>
5:21 pm - Tuesday July 20, 1627

እኔን ለመግደል ሰላሳ ዲናር ተቀብላችሁ በዱር  በየገደሉ የምትወጡ የምትወርዱ ወንድሞቼ ሆይ ስለ ድካማችሁ ሁሉ አዝናለሁ...!!! (ዘመነ ካሴ )

እኔን ለመግደል ሰላሳ ዲናር ተቀብላችሁ በዱር  በየገደሉ የምትወጡ የምትወርዱ ወንድሞቼ ሆይ ስለ ድካማችሁ ሁሉ አዝናለሁ…!!!

ዘመነ ካሴ 

፩. እኔ ያልተከሰስኩበት የወንጀል አይነት የለም። ብዙ ከንቱዎች ከመቶ ያላነሱ የክስ ዝርዝሮችን በእኔና በአማራ ህዝብ ላይ ይዘረዝራሉ። ከክሶቹ አንዱም እንኴን እኔን አይገልፁም። ሁሉም የክስ ዝርዝሮች ውጤታቸው የዜሮ ብዜት ነው።

☝️ከሁሉም የክስ ዝርዝራቸው ውስጥ ግን እጅግ የሚገርመኝና ውስጤን የሚረብሸኝ “ኢትዮጵያን ለማፍረስና ኢትዮጵያዊያንን ሰላም ለመንሳት ከሌሎቹ የውጭ አማፅያን ጋር ይሰራል!” የሚለው ነው።

☝️ሁሌም እንደምለው እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ። መሳቅ መጫዎት የምወድ። በፍትህና በእኩልነት የማምን። በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል ግን ያመኛል ! በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል ግን በደንብ ያመኛል።

☝️እናቴን ስታዋርዳት ቆሜ ከማይ ሺህ ጊዜ ግደለኝ !

☝️እህቴን ስታዋርዳት ከማይ ግን ሺህ ጊዜ ግደለኝ !

☝️አማራን ስትገድል ከማይ ሺህ ጊዜ ግደለኝ ! አሳደኝ !

☝️ያመኛል ! አልችልም ! ይሄንን መቸም አልችልም !

፪. እኔ ዘመነ ካሴ እንደ ሌላው ሰው ሁሉ በአንድ በሆነ ምክንያት ልትጠፋ የምትችል ህይወት ያለኝ ሰው ስሆን የእኔን ህይወት ሊነጥቃት የሚችለው ግን የድንግል ማርያም ልጅ እሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ብየ የማምን ሰው ነኝ። ስለዚህ እኔን ለመግደል ሰላሳ ዲናር ተቀብላችሁ በዱር  በገደሉ የምትወጡ የምትወርዱ ወንድሞቼ ሆይ ስለ ድካማችሁ ሁሉ አዝናለሁ።

+++ ሞትን ተሸክማችሁ ሞትን ፍለጋ ስለምን ትዞራላችሁ +++

፫. አሁን የአማራ ህዝባዊ ሀይል ትግል ላይ ነው ያለው። የትግሉ ዋና አላማ ደግሞ ለአማራ ህዝብ ፍትህና እኩልነት ነው። ከዚህ የተለየ ምንም አላማ የሌለው መሆኑን ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያውቀው ይገባል።

☝️የአማራ ህዝባዊ ሀይል(ፋኖ) ለስልጣን አይታገልም፣ ስልጣንም አይፈልግም!

☝️የአማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) መንግስት ለመሆን አይታገልም፣መንግስት መሆንም አይፈልግም!

☝️የአማራ ህዝባዊ ሀይል ኢትዮጵያን ለማፍረስ አይታገልም፣ ስትፈርስ ማየትም አይፈልግም፣አፍራሿንም እስከ መጨረሻው ድረስ ይታገላል። አፍራሿን ያፈርሳል !

፬. የአማራ ህዝባዊ ሀይል ዋና አላማው ሰላም፣ፍትህ እና  እኩልነት ከተቀበሩበት ቦታ እንዲወጡ ማስገደድ ነው። አትድከሙ ! ከዚህ የተለየ የትግል አላም የለንም !  ከንቱዎች ምንም ስለማታውቁት ነገር እያወራችሁ  የታሪክ ተወቃሽ ባትሆኑ ደስ ይለናል።

#ይህንን እዚህ ላይ የምንፅፈው እነሱም በዚህ እየፃፋ ስማችንን ስለሚያጠፋ ነው !

በመጨረሻም ስለ ሰላም፣ፍትህና እኩልነት የምትታገሉ ሁሉ ታላቅ አክብሮት አለን። የትግላችን አጋር በመሆን አብራችሁን የተሰለፋችሁ ሁሉ ክብር ይስጥልን !

-ትግላችን ይቀጥላል! 

-ኢትዮጵያ ሆይ ብክድሽ ፈጣሪ ይካደኝ ! 

-አማራ ሆይ ብክድህ ፈጣሪ ይካደኝ ! 

-እናሸንፋለን !

Filed in: Amharic