>
5:21 pm - Sunday July 20, 7856

"የተከፈተን የቧንቧ ውኃ ጀሪካን በመደቀን አታቆመውም!!!" (ፊልጶስ)


የተከፈተን የቧንቧ ውኃ ጀሪካን በመደቀን አታቆመውም!!!” 

 

ፊልጶስ


ሴት ልጅ የእናቷ ጓዳ ለማየት ከተሳቀቀች፤ ብዙ ተንገላቶ ላሳደገ አባት እንድ ሱሪ መገዛትና መጦር ሲሳን፤  ቀን ከሌት ደከመኝ ሳትል ከአፋ ነጥቃ እያበላች ላሳደገች  እናት ለሌማቷ የሚሆን ቁራሽ ማቅረብ  ሲያቅት፤ ታናሽ እህትና ወንድም የታላቅን እጅ እያዩ ጾምውለው ሲያድሩ   ሥራ ስርቶ  ለማደር ጎሳና ቋንቋ መመዘኛ ሲሆን፤ ጥቂቶች በቁጣን በሚታምሙበት፤ ብዙሃኑ በርሃብ አለጋ በሚገረፍበትና በሚሞትበት አገር የስርዓት ለውጥ ለማምጣት ታግሎ የሚያታግል ሲጠፋ፤ ትግል ቢካሂድና መሰዋአት ቢከፈልም ባቋራጭ ጩሊለዎችና ጎሰኞች ስልጣኑን ይዘው፤ በመግደል፣ በማጋደልና በማሳደድ የገዥነት ዕድሚያቸውን ሲያራዝሙ፤  ስደት አንዱ አማራጭ ቢሆን ምን ያስገርማል

ለነገሩማ  ሰው  ወደ ሰው አገር መሰደድ  አይደልም በገዛ አገራችው ዜጎች በማንነታችው  ከመታረድ የተረፋት፤  መሰደድና መከራተት ዕጣ ፋንታቸው ከሆነ  አራት አስርታትን አስቆጠርን እኮ። ያውም  በየሄዱበትመስጊድ እንደገባች ውሻእየታዩ። ከወለጋ እስከ አዲስ አበባ፤ ከአፋር እስከ ደብረብርሃን፤ ከቤንሽንጉል እስከ ባህርዳር፤ ከመተከል እስከ  ወሎ። 

ለዚህ ሳይሆን ይቀረል አዝማሪው፤

ግርም ያደርገኛል ያሰብኩት እንደሆን

ሰው በገዛ አገሩ ስድተኛ ሲሆን ”— ያለው።

በሳዊዲ እስር ቤት  የወገኖቻችን የሰቆቃ ዋይታ የገደል ማሚቶ ከሆነ ዓመታት አስቆጥሯል።  እንዳዶቹ  በሳዊዲ እስር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን ከዚህ በፊት አገር አለን ብለው  ተመላሽ ከሆኑ በኋላ አልሞላልህ ብሏቸው ”’ ካለፈለንአለፈልን፤ ካለያስ ምን ምርጫ አለን።ብለው    ስቃይና ሞትን ለመቀበል፤ ኑሮ እንዲሰደዱ ያስገደዳቸው ናቸው። 

 ኛን የመከራና የመሳደድ ብሎም  ግዚያዊ መጠጊያ እንኳን ማጣት ሳስብ፤ የቻይናዊያን የሃይምኖትና የፍልስፍና አባት የሆነውን ኮንፊሽየስ  የገጠመውን ያስታውሰኛል። 

ኮንፊሽየስ ብቻውን ወደ ጫካ በሜሄድ ጸሎት ማድረግ ይወድ ነበር ይባላል።  ከዕለታት በእንዱ ቀንም ኮንፊሽየስ ራቅ ወደ አለ ጫካ የተለመደውን ጸሎት ለማድረግ  ሄደ።  በአንድ ጥቅጥቅ ካለ ጫካ ከደረሰም በኋላ  በተፈጥሮ ተከቦ፣ በወፎች ዝማሪ ታጅቦና ተደላድሎ ተቀምጦ ጸሎቱን ጀመረ። ብዙ ሳይቆይ ግን  ለጀሮ የሚሰቀጥት  የዋይታና የሮሮ፤  ለቅሶ የተቀላቀለበት ድምጽ  ያለበትን ድባብ ጥሶ ወደ ጆሮ ገባ።

