>

በሙስና የሚታመሰው አዲስ አበባ ፖሊስ፣ የከተማዋ ወጣቶች እየታሰሩ ነው የሚባለው "ውሸት ነው" አለ...!!!  (ባልደራስ)

በሙስና የሚታመሰው አዲስ አበባ ፖሊስ፣ የከተማዋ ወጣቶች እየታሰሩ ነው የሚባለው “ውሸት ነው” አለ…!!!
 ባልደራስ
በምርጫ 97 በግፍ የተገደሉትን ወጣቶች 
     “ባንክ ሊዘርፉ ነበር” ብሎ ነበር !!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  የአዲስ አበባ ወጣቶች  እየታሰሩ መሆናቸውን አስተባበለ።  የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ፣ “ወጣቶች እየታሰሩ ነው የሚባለው ውሸት ነው” ብለዋል፡፡
በዚህ ውሸት ሳቢያ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ግለሰቦችን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችንና ተቋማትን የሚዘልፉ፣ የሚሳደቡና የሚያዋርዱ ሃሳቦች ይዘዋወራሉ ብለዋል።
ከዚህ በፊት፣ በምርጫ 97 ሳቢያ በመርካቶ በርካታ ወጣቶቾ በፀጥታ ኃይሎች በግፍ በተገደሉ ግዜ ፖሊስ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፣ “ባንክ ሊዘርፉ ሲሉ ነው የተገደሉት” ማለቱ ይታወሳል። ፖሊስን አሁን የሚመሩት ኃላፊዎች በዚያን ግዜ በስራ ላይ የነበሩና በህዝብ ላይ የተፈፀመው አፈናና ወንጀል ተዋናዮች የነበሩ ናቸው።
በአዲስ አበባም ሆነ በፌድራል ደረጃ ባለው የፖሊስ ኃይል ሙስና ከፍተኛ ችግር እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። የፖሊስ ሙስና በተለይ የከተማዋ ነጋዴዎችን ክፉኛ አያሰቃየ ይገኛል።  ድሮም ሆነ አሁን፣ ከገዢው ፓርቲ ጋር ተለጥፈው ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፅሙት፣ በጎንዮሽ ቀዳሚ የሙስና ተዋናዮች መሆናቸው ይታወቃል። ከተረኝነት መንፈስ ባሻገር፣ የፖለቲካ ታማኝነታቸውን ለሙስናው እንደ ሽፋን ይጠቅሙበታል።
በፖሊስ ሠራዊቱ ውስጥ ያለውን ሙስና አስመልክቶ መረጃ ያላችሁ በ inbox ልትልኩልን ትችላላችሁ።
በአዲስ አበባ በጅምላ ስለታፈሱት ወጣቶች የቀረበ የፍርድ ቤት ዘገባ ከዚህ ዜና በታች ማንበብ ይቻላል።
Filed in: Amharic