አፈናዉን ጠ!ሚሩ በቀጥታ እንደሚመሩት ተረጋግጧል…!!!
ስንታየሁ ቸኮል
*… እንዲያዙ የተባሉ ሰዎች በደብዳቤ ከጠሚ ጽ/ቤት ወጥቷል
ተጨማሪ የሚታፈኑ የሰዎች ዝርዝር ደርሶናል ከውስጥ በወጣ መረጃ በሌሎች ቡድኖች ክትትል እና ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በወጣ ደብዳቤ ስም ዝርዝር መሰረት በ 5 ግሩፕ ተከፋፍሎ ወደ ስራ ሊገባ ነው። እንዲያዙ የተባሉ ማለትም፦
1ኛ-ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አምበርብር
2ኛ- ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ
3ኛ-የአብን አመራር ዶ/ር ቴዎድሮስ ሀይለማሪያም
4ኛ-ጋዜጠኛ ማዕዛ መሀመድ እንዲሁም
5ኛ- የማሕበራዊ ሚዲያ አንቂ የሆነው አሳየ ደርቤ የሚገኙበት ናቸው። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከመጣው ደብዳቤ ውጪ በኦህዴድ ተማኞች ሰዎች ለብቻ እንዲታፈን ተደርጓል።
ይታፈኑ የተባሉት ዝርዝራቸው የተገለጸዉ አምስቱ ሰዎች በፍርሃት ዝም እንዲሉ ማድረግ ካልተቻለ በእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው ማወከብና በመንግስት አክቲቪስቶች ይታሰሩ ግፊት በማስጀመር የተቀናጀ የማህበራዊ ሚዲያ ስም የማጥፋት ዘመቻ መክፈት ከፍ ካለ ደግሞ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በተያዘበት ሁኔታ አንድ በአንድ እንዲያዙ ማድረግ አመጽ ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱትን ግለሰቦችን ፀጥ ማሰኘት ይቻላል በማለት መመሪያ እንደተሰጠ ምንጫችን ለማረጋገጥ ችለዋል።
የመረጃ ምንጫችን እንደሚሉት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መስከረም አበራን ጨምሮ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ጠሚሩ በሚመሩት ክትትል እንዲያዙ አቅጣጫ ቢቀመጥም አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለጊዜው ተሰውረዋል ተብሎ ሪፖርት ተደርጓል። ይላሉ። ከላይ የተጠቀሱት አምስት ሰዎች በብሔራዊ ደህንነት ክትትል ቡድን ውስጥ ያሉ ናቸው ተብሏል።