>
5:21 pm - Tuesday July 20, 0219

አዲስ አበባ. . . ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ! (አቻምየለህ ታምሩ)

አዲስ አበባ. . . ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!

አቻምየለህ ታምሩ

*…. በዚህ ምርጫ ተብዮው ተውኔት የአዲስ አበባ ሕዝብ እንደ ሕዝብ “ለነእስከንድር ነጋ የሰጠነው ድምጽ ተጭበርብሯል” ብሎ ድምጹን በአደባባይ ስላላሰማ በምርጫ ተብዮው ተውኔት የአዲስ አበባ ሕዝብ ከእስክንድር ነጋ ይልቅ  አፓርታይዳዊው ኦሮሙማ ይሻለኛል እንዳለ ተቆጥሮለታል።
የአዲስ አበባ ሕዝብ የእስክንድ ነጋ ጡር አለበት። አዲስ አበባን ከኦሮሙማ ስልቀጣ ለመታደግ ቀድሞ የተነሳው እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ጉዳይ በኦሮሙማ በግፍ ታስሮ በሚሰቃይበት ወቅት በአንጻራዊነት ይሻለል በሚባለው የአዲስ አበባ ምርጫ ተብዮ ተውኔት ድምጹን ለእስክንድር ነጋ እንዲሰጥ የተጠየቀው የአዲስ አበባ ሕዝብ ድምጹን የሰጠው ስለ አዲስ አበባ በግፍ ለታሰረው ለእስክንድር ነጋ ሳይሆን ዛሬ በግድ ኦሮምኛ እንዲዘምር ለሚያደርገው ለአፓርታይዳዊው ኦሮሙማ ነበር።
በዚህ ምርጫ ተብዮው ተውኔት የአዲስ አበባ ሕዝብ እንደ ሕዝብ “ለነእስከንድር ነጋ የሰጠነው ድምጽ ተጭበርብሯል” ብሎ ድምጹን በአደባባይ ስላላሰማ በምርጫ ተብዮው ተውኔት የአዲስ አበባ ሕዝብ ከእስክንድር ነጋ ይልቅ  አፓርታይዳዊው ኦሮሙማ ይሻለኛል እንዳለ ተቆጥሮለታል።
‘Elections have consequences’ እንዲሉ እነሆ ዛሬ አዲስ አበቤ ከእስክንድር ነጋ ይሻለኛል ብሎ “የመረጠው” አፓርታይዳዊው ኦሮሙማ  እያንዳንዱ አዲስ አበቤ ልጆቹን  በኦሮምኛ በግድ እንዲስዘምርና የኦፓርታይዳዊውን ኦሮሙማ የገዳ አርማ ከፍ አድርገው እንዲያውለበልቡ ግዳጅ ተጥሎበታል።
ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ ቢሆንም ቅሉ አሁንም ቢሆን በእስክንድር ነጋ ላይ ክህደት የፈጸመው የአዲስ አበባ ሕዝብ ከአጨብጫቢነት በመውጣት በኦሮምኛ በግድ እንዲዘምርና ኦሮሞ እንዲሆን ከሚያስገድዱት ኦነጋውያን መላቀቅ ከፈለገ የኦሮሙማ ናዚዝም ቀድሞ ከገባቸው ከነእስክንድር ነጋ ጋር መደራጀትና መታገገል አለበት።
ኦሮሙማ በአዲስ አበባ ላይ እየደገሰ ያለው መከራ እያንዳንዱ አዲስ አበቤ ኦሮምኛ እንዲዘምርና የገዳ አርማቸውን እንዲያውለበልብ ግዴታ በማድረግ ብቻ የሚያበቃ አይደለም። ኦሮሞ አይደለም፤ ወይም ኦሮሞ አይመስልም እያሉ ከአርሲ፣ ከሐረርጌ፣ ከጅማ፣ ከኢሉባቦር፣ ከወለጋ፣ ወዘተ በግፍ እንሚያፈናቅሏቸው ድኆች ሁሉ ኦሮሞ አይደለም ወይም ኦሮሞ አይመስልም የሚሉትን አዲስ አበቤ ሁሉ ነገ በየቤቱ እየዞሩ ከቤቱ አፈናቅለው፤ እድሜ ልኩን ያፈራኸውን ጥሪት ቀምተው ሜዳ ላይ ይጥሉታል።
ይኽንን የሚጠራጠርና  በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ አዲስ አበባ ውስጥ ለማድረግ ስላቀደው አስቀድሞ ይጮኽ የነበረው እስክንድር ነጋ ያበደ የሚመስለው ቢኖር የራሱን ጤነኛነት ይመርመር።
Filed in: Amharic