>

ቶሌ፤ የቦሌ መለማመጃ! (መስፍን አረጋ)

ቶሌ፤ የቦሌ መለማመጃ!

መስፍን አረጋ


ጭራቅ አሕመድ በመዋሸት ለመዋሸት የተፈጠረ የውሸት ሰው ቢሆንም፣ ጭራቅነቱን በግልጽ አሳይቶ ሕዝብን በማሸበር ለማስፈራራት የሚጠቅመው ሁኖ ሲያገኘው ግን እውነቱን ይልቁንም ደግሞ የልቡን ይናገራል፡፡ ለምሳሌ ያህል  ጭፍጨፋ ይቆማል ብላችሁ እንዳታስቡ በማለት ፓርላማ ላይ የተናገረው ውነቱን ይልቁንም ደግሞ የልቡን ነው፡፡  

በጭራቅ አሕመድ ዕይታ መሠረት ቶሌ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ፣ የጭፍጨፋ መለማመጃ ጢኖ ጭፍጨፋ እንጅ ጭፍጨፋ አይደለም፡፡  ዋናው ጭፍጨፋ አዲሳባ ላይ ሊፈጸም እቅድ የተያዘለት ጃኖ ጭፍጨፋ ነው፡፡  የዚህን አዲስ አበባ ላይ ሊፈጽመው ያቀደውን የጃኖ ጭፍጨፋ እቅዱን ደግሞ አሁንም የልቡን በመናገር መንግስቴን ልትነኩ ብትሞክሩ መቶ ሺወች ባንድ ጀምበር ይታረዳሉ በማለት የማወጅ ያህል በግልጽ አሳውቋል፡፡  አራጆቹ የሚመጡት ደግሞ ከየትም ሳይሆን ካዲሳባ ዙርያ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡   

ስለዚህም አዲሳቤ ሆይ፣ ለሌላ ለማንም ብለህ ሳይሆን ለራስህ ቆዳ ስትል ጭራቅ አሕመድን በማናቸውም መንገድ (by any means necessary) ባስቸኳይ ጨርቅ እንድታደርግ ትመከራለህ፡፡  አለበለዚያ በቶሌ የተለማመደው የጭራቅ አሕመድ ጭራቅ ሠራዊት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ በቦሌ መጥቶ፣ የያንዳንድህን ቤት እያንኳኳ ልጆችህና ወላጆችህን እፊትህ ካረደ በኋላ አንተኑ ራስህን ያወራርድሃል፡፡  በቶሌ የተፈጸመው ጭፍጨፋ አንተን የማይመለከት አድርገህ፣ ምን ተዳየ ብለህ፣ በባይተዋርነት እጅህን አጣጥፈህ ከተቀመጥክ ደግሞ፣ በቅርብ ቀናት ውስጥ ወር ተራህ ደርሶ የጭራቅ አሕመድ ጭራቅ ሠራዊት ቦሌ መጥቶ መክተፍ ብቻ ሳይሆን ቢከታትፍህ ይገባዋል፣ አንተም ራስህ ጭራቅ ነህና፡፡  ጭራቅን ጭራቅ ቢያንቀው ማን ይጨንቀው፡፡      

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic