ሰውዬው አገር የማፍረስ ተልዕኮ ይዞ ወደ ሥልጣን የመጣ ነው ስንል በምክንያት ነው…!!!
አሳዬ ደርቤ
➔ኦነግን ከእነ ትጥቁ አስገብቶ ተጨማሪ ወጣቶችን የሪፑብሊክ ጋርድ ጠመንጃ ያስታጠቀ፤
➔ያደራጀውን የሽብር ድርጅት ሥም “ሸኔ” በሚል ባለቤት አልባ ሥም የደበቀ፤
➔የሮዋንዳን የጭፍጨፋ ታሪክ በኢትዮጵያ ምድር ለመድገም የሚያስችል ሞት የማለማመድ ተግባር ውስጥ የተዘፈቀ፤
➔የአማራዎችን ሕይወት ከአትክልት በታች ያወረደ፤
➔አገር የማፍረስ ተልዕኮ ይዞ ወደ ሥልጣን የመጣ፤
➔በአማራ ላይ የጥላቻ ስብከትን በግልጽ የሚያስተላልፉ ኃይሎችን ከመፍጠር አልፎ፣ እራሱም የጥላቻ መምህር ሆኖ ባስተላለፈው ስብከት አማራዎችን ለእልቂት የዳረገ፤
➔አገሪቷን ቀርቶ አንደበቱን መቆጣጠር የማይችል፤
➔ስንቱን የአማራ ክልል አመራር አሽቀንጥሮ ሲጥል የሽመልስ አብዲሳን ካቢኔ የማይሻር አድባር ያደረገ፤
➔ብአዴን የተባለውን ድርጅት በሆዳሞች ሞልቶ ያለ ጠባቂ የሚጨፈጨፍ ሕዝብ የፈጠረ፤
➔ስልጣኑን መልቀቅ ብቻ ሳይሆን በዘር ማጥፋት ወንጀል መጠየቅ የሚገባው፤