>

አብይ አህመድን ጨምሮ  የኦሮሞ ድርጅቶችና መሪዎች አመለካከት ይሄ ነው...!!! (ግርማ ካሳ)

አብይ አህመድን ጨምሮ  የኦሮሞ ድርጅቶችና መሪዎች አመለካከት ይሄ ነው…!!!

ግርማ ካሳ

*…. የአገዛዝ ጀምበር ያዘቀዘቀችበት ጨፍጫፊው ቡድን ማለቃቀስ ጀምሯል:-

“ከፈጣሪ በታች አዲስ አበባ  ለኦሮሞ መገዛት ሰውኛ ሳይሆን ተፈጥሯዊ  ግዴታዋ ነው፣ ተፈጥሮን ደግሞ ብትቃወም ውጤቱ አውሎ ንፋስ ነው፣ ረሃብ ነው፣ ድርቅ ነው፣ ጠኔ ነው፣መጠማት ነው፣ መታፈን ነው….አዲስ አበባ የኦሮሚያ ልጅ ናት፡፡ ልጅ አባትን መቃወም ውጤቱ ፆም ማደር ነው።”

እንግዲህ ከአስር ሜሊዮን በላይ የሆነከው የአዲስ አበባ ህዝብ፣ ከወለጋና አርሲ፣ ከባሌና በሻሻ የመጡ ዘረኞች በዚህ መልኩ ሲቀልዱብህ፣ መብትህን  ሲረግጡህ፣ አንገትህ ሲያደፉህ ማየት አንተን አይመጥንም፡፡ ስትታገስቸው፣ ለሰማ ብለህ ዝም ስትል ትንኝና ከንቲኡ የሆንክ ይመስል በዚህ መልኩ እየናቁህ ነው፡፡  ማንነትህ ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መልኩ የምታሳይበት ጊዘው አሁን ነው፡፡

የአገዛዝ ጀምበር ያዘቀዘቀችበት ጨፍጫፊው ቡድን ማለቃቀስ ጀምሯል:-

አፋኙና ጨፍጫፊው የኦህዱእድ/ኦነግ ብልጽግና  አገዛዝ ፣ አሁን ወያኔ ላይ እያሳበበ ነው፡፡ በተለያዩ መድረኮችና አመራሮች አስር ሺህ መግለጫ እያወጡ፣ ሰዎቹ መደናበራቸው፣ መሸነፋቸው እያሳዩ ነው፡፡

” ወያኔ ሀገር የማፍረስ እኩይ ዓላማውን በጦርነት ማሳካት ስላልቻለ በየቦታው ባደራጃቸውና ባስታጠቃቸው ተላላኪ ቡድኖች አማካኝነት የጅምላ ግዲያ በተልዕኮ እየፈፀመና እያስፈፀመ ይገኛል።” ሲል ላለፉት 4 አመታት በአገሪቱ ሲደረግ ለነበረው የዘር ጭፍጨፋና እልቂት ፣ ሃላፊነት ከመውሰድ ፣ ራሷ መላ ቅጡ ጠፍቶባት ችግር ላይ ባለችው ወያኔ ላይ እያሳበቡ ነው፡፡ ሰዎቹ ምን ያህል ነውረኞች መሆናቸውን በዚህ መረዳት ይቻላል፡፡

በጣም ያሳቀኝ ደግሞ እንደነ ኢትዮ 360 ያሉ ሜዲያዎች ነጥለው እንደ አሸባሪ መቁጠራቸው ነው፡፡

“በተለይ በአሸባሪው ህዋሓት ጁንታ ቡድን ፋይናንስ የተደረጉ ሚዲያዎችን በመጠቀምና እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈፀም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማደናቀፍ ተማሪዎችን በብሄርና በሀይማኖት በመከፋፈል ግጭት እንዲፈጠር ለማነሳሳት ሌት ተቀን አሸባሪዎች እየሰሩ መሆናቸውን የጋራ ግብረ ኃይሉ ደርሶበታል።”

ኢትዮ360 በዩቱብ ከ50 መቶ ሺህ የሚሆኑ መልእክቶችን ያስተላልፋል፡፡ ሜዲያው ለሚሊዮኖች  የሚያስተላልፈው በዋናነት በመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት ነው፡፡ መረጃ ቲቪ ኢትዮ360ን ብቻ ሳይሆን በርካታ ሜዲያዎችን (ራስ ሜዲያ፣ ማማ ሚዲያ….)  ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ማህበረሰብ እንዲሰማ እያደረገ ያለ ሜዲያ ነው፡፡ በፍቃደኝነት በመረአጅ ቲቪ ውስጥ እሰራለሁ፡፡ መረጃ ቲቪ 100% በኢትዮጵያዉያን ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ተቋም እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ህወሃት እየደገፋቸው ነው፣ የሕወሃት ተአልላኪዎች ናቸው ብለው እነ አብይ አህመድ  ሲናገሩ ከመስማት የበለጠ አስቂኝ ነገር የለም፡፡

Filed in: Amharic