በኦሮሞ ወረራ የጠፉ ብሔሮች!
ጌጥዬ ያለው

አማራ ትልቅ ታሪክ ያለው፣ ሰፊ ቁጥር ያለው፣ በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በመላው ዓለም የሚኖር፣ በአማራ መስተዳድር ወሰን ውስጥ በአንድ ላይ ተሰባስቦ የሚኖር፣ በተለያዩ ጦርነቶች ጀግንነቱን ያስመከረ ታላቅ ሕዝብ ነው። በመሆኑም ጠላት ቢደራረብ የህልውና ስጋት የለበትም የሚል መከራከሪያ ሊገሳ ይችላል። ሆኖም ይህ ስህተት ነው። ኩርዶች በአመዛኙ ከአማራ የሚመሳሰል ታሪክ አላቸው። ከህልውና ስጋት ግን አልተረፉም። የኩርድን ጉዳይ ለጊዜው እንተወውና ኦሮሞዎቹ በኢትዮጵያ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያደረጉትን እንመልከት፦
ኦሮሞዎች በ1522 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ ጊዜ ጀምሮ የከብት ጭራ እየተከተሉ በመጓዝ ነባር ሰላማዊ የኢትዮጵያ ብሔሮችን አጥፍተዋል። በገዳ ማህበር መመሪያ መሰረት ‘ገበሮ’ እና ‘ሞጋሳ’ በሚሉት መውረሪያ ስልታቸው የበርካቶችን ባህል፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት ብሎም ጥቅል ማንነት አጥፍተዋል። ዛሬ ኦሮምኛ የሚናገሩትና በዳሳ፣ ጃቢሳ ቅብጢሳ የሚባሉት ትውልዳቸው ወደ ኋላ ቢዘረዘር ኦሮሞዎች አይደሉም። በሞጋሳና ገበሮነት ማንነታቸውን የተነጠቁ ናቸው። ዛሬም በኦሮሚያ መስተዳድር ውስጥ የሚኖሩ ጉራጌዎች የቀበሌ መታወቂያቸው ላይ ብሔራቸውን ‘ጉራጌ’ ብለው ማስፃፍ አይችሉም። ጉራጌኛ እየተናገሩ ‘ኦሮሞ’ ተብሎ ነው የሚፃፈው።
በኦሮሞ ተወላጁ የነጋሶ ጊዳዳ ጥናት መሰረት በሰዮ ወለጋ አካባቢ ብቻ ሞጋሳ ከአሥር በላይ ነባር የኢትዮጵያ ነገዶችን አጥፍቷል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ካንቺ፣ ኮንቺ፣ ሙጩኮ፣ ጋንቃ፣ ወራጎ፣ ዳምታ፣ ካዛ፣ አጋዲ፣ ገበቶ፣ መጀንግ፣ ክወራ፣ ክዋማ እና ቡሳሴ ተጠቅሰዋል፡፡ በሌሎች ጥናቶች መሰረት ደግሞ 28 ነባር ብሔሮች በኦሮሞ ወረራ ጠፍተዋል። ከ28ቱ መካከል ጋፋት፣ ማያ፣ አንፊሎና ወርጅህ ይገኙበታል፡፡ እነኝህ ነገዶች ከነቋንቋቸውና ሌሎች ማንነቶቻቸው ቁጥራቸው ቀስ በቀስ እንዲቀንስና ፈፅሞ እንዲጠፉ የተደረጉት የገዳ ማህበር ባመጣው ወረራ እንደሆነ ዶክተር ሀብታሙ ተገኘ ‘በራራ ቀዳሚት አዲስ አበባ’ በተሰኘው መፅሀፋቸው አብራርተዋል፡፡ በተለይ የማያ ብሔር በዛሬው ናዝሬት፣ ደብረ ዘይትና ሽንብራ ኩሬ (ሞጆ) አካባቢ በስፋት ይኖር የነበረ እና በጦርነት ብቃቱ የተመሰከረለት ነበር።
የኦሮሞ ወረራ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ባደረገው ወረራ ክፉኛ የተዳከሙት የሺናሻ፣ የዘይ፣ የአርጎባ እና የማኦ ማሕበረሰቦችም በመጥፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ የሞት አፋፍ ላይ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡
በዚህ ወቅት በተለይም ከአራት ዓመት በፊት ጀምሮ ኦሮሞ ያልሆኑትን ሁሉ በመግደል፣ ንብረታቸውን በመዝረፍና በማቃጠል እየተፈፀመ ያለው እንቅስቃሴ ተቋርጦ የነበረውን የወረራ ዘመቻ ለማስቀጠል ያስቀጠለ ድርጊት ነው፡፡ ‹በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረው የኢሬቻ በዓል ከ150 ዓመታት በኋላ ዳግም መከበር ጀመረ› እንደተባለው ሁሉ ‹ተቋርጦ የነበረው የገዳ የመስፋፋት ዘመቻ ተጀመረ’ ተብሎ ስላልተነገ እንጂ ወረራውና ጭፍጨፋው በተለይም በአማራ ላይ መፈፀም ከጀመረ ቆይቷል።