>
5:18 pm - Wednesday June 15, 0489

የኢትዮጵያ የአምባሳደርነት ሹመት የፈሩትን ማራቂያ፤ የጠሉትን ማባረሪያ፤ ወዳጅን መጥቀሚያ ሆኖ ይቅር...?!? ( ሱሌማን አብደላ)

የኢትዮጵያ የአምባሳደርነት ሹመት የፈሩትን ማራቂያ፤ የጠሉትን ማባረሪያ፤ ወዳጅን መጥቀሚያ ሆኖ ይቅር…?!?
ሱሌማን አብደላ

 

* …  ዲፕሎማሲ ማለት አገርን መሸከም ነው። አገሪቱ በዲፕሎማሲ ኪሳራ ራቁቷን በቀረችበት አገር ላይ ስለሽ በቀለን የመሰለ የኢትዮጵያ ተሟጋች መድረከኛ ከናይል ወንዝ ተደራዳሪነት ገሸሽ ማድረግ፣ ኢትዮጵያን መጥቀም አይደለም።
ወታደር እና ዲፕሎማሲ የተለያዩ ናቸው። የትምህርት መርሀቸውም የሰማይና የመሬት ያህል እርቀት አላቸው። ግዴታ ሰውየው እንዲጠቀም ተብሎ አምባሳደር ማድረግ የግለሱቡን መጥቀም እንጅ የአገሪቱ ጥቅም አልታሰበም። በአለማችን ላይ  ባለ አራት ኮኮብ ጀነራሎቿን አምባሳደር አድርጋ የምትሾም አገር ኢትዮጵያ ናት። አጠቃላይ በዚህ ሦስት አመት ውስጥ የሚሰጡ የአምባሳደር ሹመቶች፣ የዘመድ መጥቀሚያ፣ የጎደኛ መሸኛ፣ በስልጣን ያኮረፈ ሰው ጡረታ ማውጫ፣ ለመንግሥት ስጋት የሆነን ግለሰብ ከኢትዮጵያ ማባረሪያ
 ሆነው እያለገለገሉ ነው።
ዩንቨርስቲዎቻችን ሙህራን ማውጣት አቃታቸው? የተማረ ወጣት ጠፋ.
የደህንነት ተቋሙ አሰልጥኖ ወደ ውጭ የሚልካቸው ሰዎች ጠፉ ?  እውነት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ለኢትዮጵያ እንዲጠቀም ተደርጎ ነው የተዋቀረው ? ወይስ ኢትዮጵያን አሳፍሮ እንዲያደቅ ተደርጎ ነው የተዋቀረው!
ለነገሩ እናተ ምን አስጨነቃችሁ፣ ትልውዱ እንደሆነ አንዴ በብሔር፣ አንዴ በእምነት አንዴ በክልል፣ አንዴ በከተማ ይገባኛል ጥያቄ ሲጮህ ይውላል እንጅ፣ ስለውጭ ጉዳይ መስሪያቤቱና ስለ ዲፕሎማሲ ውጤቱ የሚጠይቅ ትውልድ የለም።
Filed in: Amharic