የአማራ ብልፅግና አመራሮች፡ እውን የሰው ተክለ-ሰውነት አላችሁ?
ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ
ሰው ራሱን መሆን ካልቻለ፣ ለአዕምሮው ሳይሆን ለሆዱ የሚኖር ከሆነ፣ ለሰዎች ስልጣን መጠቀሚያ ሁኖ ራሱን ካመቻቸ፣ በአድርባይነት መንፈስ ለፖለቲከኖች ዙፋን አጃቢ ሁኖ ከሚኖር ሳይወለድ ቢጨነግፍ ይሻላል፡፡ ብአዴን/የአማራ ብልፅግና በአማራ ህዝብ ላይ ለደረሰው እና ለሚደርሰው የዘር ማጥፋት/የዘር ማፅዳት፣ ውርደት፣ግፍ፣ሰቆቃ ዋና ተጠያቂው ብአዴን/የአማራ ብልፅግና ነው፡፡
ዛሬ እናንተ በስልጣን ላይ እንድትቆዩ የአማራ ፋኖ የማይተኬ ህይወቱን ከፍሏል፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በእናንተ የአመራር ድክመት ከተመታ በኃላ ሀገር እንዳትፈርስ የጠበቀ የአማራ ፋኖ፣የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚኒሻ ፣ የአፋር ልዩ ኃይል እና ከሞት የተረፈው መከላከያ ነበር፡፡ የትህነግ ሰራዊት ወደ አፋር እና ወደ አማራ ክልል ወረራ ሲያካሂድ በመደበኛ አደረጃጀት አጥፊውን ኃይል መመከት እንደማይቻል እና የክተት አዋጅ በማወጅ ፋኖን በገሀድ እንዲሰማራ ያደረጋችሁ እናንተው ነበራችሁ፡፡ ዛሬ ስልጣናችሁ የተደላደለ መሰላችሁና የታደጋችሁን ኃይል ስሙን በማጥፋት ልትበትኑት ፈለጋችሁ፡፡ ሀገር እና ህዝብን የሚታደገውን የአማራን ፋኖን እንበትናለን ብላችሁ ሁሉንም አማራ ፋኖ አድርጋችሁት ታሪክ በተለየ አቅጣጫ እንዳይቀየር ልብ ይሏል፡፡