>
5:13 pm - Wednesday April 20, 8692

ዐብይ አሕመድ ወይስ ጭራቅ አሕመድ? (መስፍን አረጋ)

ዐብይ አሕመድ ወይስ ጭራቅ አሕመድ?

መስፍን አረጋ


የዐብይ አሕመድ አንድና ብቸኛ ዓላማ የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ አጥፍቶ የኦሮሞን አጼጌ (oromo empire) በመመሥረት በቀሩት ኢትዮጵያውያን ላይ በግድ መጫን ነው ማለት የአዋጁን በጆሮ ነው፡፡  በዚህ ኦነጋዊ ዓላማው መሠረት ባለፉት ዐራት ዓመታት ይህ ነው የሚባል መሰናክል ሳያጋጥመው በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ የአማራን ሕልውና ከትልቅ የጥያቄ ምልክት ውስጥ አስገብቷል ማለት ቀባሪውን ማርዳት ነው፡፡  በዚህ ፍጥነት መጓዙን እንዲቀጥል ከተፈቀደለት፣ ኦነጋዊ ዓላማውን ሙሉ በሙሉ የሚያሳካበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ደግሞ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡  

ስለዚህም መሠረታዊው አንገብጋቢ ጥያቄ ዐብይ አሕመድ ፀራማራ ዓላማውን ለማሳካት ምንም መሰናክል ሳያጋጥመው በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ አሁን ከደረሰበት ወሳኝ ደረጃ ላይ ሊደረስ የቻለው ለምንድን ነው የሚለው ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ ለዚህ ደረጃ የበቃው በኦነጋዊ ሠራዊቱ ሊሆን አይችልም፣ የኦነግ ሠራዊት ጨለማን ተገን አድርጎ ቤታደሮችን (civilians) ከማረድ በስተቀር በታሪኩ አንድም ጊዜ ድል ማድረግ ቀርቶ በቅጡ ተዋግቶ የማያውቅ ግሳንግስ ሠራዊት ነውና፡፡  ዐብይ አሕመድ ለዚህ ደረጃ የበቃው ፀራማራ ዓላማውን ከሚጋራው ከወያኔ ጋር  ስለሚተባበር ሊሆን አይችልም፣ የወያኔ ሠራዊት እስካፍንጫው ቢታጠቅም በአማራዊ አዛዥ ከሚመራ የአማራ ሠራዊት ፊት መቆም እንደማይችል ቅራቅርና ሌሎች የምዕራብ ጎንደር የጦር ዐውድማወች በግልጽ አስመስክረዋልና፡፡  

ዐብይ አሕመድ እዚህ ደረጃ ሊደርስ የቻለው የሕልውና ጠላቱ እሱና እሱ ብቻ መሆኑን የአማራ ሕዝብ በጽኑ ተረድቶ በጹኑ ስላልታገለው ብቻ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ዐብይ አሕመድን ከጫንቃው ላይ ካወረደ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡  መለስ ዜናዊ ሲሞት ወያኔ እንደፈራረሰ፣ ዐብይ አሕመድም ሲወገድ ከመሬት አንስቶ ሰማይ ያደረሰው ኦነግና፣ ከሞት አፋፍ አንስቶ እንዲያንሰራራ ያደረገው ወያኔ ሁለቱም ፍርስርሳቸው ይወጣል፡፡  

የአማራ ሕዝብ ዐብይ የሕልውና ጠላቱ የሆነውን ዐብይ አሕመድን ማስወገድ የሚችለው ግን በጽኑ ሲታገለው ብቻ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ዐብይ አሕመድን በጽኑ የሚታገለው ደግሞ ዐብይ አሕመድ የአማራን ሕዝብ በጽኑ የሚጠላውን ያህል የአማራ ሕዝብም ባጸፋው ዐብይ አሕመድን በጽኑ ሲጠላው ነው፣ በጽኑ ያልጠላኸውን በጽኑ አትታገለውምና፡፡  የአማራ ሕዝብ ሕልውናውን ማስቀጠል የሚችለው ዐብይ አሕመድን በጽኑ ጠልቶ በመጸየፍ አር እንደነካው እንጨት አሽቀንጥሮ ሲጥለው ብቻና ብቻ ነው፡፡  

ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ሕልውና ያሳስበናል የምትሉ የሚዲያ ሰወች፣ ይህን እኩይ ፀራማራ ግለሰብ ዶክተር፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ እሳቸው እያላችሁ በማይገባው ክብር በመጥራት የአማራ ሕዝብ ጽኑ ጠላቱን በጽኑ እንዳይጠላ አታድርጉት፣ በክብር የሚጠሩትን በጽኑ አይታገሉትምና፡፡    

ዐብይ አሕመድ ለአማራ ሕዝብ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሳይሆን በላዔ አማራ ጭራቅ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ የአማራን ሕዝብና አማራዊ አመራሮቹን በግፍ ከጨፈጨፈና ካስጨፈጨፈ በኋላ ደስታውን አበባ በመትከልና ሕንፃ በመመረቅ በይፋ የሚገልጽ ኦነጋዊ አረመኔ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ እኔን ብትነኩ መቶ ሺወቻችሁ ባንድ ጀምበር ትታረዳላቸሁ እያለ በግላጭ የሚዝት፣ ባራጅ ሠራዊቱ የሚተማመን ኦነጋዊ አራጅና አሳራጅ ነው፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ይህን ኦነጋዊ አውሬ በማናቸውም መቸት (መቸና የት) ላይ መጥራት ያለበት ዐብይ አሕመድ ብሎ ሳይሆን ጭራቅ አሕመድ ብሎ ነው፡፡  

ግራኝ አሕመድ ዛንተራ ላይ ወደቀ፡፡  ጭራቅ አሕመድስ የሚወድቀው የት ይሆን?  ሰንጋተራ?    

Email: mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic