>

መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበር እና የማስከበር ሀላፊነቱን በአግባቡ ይወጣ!!!! (ኢሰመጉ)

መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበር እና የማስከበር ሀላፊነቱን በአግባቡ ይወጣ!!!!

ኢሰመጉ


ህገወጥ እስር

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ኢትዮጵያ በጋዜጠኞች፣ በተፎካካሪ ፓርቲ አባላትና አመራሮች፣ በማህበረሰብ አንቂዎችና በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች

ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ህገወጥ እስር ሲፈጸም ቆይቷል፡፡ ይህ ድርጊት ተገቢውን የህግ ስነ-ስርዓት ያልተከተለ እና አስገድዶ የመሰወር(እገታ) ድርጊት

በመሆኑ ለተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ማለትም ማሰቃየትን ለመሳሰሉ ድርጊቶች በርን የሚከፍት ነው፡፡ ይህንንም ጉዳይ አስመልክቶ ኢሰመጉ በተደጋጋሚ መግለጫዎችን በማውጣት ማንኛውም የመንግስት አካል ከዚህ ህገወጥ ድርጊት እንዲቆጠብ ሲያሳስብ የቆየ ቢሆንም በመነግስት በኩል የሚታይ አና አስተማሪ ሕጋዊ እርምጃ ባለመወሰዱ ሕገወጥ ድርጊቱ ቀጥሏል፡፡

በቅርቡ ከእስር በዋስ እንዲለቀቅ የተደረገው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በትላንትናው እለት ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ አካላት

መወሰዱን እና ቤተሰቦቹ እንዲሁም ጠበቃው ያለበትን በማፈላለግ ላይ እንደሆኑ እና ያለበትን ማወቅ እንዳልቻሉ ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

በተጨማሪም ገጣሚ እና የማህበረሰብ አንቂ የሆነው በላይ በቀለ ወያ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከሚገኘው ጊዮርጊስ ምግብ ቤት

ትፈለጋለህ ተብሎ ተወስዶ ይህ ሪፖርት እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ቤተሰቦቹ ያለበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ እንዲሁም ማን እንደወሰደው ለማወቅ እንዳልቻሉ ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል።

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች፡

በምስራቅ ወለጋ ዞን ሳስጋ ወረዳ በጉምቢ፣ ጂማታና ሀሮ ቀበሌ ውስጥ ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ኢሰመጉ ከአካባቢው ባሰባሰባቸው መረጃዎች መሰረት

በመንግስት የጸጥታ አካላት እና በሸኔ መካከል በነበረው ውጊያ መ/ር ሀብታሙ እና ወ/ሮ አበራሽ ጉልማ በጥይት ተመተው መሞታቸውን እንዲሁም

የመ/ር ሀብታሙን አስክሬን በጊዜው መቅበር ሳይቻል ቀርቶ ሜዳ ላይ ካደረ በኋላ በሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም መቅበር መቻሉን፣የ12 ዓመት ታዳጊ

የሆነችው ቢሊሴ ቶሎሳ ተመትታ በመቁሰል የአካል ጉዳት የደረሰባት ሲሆን በተጨማሪም በርካታ ቁጥር ያላቸው ከብቶች መገደላቸውንና ንብረት

ውድመት መድረሱን አረጋግጧል፡፡ በዚህ ግጭትም ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች በሰላም መንቀሳቀስ አንዳልቻሉ፣ በአካባቢው በሁለቱ

ወገኖች መካከል በሚደረጉ ውጊያዎች ነዋሪዎች ስጋት ውስጥ እንደሆኑና አካባቢውንም ለቀውለመውጣት ምቹ ሁኔታ እንደሌለ ኢሰመጉ ከቦታው ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ተያያዥ የህግ ግዴታዎች፡

የሰብዓዊ መብቶች ዓለም አቀፍ መግለጫ(UDHR) እና የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለምአቀፍ ቃልኪዳን(ICCPR) ሁለቱም ስምምነቶች በአንቀጽ 9  ላይ ማንም ሰው በዘፈቀደ ሊያዝእንደማይችል፣ ማንም ሰው ከህግ ውጪ እንደማይያዝ፣ እንደማይታሰር እና የግል ነጻነቱን እንደማያጣ ይደነግጋሉ፡፡

በተመሳሳይ የአፍሪካ ቻርተር በሰዎች እና ህዝቦች መብቶች ስምምነት አንቀጽ 6 ላይ በተመሳሳይ ማንም ሰው የነጻነትና የአካል ደህንነት መብት

እንዳለው ይህንንምመብት ከህግ አግባብ ውጪ እንደማያጣ እና ማንም ሰው በዘፈቀደ ሊታሰር እንደማይገባ ይደነግጋል፡፡በተጨማሪም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ

ህገመንግስትም እንዲሁ በአንቀጽ 17 ላይ የነጻነት መብትን ሲያብራራ ማንኛውም ሰው በህግ ከተደነገገው ስርዓት ውጪ ሊያዝ፣ ክስሳይቀርብበት

ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰር አይችልም ሲል ይደነግጋል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግስት በአንቀጽ 28 ላይ በስብእና ላይ ስለሚፈጸሙወንጀሎች

ሲያብራራ በአስገዳጅ ሰውን መሰወር በስብዕና ላይ የሚፈጸም ወንጀል መሆኑን እውቅና ይሰጣል፡፡

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ባታጸድቀውም ሰዎችን አስገድዶ ከመሰወር ለመጠበቅ የወጣው ዓለም አቀፍ ስምምነት (International Convention for  the Protection of All Persons from Enforced Disappearance) በአንቀጽ 5 ላይ በስፋት ወይም ስልታዊ በሆነ መንገድ የሚፈጸም

አስገድዶመሰወር በዓለም አቀፍ ህጎች ትርጉም በተሰጠው መሰረት በስብዕና ላይ የሚፈጸም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪም ይኸው

ስምምነት በአንቀጽ1(1) ላይማንምሰው ለአስገድዶ መሰወር ተጋላጭ መሆን እንደሌለበትበመደንገግ ይህንን ወንጀል የፈጸሙ አካላትን መንግስት

በወንጀል ተጠያቂእንዲያደርጋቸው ይደነግጋል፡፡

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (UDHR) አንቀጽ 3፣ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል-ኪዳንም (ICCPR) በአንቀጽ 6(1)

እና9(1) ላይ እያንዳንዱ ሰው በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነቱ የመጠበቅ መብት እንዳለው ያረጋግጣል። ይህንኑ መብት በማረጋገጥ፣ መንግሥታት

በቃል-ኪዳኑ (ICPR) የተረጋገጡትን መብቶች በግዛታቸውየማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት ግዴታ እንዳለባቸውም በአንቀጽ 2(1) እና 2(2)

ይደነግጋል።በተጨማሪም የአፍሪካ ቻርተርበሰዎች እና ህዝቦችመብቶች (ACHPR) አንቀጽ 4 ማንኛውም ግለሰብ በሕይወትየመኖር መብቱና

የአካሉደህንነት ሊከበርለትናሊጠበቅለት እንደሚገባና እነዚህን መብቶቹን በዘፈቀደ ሊነፈግ እንደማይችል ተመላክቷል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት

አንቀጽ 14 “ማንኛውም ሰውሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትናየነጻነት መብት አለው” ሲልይደነግጋል።

መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበር እና የማስከበር ሀላፊነቱን በአግባቡ ይወጣ!

Filed in: Amharic