>
5:13 pm - Friday April 19, 1118

ኢትዮጵያዊው የዕፅዋት ሊቅ ፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው የ2022 ሊንያን ሜዳሊያ ተሸላሚ ኾኑ...!!! (ዳዊት ተፈራ)

ኢትዮጵያዊው የዕፅዋት ሊቅ ፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው የ2022 ሊንያን ሜዳሊያ ተሸላሚ ኾኑ…!!!
 ዳዊት ተፈራ

የሦስት ሺህ አመት ታሪክ አለን። የ50 አመት ዕድሜ ያለው ሽልማት የለንም። ባለውለታዎቻችን እንደ አትሌቶቻችን የዕውቅና ሜዳልያዎችን ከውጪ ይዘውልን የሚመጡ ናቸው። እንዲህ ካሉ የእኛ ሰዎች መካከል ጉምቱው የዕፅዋት ሊቅ ፕሮፌሰር ሰብስቤ አንዱ ናቸው። ከዚህ ቀደም የእንግሊዝ የሮያል ቦታኒክ ጋርደንስ ኪው (Royal Botanic Garden, Kew Medal ዓለም አቀፍ ሽልማትን ወስደዋል። እ.ኤ.አ በ2018 “ለምርምርና ለፈጠራ የላቀ አስተዋፅኦቸው የሮያል ሶሳይቲ አባል ኾነው የተመረጡበትን Foreign Member of the Royal Society (ForMemRS) ክብርን ተቀብለዋል።
እንደ ፈረንጆቹ በ2021 ለትሮፒካል ዕፅዋት ጥናት የላቀ ድርሻቸው Cuatrecasas Medal for Excellence in Tropical Botany ሜዳልያ ከአሜሪካው የስሚትሶኒያን የተፈጥሮ ታሪክ ሙዚየም ተሸልመዋል።
ዘንድሮ ደግሞ የሳይንስ ሊቃውንቱ ለተፈጥሮ ሳይንስ ዕድገት ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሚሸለሙትን የሊንያን ሜዳሊያ 2022 አሸናፊ ኾነዋል።
ፕሮፌሰር ሰብስቤ እጅግ የገዘፈ አበርክቶ ያላቸው የኤርትራ እና የኢትዮጵያን እፅዋት አጥንተው የሰነዱ የኢትዮጵያ ፍሎራ ፕሮጀክትን ከ1988 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2001 ዓ.ም. ድረስ ከ17 የአፍሪካና የአውሮፓ አገሮች የተወጣጡ የዕፀዋት ተመራማሪዎችን በመምራት ስኬታማ ስራ የሰሩ “Aloes and Other Lilies of Ethiopia and Eritrea”፣ “Aromatic Plants of Ethiopia”፣ “Atlas of the Potential Vegetation of Ethiopia”፣ “Ethiopian Orchids”፣ “Field Guide to Ethiopian Orchids” በተሰኙ የምርምር ሥራ መጻሕፍቶቻቸው የሚታወቁ ናቸው።
አንድ ቀን እንደ እሳቸው ያሉ መልካም ሰዎች የኢትዮጵያ ጂኦግራፊና ሳይንስ ሶሳይቲ ሽልማትን ዕውን ሲያደርጉ መሰል ባለውለታዎቻችንን ሜዳሊያ ለመሸለም ሌላው ዓለም አይቀድመንም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
Keshelflay different idea’s  and research review
Filed in: Amharic