ይህ ሰው ንጹሕ ሰው ነው ፍቱት…..!!!
መምህር ታሪኩ አበራ

★ ዓቢይ አህመድ እስክንድር ነጋን ያሰረው በሃይማኖቱ ጠንካራ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ በመሆኑና በፓለቲካ አቋሙም የመንግሥትን ስህተት በግልጽ የሚቃወም ጠንካራ ሰው በመሆኑ ብቻ ነው።★
★ እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ሰው እንጂ ሌላ የክፋት አጀንዳ እንደሌለው ንጹሕ ኢትዮጵያዊ ልብ ያለው ሰው ሁሉ የሚመሰክረው ሐቅ ነው።★
★ በዘመነ ህወሓት ዘጠኝ ዓመት በእስር ሲማቅቅ የነበረን ሰው ድጋሚ በግፈኛው ዓቢይ አህመድ አረመኔያዊ ውሳኔ ከዓመት በላይ በእስር እንዲሰቃይ ማድረግ ከግፍ ሁሉ የከፋ ግፍ ነውና እስክንድርን ልቀቁት እርሱም እንደማንኛውም ሰው የግሉ ሕይወት ያለው በፍቅርና
በናፍቆት የሚጨነቁለት ቤተሰብና ልጅ ያለው ሰው ነው።ዓቢይ አህመድ ከነቤተሰብህ በሞቀ ቤት ውስጥ ተቀምጠህ በዚህ ሰው ላይ የምትፈጽመው ግፍ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ የከፋ በደልና የድፍረት ኃጢአት በመሆኑ ካንተ በፊት የነበሩ ግፈኛ ባለ ሥልጣናትን በአደባባይ አዋርዶ የቀጣ እግዚአብሔር አንተንም በከፋ ሁኔታ በውርደት ሞት እንደሚቀጣህ አትርሳ።እግዚአብሔር ፍትሐዊ ዳኛ እውነተኛም ንጉሥ ነውን

ለፍትሕ በጋራ እንቁም!!