>
5:21 pm - Saturday July 21, 7246

<<ባለቤትነቷን በይፋ እሰካልነጠቃችሁ ድረሰ የመስቀል አደባባይ ባለቤት የኦርቶዶክሰ ቤተክርስቲያን ናት>> (ፓስተር ቢኒያም ሽታየ )

<<ባለቤትነቷን በይፋ እሰካልነጠቃችሁ ድረሰ የመስቀል አደባባይ ባለቤት የኦርቶዶክሰ ቤተክርስቲያን ናት>>
ፓስተር ቢኒያም ሽታየ 

ግልፅ ደብዳቤ 
ለአዲሰ አበባ ከንቲባ ቢሮ  
ለአዲሰ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ቢሮ  
ለሰላም ሚንሰቴር 
*… ጴንጤዎች በተደጋጋሚ በዚህ አደባባይ ላይ በፈለጋችሁት ጊዜ ፕሮግራማችሁን ማድረግ ትችላላችሁ ! በፍቅር ወርሳችሁናል!
     መስቀል አደባባይ የመላው ኢትዮጵያዊ ነው!
          ከንቲባ አዳነች አበቤ

መቼም ቢሆን መቼ አቋሜ ግልፅ ነው በመሰቀል አደባባይ ባለቤትነቷን በይፋ እሰካልነጠቃችሁ ድረሰ የኦርቶዶክሰ ነው:: እንደ አንድ አገልጋይ ይዞታው የኦርቶዶክሰ ነው ብዬ የማምነው:: አሁን ነው የሰማሁት የፕሮቴሰታት መርሀግብር እንደተዘጋጀ ያወኩት በእውነት ባልጠፋ ቦታ ለምን ይህ አሰፈለገ? እባካችሁ ፈቃጅ ነን እያላቹ አታባሉን የሀይማኖት ተቋም የተመሰረተበት አላማ ምን ይሆን? የሰላም ሚኒሰተርሰ ፀብ ግጭት ሲነሳ ነው ሰራ የሚሰራው ባልጠፋ ቦታ እግዚአብሔርን ለማምለክና እርዳታ ለመሰብሰብ በሚል ሀሳብ የሀይማኖታዊ ትንኮሳ አንፈልግም:: መርሀግብር አዘጋጁ ማን ነው? ካውንሰሉ ከሆነ  ከኦርቶዶክሰ መሪዎች ጋር ሳትወያዩ ኦርቶዶክሳውያንን እያሳዘኑ አምልኮ የለም የከንቲባ ቢሮ እባካችሁ ጠቅላዪ እንዳሉ ሌላ አደባባዩች ሰሩ አታባሉን የሰሜኑ ሀዘናችን ሳይሸር እየነደድን ባለንበት እንዲህ አይነት ነገር ቢቀርብን እውነት አዘጋጅ ኮሚቴ እሰቴዲየም አትሰበሰብም አላማው ይህ ከሆነ ሁሉን እግዚአብሔር ያያል በወንጌል ሰም ፀብ አንፈልግም::የአዲሰ አበባ ከንቲባ ቢሮ ከህዝብ በተሰበሰበ ተሰራ ላላችሁት ኦርቶዶክሰ በቱሪዝም እሰከዛሬ ያሰገባችው ብዙ መሰቀል አደባባይ ያሰራል እናም ቤተክርሰቲያንን አታሳዝኑ ::በአጠቃላይ ግጭት አሰጠልቶናል ከዚህ በፊት ዘፈን ትርኢት ወዘተ ተደርጓል እያላችሁ አትደሰኩሩ:: ኦርቶዶክሰ የሰፍራ ቅዱሰነትን ማመኗን እናክብርላት::ሀገር ነችና አክብሯት ክርሰትናን ያሰተዋወቀችን በሀገር ጠባቂነቷ ወደር የሌላት እናት ቤተክርሰቲያናችን አይመማችሁ ታሪክ አጥኑ እንውረሰ የምትሉ የፕሮቴሰታን ሰባክያን ተው እንዲህ አይነት ቅዥት መፅሀፍ ቅዱሳዊ አይደም የያዝነውን በሰራንበት ሰለዚህ ተናጋሪው ከአፉ አምልጦት ነውና ይቅርታ ጠይቅ የምን መውረሰ አዋጅ 47/67  አደረከው ተው ይህ ምኞት አይበጅም ሰትፈቅድልህ ያምራል ወንድሜ ::የአዲሰ አበባ ከንቲባ ቢሮ ,የሀይማኖት ተቋማት, የሰላም ሚኒሰቴር እባካችሁ ተቻችሎ የኖረውን ህዝብ አታናቁሩት መልእክቴ ነው::  ኦርቶዶክሰ ሰትፈቅድ ማንም ምንም ያድርግበት ሁሌ በሰህተት አትጓዙ  አቋሜ መቼም ይሁን መቼ መሰቀል አደባባይ ከነ እሴቱ ቅርሰነቱ እንደተጠበቀ የኦርቶዶክሰ ነው ፕሮቴሰታንቶች  ለአምልኮ መች ቦታ ጠፋ ልብ እንጂ ኦርቶዶክሰ ከፈቀደችልን በደሰታ እንፀልይበታለን እናመልክበታለን ወንጌል ወንጌል ነውና ትውልዱን አታሰናክሉ ማንም ቢቃወመኝ አቋሜ ነው መልዕክቴም ይህ ነው ::ሼር ሼር ሼር ያድርጉልኝ መጋቢ ቢንያም ሸታዬ   “ብዙ ቦታ እያለ ምን ያገፋፋናል”
Filed in: Amharic