በድንጋጤ ተነስቶም  ሰቆቃ ወደ ሚሰማበት ድምጽን ተከትሎ  ሄደ።  ሲደርስም አንድ ሴት  እያለቀስችና መሬት ላይ እየተከባለለች አገኘ። ሴትዮዋአንድ ቀሪ ልጅን አውሬ በላውእያለች  ከአውሬው የተረፈውን የልጇን አጽምና የተቆራረጠ ልብሱን ታሳየዋለች። ኮንፊሽየስ የሚስማውንና የሚያየውን ማመን ቢያቅተውም ግዜ ወስዶ ሲትዮዋን እንደምን አረጋግቶ ማናገር ቻለ።

አንድ ቀሪ ልጀን አውሬ በላብኝ።አለች

ለምን ከተማ ውስጥ አትኖሪም  ነበር? እንዴት ጫካ ውስጥ መኖር መረጥሽ?” ሲል ኮንፊሽየስ ግራ እየተጋባ  ሃዘንተኛዋን እናት ጠየቀ።

ጌታየ! ከተማ ያሉት አውሬዎች እኮ ከዚህ ጫካ ካሉት ይብሳሉ፤ ከተማ ያሉት አንድ ልጀንና ባሌን ገለውብኝ ነው፤ ቀሪ ልጀን ሊገሉት ሲፈልጉት ለማትረፍ ብየ ከዚህ ጫካ ይዥው የመጣሁት። ይህም ጫክ አልራራልኝም ልጀን በላባኝ።በማለት በሲቃ ለማስረዳት ሞከርች። ኮንፊሽየስ የዚች ሴት  ስቃይና መከራ ምንጩ በምትኖርበት ከተማ ያለው ሥርዓት አልበኝነትና የገዥዎቹ ፍጹም አረመኔነት መሆኑን ያውቅ ነበርና፤ ሲትዮዋን ይዞ በከተማዋ ውስጥ  ስለ ህግ የበላይነትና ስለ ሰው ልጅ አንድነት በማስተማር፤ የከተመዋን አገዛዝና የህዝቡንም አመለካከት እንደ ቀየረ ይነገረል።

እኛስ ከሳውዲ አረቢያ እስከ  ወለጋ፣ ከወለጋ እስከ መቀሌ፤ ከመቀሊ እስከ  አፋር፡ ከቤንሻንጉል እስከ መተከል፤ ከአዲስ አበባ እስከ  አጣየ፤  ለቅሶ፣ ዋይታ፣ ስደትና  ግድያ በማስተናገድ ዘመናት አስቆጠርን።  በዚህ ሁሉ ስቃይ፤ የመክራችን ምንጭ ለማመልከትና መፍትሄ ለመፈለግ ያለመሞክራችን በዓለማችን የሰላም መጨረሻና የደሃደሃዋች ለመሆን በቃን። 

አሁን ለደረስንበትርስበርስ የጎሳ እልቂትም ሆነ ለስደት፤ ብሎም በገዛ ወገን ደም ካልነገድን የማንከብርና  ስልጣን የማንይዝ የመሰለበት፤ በአጠቃላይ ለዚህ  ያደረስንን ምክንያት ምንድነው ብለን አንጠይቅም፣ ብንጠይቅና ብናውቀውም በችግራችን ምንጭና ምክንያት በሆነው ነገር ላይ አንሰራም፤ ብንሰራም በመርህ ላይ ተመስርተን፣ በእውነትለእውነት ለአገርና ለህዝብ ስለማይሆን ውጤታማ እንሆንም፤ እናም ይኽው ስው የገዛ ወገኑን ንብርቱንና ሃብቱን አይደለም፣  አርዶና ስጋውን ቅርጫ አድርጎ ካልተከፋፈለ እንቅልፍ የማይወስደው ዜጎችና ትውልዶች  ለመሆን በቃን

