>
5:31 pm - Wednesday November 12, 2228

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አታምታታ... አታስቀይስ...የጦስ ዶሮ ፍለጋው አያዋጣህም....!!! (ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ)

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አታምታታ… አታስቀይስ…የጦስ ዶሮ ፍለጋው አያዋጣህም….!!!
ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ

*..…  እነ ጃዋር መሀመድ ለመፈታታቸው ያቀረቡት ቅድመ ሁኔታ የእነ ስብሃት ነጋ መፈታት ብቻ ሳይሆን የኦኤምኤን ሚዲያ ከነ ሙሉ ክብሩ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ፤ የተዘጉ የኦፌኮና ኦነግ የፓርቲ ቢሮዎች በሙሉ እንዲከፈቱ፤ የተሰደዱ የኦሮሞ ፓለቲከኞችና ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ፣ የባለሃብቶቹ ንብረት እንዲመለስላቸው፤ ህውሃት እና ሸኔ የሽብርተኝነት ፍረጃው ተነስቶላቸው  በድርድርና ምክክር መድረኩ እንዲሳተፉ …ወዘተ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው። 
 
የአቶ ስብሀት ነጋን ፍቺ ምክንያት በተመለከተ አንዳርጋቸው ጽጌ እውነቱን ለመሸፋፈን የጦስ ዶሮ ያስቀመጠበት ዘለግ ያለ መጣጥፍ ይፋ አድርጓል። የጽሁፉ ድብቅ አላማ በስብሃት ነጋ መፈታት ቅሬታ ያደረበት የተደጋፊ ተደማሪው ካምፕ ጣቶቹን ወደ ኢምፔሪያሊስት ካምፕ በተለይም ወደ አሜሪካ እንዲጠነቁል ለማሳሳት የቀረበ ነው።
እኔ ባለኝ ተጨባጭ መረጃ (ከፈረሱ አፍ የመስማት ያህል) የአነ ስብሃት ነጋ መፈታት ጥያቄ የቀረበው በጀዋር መሀመድ የሚመራውና በእስር ላይ ከነበሩት የኦሮሞ ፓለቲከኞች ዘንድ ነው። እነ ጃዋር መሀመድ ያቀረቡት ቅድመ ሁኔታ የእነ ስብሃት ነጋ መፈታት ብቻ ሳይሆን የኦኤምኤን ሚዲያ ከነ ሙሉ ክብሩ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ፤ የተዘጉ የኦፌኮና ኦነግ የፓርቲ ቢሮዎች በሙሉ እንዲከፈቱ፤ የተሰደዱ የኦሮሞ ፓለቲከኞችና ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ፣ የባለሃብቶቹ ንብረት እንዲመለስላቸው፤ ህውሃት እና ሸኔ የሽብርተኝነት ፍረጃው ተነስቶላቸው  በድርድርና ምክክር መድረኩ እንዲሳተፉ …ወዘተ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው።
እነዚህን የእነ ጀዋር መሐመድ ጥያቄዎች ከእስር ቤት ወደ ዓብይ አህመድ እና የኦህዴድ ብልጽግና በማመላለስ የሽምግልና ሥራ ሲሰራ የነበረው ደግሞ የአቶ ሌንጮ ለታ ቡድን ነው።
የመረጃ ምንጬ እንደነገረኝ ከሆነ ዓብይ አህመድ እነ ጀዋር መሐመድ የእነ ስብሃት ነጋን መፈታት በቅድመ ሁኔታ ማቅረባቸው ከመደንገጥም አልፎ አግራሞት ውስጥ ከቶት ነበር። እርግጥ ከቀናት ማሰላሰል በኃላ ተቀብሎታል። ወደ ተግባርም ቀይሮታል።
እናም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አታምታታ! አታስቀይስ!
Filed in: Amharic