>
5:13 pm - Sunday April 19, 7626

አቶ ገብሩ አስራት ስለወልቃይት እና ራያ ጉዳይ የተናገሩት....!!! ( ነጋሪት ሚድያ)

አቶ ገብሩ አስራት ስለወልቃይት እና ራያ ጉዳይ የተናገሩት….!!!
ነጋሪት ሚድያ

የራያ እና ወልቃይት እንዲሁም ሌሎች የማንነት ጥያቄዎች ሰበቦች እንጅ የጦርነቱ ዋነኛ ምክንያቶች እንዳልሆኑ አቶ ገብሩ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል፡፡ እንኳን በአንድ ሀገር ውስጥ በሌሎች ሀገራትም መሃል ድንበር ሊያዋጋ ይችላል በአብዛኛው በሰላም በህግ ይፈታል ብለዋል፡፡ ሕግንና ሕገ መንግስትን ተከትሎ መፍታት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ድንበር በተለያዩ ወቅቶች በተለይ ከአጼ ምንሊክ በኋላ ሲቀያየር እንደነበር ገልጸው በዛው የትግራይም ቅርጽ ተቀያይሮ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ በአንድ ወቅት የትግራይ ግዛት እስከ አለውሃ ጸለምትና አፋርን ጭምር ያካትት እንደነበርና በኋላ ደግሞ አላማጣና ኮረም ወደ አማራ ክልል ታጥፈው እንደነበር የቀድሞው የትግራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ገልጸዋል፡፡
“ከ1985ዓ.ም በኋላ የመጣው አከላለል መሬት የመውሰድ አከላለል አልነበረም” የሚሉት አቶ ገብሩ አስራት ፤ የአከላለል መርሁ በቋንቋና በብሔር እንደሆን ተወስኖ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የ1985ዓ.ም አከላል ዘላቂ ላይሆን እንደሚችል ያነሱ ሲሆን፤ ሕዝቡ መክሮበት አያስፈልግም ካለ ሊቀይረው እንደሚችልና ሌላ አከላለልም ሊመጣ እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡
በአንድ ሀገር ያለው የወሰን አከላለል በየወቅቱ ሊቀያየር እንደሚችልና ቋሚ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ የድንበር ጉዳይ ይህ ሁሉ ሕዝብ ላለቀበት ጦርነት ሰበብ ይሆናል ብለው እንደማያስቡም አቶ ገብሩ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል፡፡ አሁን ላይ አከላለልን በተመለከተ መለወጥ ካለበት የራያና ወልቃይት ብቻ በማንሳት ሳይሆን በአጠቃላይ መቀየር አለበት ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡
አቶ ገብሩ፤ ቤኒሻንጉል ክልል ከፊል ከጎጃም፤ ከፊል ከወለጋ ተወስዶ እንደተቋቋመ የገለጹ ሲሆን ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ በራህሌ እና አፍዴራ የሚባሉ አካባቢዎች በትግራይ ስር እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡ አዲስ አከላለል ሲመጣ በሀብት ወይም በመሬት ስፋት ቢሆን ኖሮ አሁን በአፋር ስር ያሉት መልቀቅ ይገባ ነበር ወይ ሲሉ ጉዳዩን በጥያቄ መልሰዋል፡፡ ወደ ክፍለ ሀገር እንደመለስ ካልን እንደገና ነው ለውጥ መደረግ ያለበት ይላሉ፤
የትግራይ አማጺያን ከአፋር እና ከአማራ ይውጡ የሚሉ ጥያቄዎች እንዳሉ ያነሱት አቶ ገብሩ፤ የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ ክልል ይውጣ የሚል ጥያቄ ለምን አልተነሳም ብለዋል፡፡
የራያ እና ወልቃይት ጉዳይ በምን ይፈታ?
አቶ ገብሩ አስራት የራያ እና ወልቃይት ጉዳይ በሕግና በሕገ መንግስት እንደሚፈታ እምነት አላቸው፡፡ ሕገ መንግስቱ ላይ ብዙ ችግሮች እንዳሉ የሚቀርቡ ጥያቄዎአች እየተነሱ በመኖራቸው እርሱ እንደት ችግር ሊፈታ ይችላል የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ገብሩ፤ መንግስት እየተመራ ያለው በዚህ ሕገ መንግስት በመሆኑ መፍታት ይቻላል ብለዋል፡፡
ከሕግ ውጭ በጉልበት እንመልስ ከተባለ የማያባራ ጦርነት ሊከሰት እንደሚችልም አቶ ገብሩ የገለጹ ሲሆን ችግሮቹን ለመፍታት ግን በሰላም መነጋገር ብቸኛው አማራጭ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡ይሁንና አሁን ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊሂቃኑ ያጦዙትና ሰከን ብሎ መነጋገርን ያላስቀደመ ነው ብለዋል አቶ ገብሩ፡፡
ሕገ መንግስቱ የጸደቀው ራያ እና ወልቃይት ወደ ትግራይ ከተካለሉ በኋላ መሆኑ ችግሩን በሕገ መንግስት ለመፍታት አይቻልም የሚል ጥያቄ ከተለያዩ አካላት ቢነሳም፣ አቶ ገብሩ ግን ሕገ መንግስቱ በኋላ ቢመጣም በፊት ቢመጣም የክልሎችን ቁጥር ስላስቀመጠ ችግሩን በሕግ መፍታት ይቻላል ብለዋል፡፡ዝርዝሩን ለማንበብ፡-
Filed in: Amharic