>

"በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ በ15 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰረት ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳልፏል...!!!" (ታሪኩ ደሳለኝ)

“በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ በ15 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰረት ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳልፏል…!!!”

ታሪኩ ደሳለኝ


*…. ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በመፅሄቱ ላይ ወታደራዊ ምስጢሮችን ጽፏል – ይህን እያጣራሁ ነው በማለት ከጥበቃው ጋር  ክርክር ተካሂዷል።

በዛሬው ዕለት በተሰየመው ችሎት አቃቤ ህግ “አንድ መቶ ሰባት የፍትህ መፃሄቶችን እየመረመርን ነው:: በመፅሄቱ ላይ ወታደራዊ ምስጢሮች ተፅፈዋል:: ተጠርጣሪው የተጠረጠረበት ወንጀል አመፅና ብጥብጥ ለማስነሳት ስለሆነ በፁሁፎቹ ምክኒያት ሞትም ተከስቶ ይሆናል ስለዚህ ይሄንም አጣርተን ክስ ለመመስረት 15 ቀን ፍርድ ቤቱ ይፍቀድልን”

ብለዋል::

ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ በበኩላቸው “እስካሁን ድረስ አቃቤ ህግና ፖሊስ አብረው እየሰሩ ነው የቆዩት:: አቃቤ ህጉም ጉዳዩን ከመጀመሪያ ጀምሮ ያውቀዋል:: ይሄንም ችሎቱ ይረዳል::

ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ምንም ተጨማሪ ቀን ሳይፈቅድ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የተፈቀደለትን የዋስትና መብት አክብሮ ከስር እንዲፈታው እጠይቃለሁ” ብለዋል::

ዳኛው አቃቤ ህግ የጠየቀውን አስራ አምስት ቀን ይሁን በለው ለአቃቤ ህግ 15 ቀኑን ፈቅደዋል::

በመሆኑም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  ለሰኔ 22/2014ዓ.ም ተቀጥሯል::

[እስካሁን የነበረው ሂደት…]

የፖሊስ ኮሚሽኑ መርማሪ ፖሊሶችን አቃቤ ህጎች

↘️ በመጀመሪያ ጋዜጠኛ ተመስገን ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት በዩትዩቦች ይጠቀማል አሉ፤

↘️ከአስር ቀን ቀጠሮ በኋላ በዩትዩብ ሳይሆን በፍትሕ መፅሔት ይጠቀማል አሉ፤

↘️ፍርድ ቤቱ ይሄን ተከትሎ በዋስ እንዲወጣ ወሰነ፤

↘️ይሄን ተከትሎ የፖሊስ መርማሪዎችና አቃቤ  ህጎች ይግባኝ ብለው ወንጀሉ ውስብስብና ሌሎች አባሬዎች አሉ አሉ፤

↘️ፍርድ ቤቱም ሰኔ 2/2014 በዋለው ችሎት ደግሞ ፖሊስ 8 ቀን ወስዷ ምርምሮ ለሰኔ 10/2014  በድጋሚ ያቅርባቸው ብሎ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ወሰነ::

↘️የሰኔ 10/2014 ቀጥሮ ቀርቶ ዛሬ ሰኔ 7/2014 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳልኝ ከ5 ቀናት በኋላ ፍርድ ቤት ቀርቦ አቃቤ ህጎቹም የተመስገን ፁሁፍ ወታደራዊ ሚስጥሯች ፅፏል:: ፁሁፍን ተከትሎ ሞትም ተከስቶ ሊሆን ይችላል የሚል አዲስ ክስ አምጥተዋል::

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እስራት፣ በግለሰቡ ብቻ ሳይሆን ሙያው ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው ስንል የሰነበትነው በዚህ ምክንያት ነው።

ቤተሰቦቹ እና የፍትሕ መፅሔት ባልደረቦች

Filed in: Amharic