>

የብርጋዴር ጄነረል ተፈራ ማሞ የፍርድ ቤት ውሎ...  (አ.ብ.ክ.መ )

የብርጋዴር ጄነረል ተፈራ ማሞ የፍርድ ቤት ውሎ… !

 

አ.ብ.ክ.መ 


ጠቅላይ ፍ/ቤት ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል።

በዚህም ፤ የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራየን ጨርሸ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቢ ህግ ለመላክ በዝግጅት ላይ ነኝ ያለ ሲሆን የክልል ዐቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ አዎ ምርመራው አልቋል የክስ መመስረቻ ጊዜ 15 ቀናት ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል።

የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው ምርመራ ካለቀ ደንበኛችን የተከሰሱበት ጉዳይ ዋስትና የሚያስከለክል ባለመሆኑ እና  ተጠርጣሪው ደንበኛችን ታዋቂ ሠው በመሆናቸው ሊጠፉ ስለማይችሉ የደንበኛችን የዋስትና መብት ይከበርላቸው ሲሉ ተከራክረዋል።

ፍርድ ቤቱም ሲሰጥ የነበረው የጊዜ ቀጠሮ ምርመራው ያለቀ በመሆኑ የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ ዘግቷል።

በመቀጠል የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ዐቃቤ ህግ አስተያየት እንዲሰጥበት አድርጓል።

ዐቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሰሱበት ጉዳይ የሽብር ወንጀል ስለሆነ በተጨማሪም ከሚዲያ ጋር በተያያዙ ሌሎች ተጨማሪ ክሶች ሊቀርቡ ስለሚችሉ ዋስትና ሊፈቀድላቸው አይገባም ሲል ተከራክሯል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የተጠርጣሪ የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ለሰኔ 3/2014 ዓ/ም  ቀጠሮ ሰጥቷል።

መረጃው የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው።

Filed in: Amharic