ብዙ የአገራችን ተናጋሪዎችና  ፓለቲከኞች አገራችንን ይዟት የሚጠፋውና ለአለንበት የዘር  እልቂት፤ የዘር ፓለቲካና ክልል ነው ሲሉ ይደመጣሉ።  ነገር ግን የዘር ፓለቱካና  በህግ እንዲታገድና ዘርን ማዕከል ያደረገውም ክልል ሌላ መፍትሄ እንዲፈለግለት ሲሰሩ አይታዩም። ትላንትህገመንግሥቱ የችግራን ዋናው ምንጭ  ነው”  ሲሉ የነበሩ፤ አሁን ወደ ሥልጣነመምበሩ ሲጠጉ፤ ጭራሽ የህገመንግስቱን  አስፈላጊነት ካልጠቀሱ ቃላት ከአንደበታቸው አይወጣም።

 ላለንበት ውስብስብ ችግርና እልቂት ዋናው ምክንያት ህግመንግሥቱን መሰረት ያደረገው የዘር ቦለቲካ ስለመሆኑ አጠያያቂ አይደልም። የዘር ፓለቲካ በህግ ሳይታገድና ዘርን መሰረት ያደረገ ክልል ሳይፈርስና መፍትሄ ሳያገኝ፤ የአገርን ልኡዋላዊነት አስከብራለሁ፣ የዜጋውን ደህንነት እጠብቃለሁ፣ ሰላም አወርዳለሁ ማለትላማ አለኝበሰማይ—-’’ ነው። እስከ አሁን የተሞከረውም  ”ከእሳት ወደረመጡእንደከተተን ያየነውና ዋጋ እየከፈልነበት ያለ እውነታ ነው።  ለዚህም ነውየተከፈተውን የቧንቧ ውኃ ጀሪካን በመደቀን አታቆመውም፤ ማድርግ ያለብህ ራሱ የቧንባውን ውኃ መዝጋት ነው።የሚባለው። 

ህዝብ የአገሩ ባለቤት እንዲሆንና አንድነቱ ጠብቆ፤  ሰው በመሆኑ ብቻ ተክብሮና አክብሮ የሁላችን ኢትዮጵያ እንድትኖረን  ከፈለግን፤ የችግሩን ምንጭ  እናድርቀው፤ እሱም  ህግመንግሥቱን መሰረት ያደረገው የዘር ፓለቱካ ነውና በህግ ይታገድ! ዘርንና ቋንቋኝ መዋቅር ያደረገው ክልል መልካምድርና ምጣኔ ሃብትን ማዕከል በማድረግ ይዋቀር።

ይህን በማድረጋችን የሚመጣውን የዘረኞችና የጎሰኛችን ተቃውሞ ደግሞ የሚታገለው ህዝብ ነው። ህዝብ አንድነቱን፣ ሰላሙንና አገሩ ከማንም በበለጠ ይጠብቃልና። እንደ እናንተ እንደ ገዥዎቻችን ህገ-መንግስት ህዝብን መከፋፈልና  አምባገነንነት ቢሆንማ ዛሬ እኮ ኢትዮጵያ የለችም።  

ላለንበትም ሆነ ለመጭው ትውልድ አገር እንዲኖረውና በሰላም እንዲኖር ከፈለግን በፓለቲካው  ዓለም ውስጥ ያለንም ሆን የሰባዊ መብት ተሟጋች ነን የምንል፤ የተጫነብንን የዘር ፓለቲካና  ክልል በህግ እንዲታገድ ሁላችንም የዜግነታችን ድርሻ እንወጣ።  ገዥዎቻችንም  ”ህዝብ ሰላም ሲሆን በሥልጣናችን ላይ ይመጣል።የሚለውን  የአምባገነኖች ብሄል ትታችሁ፤  የሚጠበቅባችሁን ብታደርጉ  በሰላምና ለረጅም ግዜ  የመግዛት እድላችሁ ይሰፋል።  ”አገራዊ ምክክርምናምን እያላችሁ በህዝብና በአገር ላይ  መቀለዱን ትታችሁ  ወደገደለውግቡ ያለያ ግን የኋላኋላ  እንደ ማንኛውም አምባገነን ዋጋችሁን ታገኛላችሁ። አሁን ግን ግዜው አላችሁና  ታሪክ ሥሩ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

ፊልጶስ e-mail: philiposmw@gmail.com

Filed in: Amharic