>

"የትናንቶቹ ባለጊዜዎች የሚፈጽሙትን መድሎና ግፍ የተቃማችሁ ፖለቲከኞች ተረኞቹ በከፋ ሁኔታ ሲፈጽሙት ጽድቅ ሆኖ ታያችሁ...???" (ጌራወርቅ ዝናቡ)

የትናንቶቹ ባለጊዜዎች የሚፈጽሙትን መድሎና ግፍ የተቃማችሁ ፖለቲከኞች ተረኞቹ በከፋ ሁኔታ ሲፈጽሙት ጽድቅ ሆኖ ታያችሁ…???”
ጌራወርቅ ዝናቡ

የኦሮሞ ብልጽግና ታከለ ኡማ በሚመራው ተቋም ጥቂት እንደማሳያ ትናት ወያኔ እሚጠላው ትንሹንም ትልቁንም እኔው ካላግበበስኩት ሌላው ቆሞ ተመልካች ከመሆን የዘለለ ሚና የለውም በሚል ነው ትናት የአገሪቱን ሀብት በሞኖፖል የአንድ ብሔር ብቻ የሆኑ ኢፍትሀዊ በሆነመንገድ በመቆጣከራቸው ያን ሀብት እያወጡ ዛሬ ላይ አገር ለማፍረስ እየተጠቀሙት እንደሆነ በተግባር አይተናል ተረኛውስ ምን እያረገ ይሆን? በዚህ ወቅት ከመንግስት ጎን አለመቆም የአገር ክደት ነው የምትሉን ያገር አሳቢ ከሆናችሁ እንደዚህ አይነት አይን ያወጡ እልቆ መሳፍርት የሌላቸው አንዳዶቹ ከትናት ከዘመነ ወያኔ በከፋ መንገድ ሲፈጸሙ ምነው ድምጻችሁ ይጠፋል መርሀችሁ ኢፍትሀዊነትን መታገል ከሆነ ድምጻችሁ ለምን ይጠፋል ትናት የትግራይ ፖለቲከኞች የሚፈጽሙትን መድሎና ግፍ ከተቃማቸው የኦሮሞ ፖለቲከኞች የትናቱን መገድ በከፋ ሁኔቴ ሲፈጽሙት ጽድቅነው ማለት ነው? ለኔ ይህ አንድ ዘረኝነት
ሁለት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የጥቅም ተጋሪነት
ሶስት አድርባይነት እና አሽቃባጭነት ነው መርህ በአገር ላይ የትኛውም አካል የሚፈጽመውን ግፍ ተቃውመህ የተሻለ ነገር እንዲመጣ ከሆነ ፍትህን እኩልነትን መርህ አርገህ ከዛውጭ ወያኔን ብቻ በመርገም ሌላውን የግፈኞች ቁንጮ አናትላይ አርጎ በባዶ በመጨፈር አገርን ከድቀትና ከቀውስ ማውጣት አይቻልም።
አገርን ሰም እየጠሩ ኑ አንድ ጋር እንቁም ከማለት በፊት መጀመሪያ አይነስር ያለውን ጉድፍ አሳና ከዛ ስለአገር ለመናገር ሞራል ይኖርሀል!
Filed in: Amharic