራ)

“የአማራ ኢሊቶች..”?

 

    ጌታችው አበራ


የወያኔ ሮሮ፣

የጅል እንጉርጉሮ፣

ሲዘመር ሰምቼ፣

ጆሮዬን አቅንቼ፣

ሳዳምጥ በብርቱ፣

ነበር ለካስ ከንቱ!

 

“ሂሳብ ማወራረድ..

ከአማራ ኢሊቶች”፣

ይል ነበረ ግጥሙ..

የጭካኔው አዝማች፤

ያረመኔ ተግባር ..

ቢሆንም ድርጊቱ፣

መስሎኝ የነበረው..

ሰው ነበር “ኢሊቱ”፤

 

ለካስ በወያኔ፣

በደደቢት ቅኔ፤

ጥማድ በሬዎቹ፣

ላሞች ጥገቶቹ፣

በጎች ፍየሎቹ… 

ነበሩ “ኢሊቶች”..

ያማራ ሃብቶቹ።

 

እንሰሳት ገዳዩ፣

ቡሃቃ አማሳዩ፣

ሆስፒታል ነቃዩ፣

ሬሳ አቃጣዩ…፣

አረመኔ ጨካኝ..

ቦቅቧቃ ማፊያ፣

ወያኔ! ወያኔ!..

የአገር ማፈሪያ!

 

Filed in: Amharic