>

በአብን ገጽ ላይ የወጣው የበለጠ ሞላ መግለጫ...!!! (አሳዬ ደርቤ)

በአብን ገጽ ላይ የወጣው የበለጠ ሞላ መግለጫ…!!!

አሳዬ ደርቤ


*…. ከደቂቃዎች በፊት የተወገደውን መግለጫ በስክሪን ሹት ይዘነዋል…!!!

➔በአማራ ፋኖ ላይ እየተወሰደ ያለውን የማሳደድ ዘመቻ ሊቃወም ቀርቶ የፋኖን ሥም ሳይጠራ በቸልታ ያለፈ፤

➔ከአብን አባላት ውጭ ባለው የአማራ ኤሊትና ወጣት ላይ እየተወሰደ ያለውን አፈሳ የደገፈ፤

➔አፈናውን የሚቃወሙ አክቲቪስቶችን፣ ጋዜጠኞችንና ሚዲያዎችን “የወያኔ ተከፋዮች” በማለት የነቀፈ፤

➔”ተጠርጣሪዎች የሚያዙበት መንገድ ጥንቃቄ የተሞላበት አለመሆኑ መንግሥታችንን እያስተቸ ነው” የሚል መልዕክት ያስተላለፈ፤

➔የአባላቱን እና የሕዝብን ግብረ መልስ ላለመቀበል የሐሳብ መስጫ ሳጥኑን የቆለፈ፤

➔ከአብን በተጨማሪ ሕዝብን ወርውሮ ብልጽግናን ለመቀላቀል በወሰነ አመራር በብስጭት መንፈስ የተጻፈ….. እጅግ አሳፋሪ መግለጫ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

ክቡር ሚኒስቴር በአጭር ጊዜ ጭምብልዎን በማውለቅዎ እናመሠግናለን ‼️

አፈናን እና ብልጽግናን የተቃወሙ ወገኖችን ሁሉ በወያኔ ተላላኪነት ፈርጆ ለጠላት ጥቃት ተጋላጭ ካደረገውና ከደቂቃዎች በፊት ከተወገደው መግለጫ ላይ አለመሳተፋቸውን የገለጹ የአብን አመራሮች፦

1. ዶክተር ቴዎድሮስ ኃ/ማሪያም

2. ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ

3. አቶ ክርስቲያን ታደለ (ገብርዬ)

4. አቶ የሱፍ ኢብራሒም (ሀጂ ነስረላህ)

5. አበባው ደሳለው

Filed in: Amharic