ስንታየሁ ቸኮል ላይ የግድያ ዛቻ የሰነዘረው ኮማንደር ከአቶ አገኘሁ ተሻገር ቀጥተኛ ትእዛዝ እንደሚቀበል ተደረሰበት…!
ጌጥዬ ያለው
ስንታየሁ ቸኮልን እንደሚገድለው የዛተበት፣ የፍርድ ቤት መጥሪያን አልቀበል ያለው እና ‘ስንታየሁን ትደግፋላችሁ’ በሚል ሦስት ፖሊሶችን በእብሪት ያሰረው የባሕር ዳር ፖሊስ መምሪያ 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኮማንደር #አሻግሬ ይግዛው ትዕዛዝ የሚቀበለው ከአቶ አገኘሁ ተሻገር እንደሆነ መረጃ ደርሶናል።
ይህ ሰው ከመስተዳድሩ ፖሊስ ኮሚሽን/መምሪያ ይልቅ ለአገኘሁ የሚታዘዘው ደግሞ በሚስቱ በኩል ነው።
ሚስቱ #የምሥራች አበጀ ትባላለች። በገዥው ፓርቲ ካቢኔ ውስጥ ስትሰራ፤ ተወልዳ ካደገችበትና ብዙ ከኖረችበት ጭልጋ በአገኘሁ ተሻገር መራጭነት ወደ ባሕር ዳር ተዘዋወረች። በአገኘሁ ትዕዛዝ ባሕር ዳር ተቀምጣ የምትሠራው አማራውን በጎጠኝነት መከፋፈሉ ላይ ነው። ይህ በአገኘሁ መሪነት በርካታ አባላት ያሉት ከፋፋይ መዋቅር ነው። በባሕር ዳር የተለያዩ ክፍለ ከተሞች በጎጠኝነት የሚከፋፍሉ ሰዎችን እየመለመሉ ከአገኘሁ ጋር የማገናኘት ሥራውን ከሚሠሩት መካከልም አንዷ ነች። በዚህ ተሳክቶላት አንድነቱ እንደ ሞፈርና እርፍ ፍፁም የተዋደደውን አማራ መከፋፈል ባትችል እንኳን ጥረቷ በአገኘሁ ዘንድ አስመስግኗታል።
አገኘሁ የአማራ ብልፅና ሓላፊ ሲሆን እርሷን ደግሞ የምኒልክ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ሓላፊ አድርጎ ሾማት። እርሷም በተሻሻለ ሥልጣን አማራን የመከፋፈል ሥራዋን ቀጠለች። ቀጥሎም በእድገት በከተማ መስተዳድሩ ውስጥ በከፍተኛ ሹመት ላይ ተቀመጠች።
ዛሬም በዚች ሴት በኩል ነው ስንታየሁ ውሃ በሌለበት፣ ፍራሽና መብራት በሌለበት ተባያማ ጨለማ ቤት ውስጥ እየተሰቃየ ያለው።