>

አገኘሁ ተሻገር እና አብርሃም አለኸኝ ሲቀሩ፣ 60 ሚሊዮን የዘረፉት አመራሮች ከስራቸው ታግደዋል....!!! (ፈለገ ግዮን)

አገኘሁ ተሻገር እና አብርሃም አለኸኝ ሲቀሩ፣ 60 ሚሊዮን የዘረፉት አመራሮች ከስራቸው ታግደዋል….!!!
ፈለገ ግዮን

 60 ሚሊዮን ብር የዘረፉ የብአዴን  አመራሮች  የወሰዱትን ብር ከእነ ወለዱ እንዲከፍሉ አና ከዛሬ  25/06/2014  ጀምሮ  ከስልጣናቸዉ እንዲታገዱ ተወስኗል።
 
* ….የኦህዴድን ዘራፊዎችስ ማን ይሆን ሀይ የሚላቸው???
 
አቶ አብርሃም አለኸኝ በሌላ አመራር ስም ተበድሮ እንደወሰደ ታውቋል። አቶ ባህሩ በሚባልና በድርጅቱ ሚዲያ ዘርፍ ሃላፊ በኩል ገንዘቡን አስወጥቶ ወስዷል። በዚህም በአቶ ባህሩ ስም 9 ሚሊዮን ከወጣ በሗላ፣ 1.5 ሚሊዮኑን አቶ ባህሩ ወስዶ ቀሪውን ለአቶ አብርሃም ተሰጥቶታል።
አቶ አገኘሁ ተሻገር በወቅቱ ስሙ ከተላለፈ በሗላ ብሩን ሳያወጣው መቆየቱ ታውቋል። ነገር ግን የወልቃይትን ሰሊጥ ለባለሀብቶች በመሸጥ በርካታ ብር መውሰዱ ተረጋግጧል። በዚህም ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የወልቃይትን ሰሊጥ ለባለሀብቶች በመስጠት የድርሻውን አፍሷል ተብሏል። ይሄም ሰሞኑን በማስረጃ እንደሚቀርብ ተረጋግጧል።
የአማራ ብልፅግና አመራሮች ወያኔ ደብረታቦር ሲቃረብ ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም(አብቁተ) የተቀመጠውን የፓርቲውን 60 ሚሊዮን ብር ተከፋፍለው የወሰዱ አመራሮች ስም ዝርዝር
1ኛ. አብርሃም አለኸኝ የብልፅግና ሃላፊ 8 ሚሊየን
2ኛ. ደሳለኝ በላይ የብልፅግና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ 8 ሚሊየን
3ኛ. ጎሹ እንዳለማው  የብልፅግና የአደረጃጀት ሃላፊ 8 ሚሊየን
4ኛ. ፍስሃ ደሳለኝ በአሁኑ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ 4.9 ሚሊየን
5ኛ. አማኑኤል  በአሁኑ የወጣቶችና ስፖርት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ 4.9 ሚሊየን
6ኛ. ደሣለኝ የፖለቲካ ዘርፍ ጥናት ክፍል ሃላፊ 1.3 ሚሊዮን
7ኛ. ፍቃዴ ዳምጤ ኦዲትና ቁጥጥር ሃላፊ 1.5 ሚሊዮን
8ኛ. ጌትነት የፋይናንስ ሃላፊ 8 ሚሊየን
9ኛ. ጌትነት አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል 4.9 ሚሊየን
10ኛ. ጥላሁን አደረጃጀት ምክትል 4 ሚሊየን
!11ኛ. ባህሩ የድርጅቱ ሚዲያ ዘርፍ 1.5 ሚሊየን
12ኛ. አገኜሁ ተሻገር 9 ሚሊየን
ቀሪዎች ወደ 28 ለሚጠጉ ዝቅተኛ ሠራተኞች እንደ ደረጃቸው የሚሆነው አይታወቅም ተብሎ ለቤት መሥሪያ፣ ለመኪና መግዣ በሚል  በአብርሃም ትዕዛዝ አብቁተ ወጭ ተደረጎ ወደ አካውንታቸው ገብቷል።
Filed in: Amharic