>

የሕግ ማስከበርን በተመለከተ የጠ.ሚ/ሩ ምላሾች...!!! ጠ/ም ቢሮ

የሕግ ማስከበርን በተመለከተ የጠ.ሚ/ሩ ምላሾች…!!!

ጠ/ም ቢሮ


በብልጽግና በኩል በሕዝቡን ፍላጎት ለማድመጥ ስንሞክር ሰላም፣ የኑሮ ውድነት እና መልካም አስተዳደር ዋነኛ ጥያቄዎች ሆነው ተነስተዋል። ከሁለት ወር በትፊ በብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ተሰብስበን፣ ጉዳዮችን ለይተን አውጥተናል። በዚህም በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል የጸጥታ ሁኔታ፣ በአዲስ አበባ (ቅሚያ እና የጠላት ቅጥረኞች) እንዲሁም በሶማሌ ደግሞ አልሸባብና ኮንትሮባንድ ዋነኛ የሰላም እክል ሆነው ተገኝተዋል። ከበ2 ወራት ውስጥ 1000 የሚበልጡ የሸኔ አባላት ርምጃ ተወስዶባቸዋል። በተሰራው የሰላም ማስከበር ሥራ በሁሉም ስፍራዎች መልካም ውጤት አግኝተናል። ከዚያ በኋላ መልሰን ሕዝቡን ስናወያይ መልካም ምላሽን አግኝተናል። ርምጃዎች ሲወሰዱ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማስለመድ በተቻለ መጠን ሰላማዊ አማራጮችን ለመከተል ተሞክሯል። ይህም መንግሥትን አቅመ ቢስ አስመስሎታል። ነገር ግን፣ ኃይልን የመጠቀም ስልጣን ያለው መንግሥት እንደ ሆነ መታወቅ አለበት።

በአማራ ክልል በተወሰደው ርምጃ የፌደራል መንግሥት ሳይሆን፣ የክልሉ ልዩ ኃይል ነው የተሳተፈው። የየክልሉን የሕግ ማስከበር ዘመቻ የሚመራው የክልሉ ኃይል ነው፣ ከፌደራል የሚያገኘው የቴክኒክ ድጋፍ ብቻ ነው። ርምጃው አካባቢያዊ መሆኑን፣ በሕዝብ ጥያቄ እንደ ተጀመረ፣ በተገኘው ውጤት ሕዝብ ደስተኛ መሆኑን እና ሰላም እያገኘ መሆኑ መታወቅ አለበት። በሀገር ወዳዶች ስም የሚቆሙ አጥፊዎችን ለሕግ ማቅረብ ግዴታ ነው። በክልሉ በሕግ ማስከበር ርምጃ 3500 የከዳ ሰራዊት ተይዟል፣ ከዚሁም ውስጥ ከ2000 የሚበልጠው ከልዩ ኃይል የወጣ ነው። ሃሺሽ፣ የውጪ ምንዛሬ፣ ተቀጣጣይ ፈንጂ እና ቦንብ ይዘናል። ከዘመቻው በኋላ የገባ እና መከላከያ ብቻ የሚታጠቀው አዲስ አይነት ጠመንጃ አለን። መከላከያን ገድለው ያንን ጠመንጃ ታጥቀው የተገኙ ሰዎች ናቸው የተያዙት።  እሳት ቤት እንዳያጠፋ ሰብሰብ ተደርጎ መያዝ አለበት። ነጻነትና ብልጽግና የሚኖረው ከመረጋጋት ጋር ነው።

በስህተት የተያዘ፣ ያለአግባብ የተጎዳ ሰው ሊኖር ይችላል። ተጣርቶ የእርምት ርምጃ ሊወሰድ ያስፈልጋል።

Filed in: Amharic